Get Mystery Box with random crypto!

'አዲስ እይታ ለስኬታማ ቢዝነስ!' በሚል ርዕስ ስልጠና ተሰጠ። አዲስ እይታ በንግድ እና ኢንቨስ | Addis Eyita

"አዲስ እይታ ለስኬታማ ቢዝነስ!" በሚል ርዕስ ስልጠና ተሰጠ።

አዲስ እይታ በንግድ እና ኢንቨስትመንት የማማከር ሥራ አገልግሎት ከሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር "አዲስ እይታ ለስኬታማ ቢዝነስ!" በሚል ርዕስ ለተለያዩ አካላት ስልጠና ተሰጠ።

ቦሌ በሚገኘው በዓለም ሲኒማ ሴኔ 25 ቀን 2014ዓ.ም በተሰጠው ስልጠና ላይ ቢዝነስ የጀመሩ ማህበራት አባላት እና ስራ ፈጣሪ ግለሰቦች ተሳታፊ ሆነዋል።

የሰው ባህሪ እና የቢዝነስ ስነ-ልቦና ፣ በቢዝነስ ውስጥ ስኬትን ማስቀጠል እንዴት ይቻላል፣ ቢዝነስ ለመስራት እራስን መስራት ፣ የቢዝነስ አመራርና አስተዳደር እና የማኑፋክቸሪንግ ቢዝነስ ባህሪያት በሚሉ ርዕሶች በዶክተር ወሮታው በዛብህ በዶክተር እዮብ ማሞ ፣በዶክተር ኤሊያስ በላይ ፣ በአቶ ሳሙኤል ተክለእየሱስ ፣ በአቶ ክብረት አካሳ እና በአቶ ተመስገን ዐብይ ተሰጥቷል።

ከአዲስ እይታ የስልጠና መርሐግብር ፍጻሜ በኃላ ከዚህ ቀደም የአዲስ ህይወት ስልጠና ወስደው በስራ ላይ የሚገኙ ስራ ፈጣሪዎች እና አጋር አካለት የዕውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።