2022-07-11 21:02:59
ቅሬታ !
የቤት ደርሷቸው እንደሆነ ለማወቅ የሚጠባበቁ ነዋሪዎች የስም ዝርዝር ይፋ ባለመደረጉ ቅሬታ እንዳላቸው ገለፁ።
የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ዓርብ ቢወጣም እስካሁን የቤት ዕጣ የደረሳቸው ሰዎች ስም ዝርዝር በይፋ አልተገለፀም።
ይህም የቤት ዕጣ ደርሷቸው እንደሆን ለማወቅ እየተጠባበቁ ባሉ ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሯል።
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን አርብ ለቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በሰጠው ቃል ፥ የቤት ዕጣ የወጣላቸው ነዋሪዎች ዝርዝር እስከ ዛሬ ሰኞ ድረስ በኮርፖሬሽኑ ድረገፅ እንዲሁም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ታትሞ እንደሚወጣ ገልጾ ነበር።
እጥፍ ክፍያም ተከፍሎ ቢሆን በጋዜጣው ታትሞ እንዲወጣ እየተሰራ እንደነበር ኮርፖሬሽኑ መገለፁ አይዘነጋም።
የስም ዝርዝሩ ግን ዛሬ በድረገፁም ሆነ በጋዜጣው አልወጣም።
የስም ዝርዝር ይፋ ባለመደረጉ ቤት ደርሷቸው እንደሆነ ለማወቅ የሚጠባበቁ ነዋሪዎች ቅሬታ እንዳደረባቸው ገልፀዋል።
የደረሳቸው ሰዎች ከታወቁ ለምን ይህን ያህል ሊቆይ ቻለ ? በዲጂታል ሚዲያ ለምን ማሰራጨት አልተቻለም ? በኦንላይን ይታያል ተብሎ በአርቡ ስነስርዓት ላይ ተገልፆ ነበር ይህ ለምን አልሆነም ? ከተማ አስተዳደሩ ግልፅ ማባራሪያ ሊሰጥ ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል።
ቅሬታዎችን ይዘን ዛሬ ከጥዋት ጀምሮ ለሚመለከታቸው አካላት ስልክ ብንደውልም ስልክ አይነሳም።
አሁንም ዕጣ የወጣላቸው ነዋሪዎች የስም ዝርዝር በተመለከተ ማብራሪያ ለማግኘት እየጣርን እንገኛለን ሲሳካልን እና ትክክለኛ መረጃ ሲደርሰን እንልክላችኃለን።
4.1K views18:02