Get Mystery Box with random crypto!

በአፋር ክልል በአብኣላ በኩል እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል መጓጓዝ ጀመረ በዓለም ምግብ ድርጅት አማ | አዲስ ቲቪ Adiss Tv AMN

በአፋር ክልል በአብኣላ በኩል እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል መጓጓዝ ጀመረ

በዓለም ምግብ ድርጅት አማካይነት 21 ከባድ የጭነት መኪናዎች የእርዳታ እህል በመጫን በአፋር ክልል በአብኣላ በኩል የሰብዓዊ እርዳታ በየብስ ትራንስፖርት ወደ ትግራይ ክልል ማጓጓዝ መጀመሩን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ውስጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዜጎችን ህይወት ለመታደግ ሁሉንም አማራጮች በመጠቀም የሰብዓዊ እርዳታን ለማቅረብ እንቅስቃሴ መጀመሩ የሚታወስ ነው፡፡

ውሳኔው ከተወሰነበት ቀን ጀምሮ የመድኃኒት፣ የህክምና መሳሪያዎች፣ ገንዘብና አልሚ ምግቦችን ረጂ ድርጅቶች በቻሉት መጠን በአየር ትራንስፖርት በየዕለቱ ማጓጓዝ መጀመራቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አመላክቷል፡፡

በዛሬው ዕለትም በዓለም ምግብ ድርጅት አማካይነት 21 ከባድ የጭነት መኪናዎች የእርዳታ እህል በመጫን በአፋር ክልል በአብኣላ በኩል የሰብዓዊ እርዳታ በየብስ ትራንስፖርት ወደ ትግራይ ክልል ማጓጓዝ መጀመራቸውን ነው ያስታወቀው፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቱን በተሟላ ሁኔታ ለማስኬድ ከተባበሪና ባለድርሻ አካላት ጋር ለመስራት ዛሬም ቁርጠኛ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥቷል፡፡

@Addis_Tv