Get Mystery Box with random crypto!

የነዳጅ ስርጭት ችግር የሚፈጥሩ የነዳጅ ማደያዎችን እንደማይታገስ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወ | አዲስ ቲቪ Adiss Tv AMN

የነዳጅ ስርጭት ችግር የሚፈጥሩ የነዳጅ ማደያዎችን እንደማይታገስ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው በየጊዜው በሚስተዋለው የነዳጅ እጥረት ዙሪያ በከተማው ካሉ የነዳጅ ማደያ ባላቤቶች ጋር የተወያየ ሲሆን በውይይቱ የነዳጅ አቅርቦት ችግር እንዳሌለ ነገር ግን ከስርጭት ጋር ተያይዞ እጥረት መከሰቱ ተገልጿል፡፡

ሆኖም ከስርጭት ጋር ተያይዞ አንዳንድ ማደያዎች የሚፈጥሩትን እንግልትና አሻጥር ፈር ለማስያዝ ጠበቅ ያለ እርምጃ እንደሚወስድና ብልሹ አሰራርን እንደማይታገስ መግለፁን ከአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የቢሮው ሃላፊ አቶ አደም ኑሪ ÷ከስርጭት ጋር ተያይዞ በአንዳንድ ማደያዎች የሚፈጠረው ብልሹ አሰራር የምርት ስርጭት ፈተና መሆናቸውን አብራርተው ፤ያልተገባ ጥቅም በመፈለግ እጥረቱን በሚያባብሱ የነዳጅ ማደያዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስረድተዋል።

ችግሩን በዘላቂነት ለመከላከልም የነዳጅ አቅርቦትን በማሳደግ እና ቁጥጥሩን በማጠናከር ሌሊት ነዳጅ በሚሸጡት ላይ የመጠን ማሻሻያ እንደሚደረግና በዘመናዊ የመረጃ ዘዴ ማደያዎች እለታዊ መረጃን ለቢሮው እንዲያሳውቁ ማድረግ የሚያስችል አሰራር የሚዘረጋ መሆኑንም የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

በከተማዋ ከ134 የነዳጅ ማደያዎች 117 ማደያዎች አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ሲሆን ÷ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ በፈጠሩና በምሽት በበርሜል ነዳጅ ሲሸጡ የተገኙ ሶስት ማደያዎች ላይ ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ መቻሉን አቶ አደም ኑሪ ተናግረዋል፡፡

@Addis_Tv