Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ በአሰላና ኢተያ አካባቢ የ50 ሜጋ ዋት የእንፋሎት ሀይል ማመንጫ ግንባታ ለማከናወን የ1 | አዲስ ቲቪ Adiss Tv AMN

በኢትዮጵያ በአሰላና ኢተያ አካባቢ የ50 ሜጋ ዋት የእንፋሎት ሀይል ማመንጫ ግንባታ ለማከናወን የ100 ሚሊየን ዶላር ስምምነት ተፈረመ።

ስምምነቱን የተፈራረሙት የቱሉ ሞዬ ሀገር በቀል ድርጅትና ሚትስቡሽ ኮርፖሬሽን ሲሆኑ ፕሮጀክቱ የሚከናወነው ከፈረንሳይ መንግስት በተገኘ ፈንድ ነው ተብሏል።

ከእንፋሎት የሚገኝ የሀይል አማራጭ ከአከባቢ ብክለት የፀዳና ዘላቂ በመሆኑ ተፈላጊነቱ ከፍተኛ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ኢትዮጵያም በዘርፉ እምቅ ሀይል ስላላት ማልማት እንደሚገባ ተመላቷል፡፡

“የእንፋሎት ሀይልን በሀገራችን በስፋት መጠቀም እንፈልጋለን” ያሉት የማዕድን ሚንስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ፥ አማራጭ የሀይል ምንጮችን ለማስፋፋት መንግስት ቁርጠኛ ነው ብለዋል።

የበለጸገችና ገናና ሀገር ለመገንባት የሃይል አቅርቦት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፥ ለዚህም መንግስት የሚቀጥሉትን 10 አመታት የሚያገለግል ፖሊሲ ቀርፆ ወደ ስራ መግባቱን ተናግረዋል።

ኢንጅነር ታከለ አክለውም በሀይል አቅርቦት ዘርፉ ላይ የግል ዘርፉ እንዲሳተፍ እንደሚፈለግና በዚህም መንግስት ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቀዋል።

@Addis_Tv