#ጤናመረጃ
የአብሽ 10 የጤና ጥቅሞች!አብሽ ለጤና ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ ያውቃሉ? ለልብ ድካም፣ ለደምግፊት፣ ኮሌስትሮል ለመቀነስ፣ ለጨጓራና በስካር በሽታ ለሚሰቃዩ ፍቱን መድሃኒት ነው::ገና ለወለዱ እናቶችም የጡታቸውን መጠን የተወሰነ ለመጨመር ይጠቅማል።
ጥቅሞቹ በዝርዝር ቀጥሎ ቀርበዋል፦
※
የስኳር በሽታን ለመቆጣጠር ይረዳል፦ አብሽ ደም ውስጥ የሚገኘውን የስኳር መጠን በመቆጣጠር ኢንሱሊን መቋቋምን ይቀንሳል።
※
የልብ በሽታን ያስወግዳል፦የልብ ጉዳትን ለመከላከልና ኦክሲዳቲቭ ውጥረት ለማስወገድ ይረዳል።
※
የወር አበባ ቁርጥማትን ያስታግሳል፦አብሽ ከቁርጥማት በተጨማሪ ራስ ምታት፣ ማቅለሽለሽና ድካምን ለመቀነስ ይረዳል።
※
የጡት ወተት ምርትን ያሻሽላል፦አብሽን መጠጣት የወተት ምርትን የሚጨምር ውህድ ስላለው፤ ለሚያጠቡ እናቶች ይረዳል።
※
የምግብ መፍጨት ችግርን ይረዳል፦የሆድ ድርቀትንና ከጨጓራ መቆጣት የተነሳ ለሚከሰት የምግብ መፍጨት ችግርን ለመከላከል ይረዳል።
※
የጸጉር መሳሳትን ለመከላከልና ለፀጉር እድገት ጠቃሚ ነው።የተፈጨ አብሽን ሳይወፍር በብርጭቆ ውሀ በማዋሀድ መቀባት።
※
አብሽ መጠጣት አቅም ማጣትን ለማከምና የወሲብ ችሎታን ለመጨመር ይረዳል።※
አብሽ መጠጣት ብጉርን ለመከላከል ይረዳል።※
ፀረ-እርጅና ጥቅም አለው፦ለቆዳችን አስደናቂ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን የእርጅና ምልክትን እንደ የቆዳ መጨማደድና ቀጫጭን መስመርን ያስወግዳል።
※
ቆዳን ለማርጠብ፦ የአብሽ የሚሙለጨለጨው በሀሪ የደረቁ ቆዳዎችን በማስወገድ ቆዳችን እንዲረጥብ ይረዳናል።
አጠቃቀሙ፣ በ1ብርጭቆ ውሃ ውስጥ 2 የሾርባ ማንኪያ የተፈጨ አብሽ በማዋሀድ መጠጣት። ተፈጥሯዊ ስለሆነ ምንም አይነት ጉዳት የለውም። ክብደት እንዳይጨምሩ በመጠኑ ይጠቀሙ።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter