Get Mystery Box with random crypto!

ትዊተር አርማውን ከምናውቃት ወፍ ወደ ‘ኤክስ’ ምልክት ሊቀይር መሆኑን ኢላን መስክ ገለጠ! የትዊ | አዲስ ሪፖርተር - NEWS

ትዊተር አርማውን ከምናውቃት ወፍ ወደ ‘ኤክስ’ ምልክት ሊቀይር መሆኑን ኢላን መስክ ገለጠ!

የትዊተር ባለቤት ኤላን መስክ የትዊተር ‘ሎጎ’ ከተለመደው የወፍ ምልክት ወደ ‘ኤክስ’ [X] ሊቀይር መሆኑን ገልጧል።የቢዝነስ አርማውን ወደ ኤክስ ኮርፕ የቀየረው መስክ “እንደውም ይህን ሊሆን የሚገባው ቀድሞ ነበር” ብሏል።

ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት ቢሊየነሩ ልክ እንደ ቻይናው ዊቻት ኤክስ የተባለ “ሁሉን ያካተተ” መተግበሪያ የመሥራት ሐሳብ አለው።የትዊተር አርማ የሆነችው ወፍ እንደምትቀየር እሑድ ዕለት ያሳወቀው መስክ “በቃ ሁላችንም የትዊተር አርማን ቻው የምንልበት ጊዜ ተቃርቧል። ቀስ በቀስ ደግሞ ሁሉንም ወፎች” ብሏል።

የዛኑ ዕለት አዲስ ጊዜያዊ አርማ ይፋ እንደሚደረግም ያሳወቀው መስክ የእንግሊዝኛ ኤክስ ፊደል ምልክት ያለበት አርማ ለጥፏል።የትዊተር ሥራ አስፈፃሚ ሊንዳ ያካሪኖ በትዊተር ገፃቸው አርማ መቀየሩ አስደሳችና አዲስ ጅማሮ ነው ብላለች።በእስያ ሃገራት ለምሳሌ በሕንድ ፔይቲኤም፤ በኢንዶኔዥያ ደግሞ ጎጄክ የሚባሉ መተግበሪያዎች ሁሉን አቀፍና በርካቶች የሚጠቀሙባቸው ናቸው።

Via BBC

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter

አማራ ለሆኑ ብቻ

https://t.me/+fQqpVIV6_Q82ZGQ0
https://t.me/+fQqpVIV6_Q82ZGQ0