Get Mystery Box with random crypto!

'የሬሜዲያል ፕሮግራም ተመዝጋቢዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን እስከ ህዳር 12 ድረስ ማስተካከል ይችላ | አዲስ ነገር መረጃ

"የሬሜዲያል ፕሮግራም ተመዝጋቢዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን እስከ ህዳር 12 ድረስ ማስተካከል ይችላሉ"

በ 2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የሬሜዲያል (Remedial) ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምርጫቸውን በየትምህርት ቤቱ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ ህዳር 12 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል እንደሚችሉ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በዚህ ዓመት የሬሜዲያል ፕሮግራም አዲስ አበባ፣ ሀዋሳ፣ አርሲ፣ ኮተቤ፣ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሮግራሙን የማያስተናግዱ ዩኒቨርሲቲዎች መሆናቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

@Addis_News