Get Mystery Box with random crypto!

በሞባይል ባንኪንግ የተጭበረበረች የወልቂጤ ከተማ ነዋሪ እራሷን አጠፋች በማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል | አዲስ ነገር መረጃ

በሞባይል ባንኪንግ የተጭበረበረች የወልቂጤ ከተማ ነዋሪ እራሷን አጠፋች

በማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን በሞባይል ባንኪንግ የተጭበረበረች የወልቂጤ ከተማ ነዋሪ እራሷን ማጥፋትዋ የዞኑ ፖሊስ ገለፀ።

በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ሶሬሳ ህንፃ ስር  ከሚገኝ የግለሰብ ሞባይል ሴንተር  ተቀጥራ የምትሰራዉ 21 ዓመቷ ወጣት መቅደስ መኮንን  አራት  የሞባይል ስልኮችን በ69 ሺህ ብር  ለመግዛት ከፈቀዱ  ሁለት ግለሰቦች የገዙበትን ክፍያ በሞባይል ባንኪንግ ሊያስተላልፉላት ትስማማና ገቢ የሚደረግበት አካዉንት ትሰጣቸዋለች።

  ሁለቱ ግለሰቦች አካዉንቱን ተቀብለዉ ሞባይላቸዉን  ከነካኩ በኋላ ስለመድረሱ ማረጋገጫ   የሆነዉን ተጠናቋል (complet) የሚለዉን መልእክት ያሳይዋትና ሞባይላቸዉን ተረከበዉ ይሄዳሉ።

ወጣቷ አራት ሞባይል ስልክ  የሸጠችበት ገንዘብ  ገቢ መደረጉ ለማረጋገጥ ወደ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመሄድ ስታረጋግጥ ገንዠቡ ገቢ አለመደረጉ ሲነገራት መታለሏን ካረጋገጠች በሗላ ራሷን አጥፍታለች ሲል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ አስታውቋል።

@Addis_News