Get Mystery Box with random crypto!

የዩክሬን ወታደሮች ላይ ኪሳራ ደርሷል ሲሉ ፑቲን ተናገሩ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የ | አዲስ ነገር መረጃ

የዩክሬን ወታደሮች ላይ ኪሳራ ደርሷል ሲሉ ፑቲን ተናገሩ


የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የዩክሬን ወታደሮች ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ መጀመራቸውን እና የሞስኮን የመከላከያ መስመሮችን በጡጫ ለመምታት ባደረጉት ጥረት "ከፍተኛ" ኪሳራ እየደረሰባቸው መሆኑን ተናግረዋል ። የዩክሬን ጦር ስልታዊ መንገድን በመጠቀም ጥቃቱም ጀምሯል ማለት እንችላለን ሲሉ ፑቲን በሶቺ ውስጥ በዩራሺዢያን ኢኮኖሚ ህብረት ውስጥ ከሌሎች መሪዎች ጋር የነበራቸውን ቆይታ ተከትሎ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ኪየቭ ዘመቻውን ትጀምር እንጂ የዩክሬን ወታደሮች በትግል ሜዳ የተሰጣቸውን ተግባራን አላሳኩም ሲሉ አክለዋል ። "ይህ ደግሞ የዩክሬን አገዛዝ ወታደሮች ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰባቸው መሆኑን እያየን ነው" ያሉት ፑቲን "አጥቂው ወገን 3 ለ 1 ኪሳራ እንደሚደርስበት ይታወቃል" ሲሉ ጠቁመዋል።

ከጦር ግንባር ምንም አይነት ገለልተኛ ዘገባ ባይኖር የኪየቭ ወታደራዊ እንቅስቃሴ መኖሩ በዚህ ወገን ደግሞ ፑቲን ድል ነስተናል ማለታቸው በስፋት እየተደጠ ይገኛል። ዩክሬን የሩሲያ ወታደሮችን ከግዛቷ ለማስወጣት በምታደርገው ጥረት የሩሲያ መከላከያን እየጣሰች ስለመሆኑ ለመገምገም አልተቻለም። በምስራቅ ዩክሬን ከሩሲያ ጦር ጋር በተለያዩ ግንባሮች ጦርነቱ መጨመሩን ወታደራዊ ተንታኞች እና የዩክሬን ምንጮች ገልፀዋል።

የጦርነት ዘመቻው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሄዱን ተንታኞች ቢገልጹም የዩክሬን ባለስልጣናት የመልሶ ማጥቃት መጀመሩን ክደዋል ወይም ለማረጋገጥ አልፈለጉም። የአገሪቱ ደቡብ ምስራቃዊ ክፍሎች ግን በጥይት ድምፅ እየተናጡ ይገኛል።

በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የጦርነት ጥናት ኢንስቲትዩት አርብ ዕለት እንዳስታወቀው “የተለያዩ ጠቋሚ ምልክቶች መኖራቸውን” የዩክሬን የመልሶ ማጥቃት መጀመሩን እና የዘመቻው የመጀመሪያ ደረጃም የዩክሬን ኪሳራ እንደሚያሳይ ገልጿል።በጦር ግንባር የሩስያ ኃይሎችን ለመከላከል ጥረት ሲደረግ ማስተዋል ተችሏል ሲል ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል።

#ዳጉ_ጆርናል

@Addis_News
@Addis_News