Get Mystery Box with random crypto!

ቱርክ ወደ አፍሪካ ሀገራት ሊዘዋወር የነበረ 1 ቢሊየን ዶላር ሀሰተኛ የገንዘብ ኖት በቁጥጥር ስር | አዲስ ነገር መረጃ

ቱርክ ወደ አፍሪካ ሀገራት ሊዘዋወር የነበረ 1 ቢሊየን ዶላር ሀሰተኛ የገንዘብ ኖት በቁጥጥር ስር አዋለች
ከዚሁ ድርጊት ጋር በተያያዘ አንድ ጋናዊ እና ሶስት ስዊድናውያንን ጨምሮ ስድስት ግለሰቦችን መያዛቸውንም ነው የኢስታንቡል ከተማ አስተዳደር ያስታወቀው።

ተመሳስለው የተሰሩት የ100 ዶላር ኖቶቹ ወደ አፍሪካ ሀገራት ሊላኩ እንደነበርና በተጠርጣሪዎቹ ቤት በተደረገ ፍተሻም ከፍተኛ መጠን ያለው ሀሰተኛ ገንዘብና ውድ ጌጣጌጦች መገኘታቸው ተገልጿል።

ጉዳዩን የስዊድን እና ጋና ቆንስላዎች እንዲያውቁት መደረጉን ቱርክ አስታውቃለች።

ተጠርጣሪዎቹ ተመሳስሎ የተሰራውን 1 ቢሊየን ዶላር ወደየትኞቹ የአፍሪካ ሀገራት ሊልኩት እንደነበር አልተገለጸም።
በኢስታንቡል ትናንት የተያዘው ሀሰተኛ ገንዘብ በቱርክ ታሪክ ከፍተኛው ነው ተብሏል።
Alain

@Addis_News
@Addis_News