Get Mystery Box with random crypto!

ከአውሮፕላን አደጋ ተርፈው ለ40 ቀናት የአማዞን ጫካ ውስጥ የቆዩ አራት ህጻናት በህይወት ተገኙ | አዲስ ነገር መረጃ

ከአውሮፕላን አደጋ ተርፈው ለ40 ቀናት የአማዞን ጫካ ውስጥ የቆዩ አራት ህጻናት በህይወት ተገኙ

በኮሎምቢያ ከአውሮፕላን አደጋ ተርፈው ለሳምንታት የአማዞን ጫካ ውስጥ የቆዩ አራት ህጻናት በህይወት ተገኙ።

ባለፈው ግንቦት መጀመሪያ ህጻናቱን፣ እናታቸውን እና ሁለት አብራሪዎችን የያዘችው ቀላል አውሮፕላን ጫካ ውስጥ በመከስከሷ የልጆቹ እናት እና ሁለቱ አብራሪዎቹ ህይወታቸው አልፏል። ይህን ተከትሎም የጠፉትን ህጻናት ለመታደግ በርካታ ወታደሮች እና የአካባቢው ሰዎች የተሳተፉበት የማዳን ዘመቻ ሲደረግ ነበር። ልጆቹ እና እናታቸው ሲጓዙበት የነበረው ‘ሴሴና 206’ አውሮፕላን ከአራራኩዋራ ወደ ሳን ሆሴ ዴል ጉዋቪያር በመብረር ላይ ሳለም በሞተር ብልሽት ሳቢያ እንደተከሰከሰ ተገልጿል።

በአደጋው ህይወታቸውን ያጡት የሦስቱ ሰዎች አስከሬን አደጋው በደረሰበት ቦታ በሠራዊቱ የተገኘ ቢሆንም ልጆቹ ከአደጋው ተርፈው እርዳታ ለማግኘት ጫካውን ማሰስ በመጀመራቸው ሊገኙ አልቻሉም ነበር። ህፃናቱ “ሁይቶ” የተባለ ማህበረሰብ ተወላጅ ሲሆኑ፤ ስለ ፍራፍሬ እና የጫካ ኑሮ እውቀት ያላቸው ስለሆኑ በህይወት የመቆየት እድል እንደሚሰጣቸው ተስፋ ተደርጎ ነበር።

የኮሎምቢያው ፕሬዝዳንት ጉስታቮ ፔትሮ የህጻናቱ በህይወት መገኘት አስደናቂ ነው፤ በታሪክ ሲታወሱ የሚኖሩ የጀግንነት እና የጽናት ምሳሌ ይሆናሉ ብለዋል። በኮሎምቢያ የመከላከያ ሚኒስቴር የተሰራጨው ቪዲዮ ህፃናቱ ከጫካው ረጃጅም ዛፎች ላይ በሄሊኮፕተር ሲወሰዱ አሳይቷል። በህይወት የተገኙት ህጻናት በኮሎምቢያ ዋና ከተማ በሚገኝ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሆነም ቢቢሲ ዘግቧል።(ቢቢሲ፣ኢቢሲ)

@Addis_News
@Addis_News