Get Mystery Box with random crypto!

በቴዲ አፍሮ የህይወት ጉዞ ላይ የሚያውጠነጥን አዲስ መጽሐፍ ለገበያ ሊበቃ ነው በክቡር ዶ/ር አ | አዲስ ነገር መረጃ

በቴዲ አፍሮ የህይወት ጉዞ ላይ የሚያውጠነጥን አዲስ መጽሐፍ ለገበያ ሊበቃ ነው

በክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ የህይወት ጉዞ ላይ የሚያውጠነጥን "ቴዎድሮስ እስኪነግሥ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ከሀምሌ 20/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለአንባቢያን ይቀርባል ተብሏል።

መጽሐፉ በዘላለም ሙሉ የተፃፈ ሲሆን የፊታችን ረቡዕ ለገበያ እንደሚቀርብ ነው የተነገረው።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ #ልክ_በዛሬዋ_እለት ዝግጅታችን የብላቴናው ልደት ዛሬ መሆኑን እናንሳ። ክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ ልክ በዛሬዋ እለት ሐምሌ 7 1968 አ.ም ነበር በአዲስ አበባ የተወለደው።

ዛሬ 46ተኛ የልደት በአሉን እያከበረ ሲሆን አድናቂዎቹም በያመቱ ለሱ ያላቸውን ክብርና ፍቅር ለመግለጽ ቀኑን ደም በመለገስና በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ በመሳተፍ ያከብሩታል።

@Addis_News
@Addis_News