Get Mystery Box with random crypto!

'የህዝብ አመኔታን መቼም ቢሆን አንዘነጋም፤ ክብራችን ህዝብን በፍትሃዊነት ማገልገል ስለሆነ' :- | አዲስ ነገር መረጃ

"የህዝብ አመኔታን መቼም ቢሆን አንዘነጋም፤ ክብራችን ህዝብን በፍትሃዊነት ማገልገል ስለሆነ" :- ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

ሌቦችና እምነታቸውን ሸጠው የሚበሉ ሁሉ ለጊዜው ቢታግሉንም አያሸንፉንም፤ እውነት ምንግዜም ታሸንፋለች!!
ከሁሉም በላይ ፈጣሪ ረድቶን የህዝብን ሀብት በቴክኖሎጂ ዉንብድና ከመዘረፍ ማዳን ችለናል ።

የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ አወጣጥ ስራ ላይ አጠራጣሪ ጉዳዮች ከገጠሙ ጊዜ አንስቶ በማጣራት ሂደት ለደገፋችሁን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ፣ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ የኢኖቨሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርንና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትን ከልብ ላመሰግን እወዳለሁ።

@Addis_News
@Addis_News