Get Mystery Box with random crypto!

አዳብና መልቲ ሚዲያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ adabnamidea — አዳብና መልቲ ሚዲያ
የቴሌግራም ቻናል አርማ adabnamidea — አዳብና መልቲ ሚዲያ
የሰርጥ አድራሻ: @adabnamidea
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 817

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1

የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-12-16 11:35:10
ገረ ምሩ

ከመስፍን ሲማ በቅርብ ቀን
332 views08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-16 11:28:52 ኃላፊነቴን አስረክቤያለው
**

በአዳብና በክስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማህበር ውስጥበ ፕሬዝዳትነት የነበረኝን የመሪነት ኃላፊነት አስረክቤያለው።

እንደሚታወቀው የአዳብና በክስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማህበር ህጋዊ ሆኖ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ማህበሩን በፕሬዝዳንትነት ለአንድ ዓመት ተኩል ስመራና ሳገለግል ቆይቻለው።በአንድ ዓመት ተኩል ጉዞችንም ከማህበሩ ስራ አስፈፃሚና አስተባባሪዎች እንዲሁም ከየአካባቢው ወጣቶች ጋር በመሆን ማህበሩ ለተነሳለት ዓላማ ደፋ ቀና ስንል ቆይተናል።በዚህም በአካባቢያችን ላይ አመርቂ ስራዎች ሰርተናል ብዬ በኩራት መናገር እችላለው።

ይሄን ማህበር በመምራት ከወንድም እህቶቼ ጋር የዚህ ታሪክና ስራ ተሳታፊ በመሆኔ ትልቅ ኩራትና ደስታ ይሰማኛል።እንደግልም ለማህበረሰቤ ያለኝን ዓላማ አሳክቻለው ብዬ አስባለው።ዛሬ ብዙ የክስታኔ ተወላጅ ወጣቶች ለባህላቸውና ለአካባቢያቸው በቁጭት ተነስተዋል።ማህበራችንም በአስተማማኝና በጠንካራ ሁኔታ ላይ ይገኛል።በማህበራችንም ውስጥ ማህበሩን ሊመሩ የሚችሉና ወደፊት ሊያስቀጥሉ የሚችሉ ብዙ ጠንካራና ባለራህይ ወጣቶች አሉ።

በመሆኑም እኔ ካለብኝ የኃላፊነት መደራረብና ጫና አንፃርና እንዲሁም ተተኪ አመራሮች ወደፊት እንዲመጡ ካለኝ ፍላጎት የተነሳ ምንም እንኳ ኃላፊነቴን ለማስረከብ ገና ሁለት ዓመት ተኩል ቢቀረኝም(በማህበሩ ህግ መሰረት የፕሬዝዳንቱ የስልጣን ዘመን 4 ዓመት በመሆኑ) በገዛ ፍቃዴ ኃላፊነቴ ለማስረከብ ወድጃለው።

የማህበራችን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከሁለተኛው የአዳብና ፌስቲቫል በኋላ በተደጋጋሚ ኃላፊነቴን ለማስረከብ ያቀረብኩለትን ጥያቄ ቢዘገይም ተቀብሎኛል።በመሆኑም ለውድ የማህበራችን አባላት፣እጅግ ለምወድው ለክስታኔ ማህበረሰብና በጠቅላላ ለጉራጌ ህዝብ ኃላፊነቴን ማስረከቤን ለማሳወቅ እወዳለው።

የማህበራችን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በአጭር ጊዜ የአመራር ሽግሽግ በማድረግ ቀጣይ ማህበሩን የሚመራ የማህበሩ ፕሬዝዳንት ለማህበሩ አባላትና ለህዝብ ያስታውቃል።እኔም በተለያየ መንገድ ማህበሩን የማግዝና በማንኛው ጊዜ ከማህበሩ ጎን የምሆን ይሆናል።

የዚህ ማህበር ሀሳብና ማህበሩ መምራት ከጀመርኩበት ጊዜ ጀምሮ የማህበሩ ዓላማና ይሳካ ዘንድ ከጎኔ በመሆን ያገዛቹኝና ያበረታታቹኝ የማህበራችን አባላት በውጭ የምትገኙ የማህበሩ አባላትና ተወላጆች ድጋፍ ስታረጉልን ለነበራቹ የአካባቢያችን የመንግስት አመራሮችና ባለሀብቶች እንዲሁም ምሁራን እኔ ታናሽ ወንድማቹ ታላቅ ምስጋናን አቀርባለው።

ማህበራችን የአዳብና በክስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማህበር በቁርጠኛ የክስታኔ ልጆች እንደተለመደው ታላላቅ ስራዎችን እየሰራ ወደፊት መገስገሱን ይቀጥላል።

ክስታኔነት ያብብ ጉራጌነት ይለምልም!

ዘፀአት ቱቼ
የማህበሩ መስራችና ፕሬዝዳንት
323 views08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-15 17:19:30
470 views14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-15 17:19:18 ኃላፊነቴን አስረክቤያለው

457 views14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-14 19:43:00
ተወዳጁ አርቲስት ፈለቀ ማሩ ታህሳስ 15 ድንቅ የሆነው ሙዚቃ ክሊፑ በዮድ አቢሲኒያ የባህል ምግብ አዳራሽ ያስመርቃት።

በዕለቱ
የሙዚቃ ኮንሰርት
የእራት ግብዣ
ሌሎች አስደሳች ፕሮግራሞችም አሉ።

መግቢያ ትኬቱን የምትፈልጉ

0910186703
0966217000
ደውለው እንዲያዝሎት ይዘዙ።
256 viewsedited  16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 08:20:29 "ሀገር ሳትረጋጋ አርሶ ማደር ተኝቶ ማደር የለምና ሀገሬን አረጋግቼ እመለሳለው።"
ለሀገሩ ብሎ ህይወቱን የሰዋው የጀግናው ወታደር ወንድሙ አቢሹ ነበራ ቃል ነበር።

ወንድሙ አቢሹ ነበራ በሀራችን የሰሜኑ ክፍል 2013ዓ.ም ላይ ጦርነት ሲነሳ መንግስት ባቀረበው ጥሪ መሰረት ለሀገሩ ባለው ልዩ ፍቅርና ወኔ በራሱ ፍቃድ በወዶ ዘማችነት ሪፌንሶ ቀበሌ በመወከልና ሶዶ ወረዳ ሚሊሻ ፅ/ቤት ሄዶ በመመዝገብ ጦላይ ወታደር ማሰልጠኛ ተቋም በመሰልጠን ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2015 ዓ.ም ሀገሩን ለማረጋጋት በተለያዩ ግንባሮች ሲዋጋ ቆይቷል።ወንድሙ አቢሹ ነበራ በደሴ ግንባር በነበረ አውጊያ ቆስሎ ወደ አላጌ ሆስፒታ ገብቶ የነበረና አባትና እናቱ ቦታው ድረስ በመሄድ "እባክ ልጃችን ይሄን ያህል ለሀገር ለፍተሃል አሁን በቃ ተመለስ" ቢሉትም የወንድሙ አቢሹ ነበራ መልስ ግን" ለምን ወጣውና ለምን እመለሳለው? የወጣሁት ሀገሬን ላረጋጋ ነው።ሀገሬ ሳትረጋጋ ወደ ግንባር እንጂ ወደ ኋላ አልልም።እንደ ወንድ ወጥቼ ጦርነቱ ሳያልቅ እንደሴት አልመለስም። የምመለሰው ይሄ ጦርነት ሲያልቅና ሀገራችን እፎይ ስትል ብቻ ነው።"የሚል ነበር ።

ከዚያም ወንድሙ አቢሹ ከቁስለቱ ከአገገመ በኋላ በድጋሚ በተለያዩ አውደ ውጊያዎች ሲፋለም ቆይቶ በአላማጣና ኮረም በነበረ አውዲ ውጊያ ጥቅምት 21/2015 ዓ.ም በጠላት በኩል በተኮሰ ከባድ መሳሪያ ለውድ ሀገሩ በ27 ዓመቱ ህይወቱን ተሰውቷል።
የለቅሶ ስነ-ስርዓቱም ህዳር 27 በትውልድ መንደሩ በሪፌንሶ ኪቦ ቤተሰብ፣ወዳጅ ዘመዶቹና ጓደኞቹ በተገኙበት የጀግና አሸናኘት ተደርጎለታል።

ውዱ የክስቶ ልጅ ውዱ የሪፌንሶ ልጅ
የሙሌ አበባ
ቀረ እንደወጣ
አንጀታችን ባባ
ወገቡን በዝናር እጁን በጎራዶ በእሳት የነከረ
ሞት አይቀርም ብሎ በልቡ የመከረ
በሀገር ፍቅር ወኔ ልቡ የሰከረ
ማን አለ እንደ ወንዴ ለሀገሩ ብሎ ልብሱን የገበረ
ለወገኑ ብሎ ህይወቱን የሰዋ
ለሀገር መሞት ለጀና ጌቱ ነውና
ሲዘከር ይኖራል ሁሌ እንደፅዋ
163 views05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 08:20:27
158 views05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 21:30:33
#ውሳቻ ፡
/እንሠትን በደቦ መፋቅ/
*******
የጉራጌ ማህበረሰብ እንደሌሎቹ የሀገራችን ብሄር ብሄረሰቦች የራሱ የሆኑ የተለያዩ ባህላዊ እሴት ባለቤት ነው:: እነዚህ ባህላዊ እሴቶች በማህበረሰቡ የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ሲከወኑ ይስተዋላል፡፡ከነዚህ የእርስ በርስ የመደጋገፍና የመረዳዳት ባህልን ከሚያዳብሩ ባህላዊ እሴት አንዱ #ውሳቻ ተጠቃሽ ነው:: ውሳቻ የቃሉ ቀጥተኛ ትርጉም የእንሰት
አዝመራ ወይም የእንሰት ምርቶች የሚሰበሰብበት ወቅት ሲሆን የጉራጌ እናቶች በየአካባቢያቸው አንድ ላይ ሆነው እንሰት የሚፍቁበት የደቦ ስርአት #ውሳቻ ተብሎ ይጠራል:: ውሳቻ የሚጀምረው በብሄረሰቡ የዘመን አቆጣጠር መሸ ወይም ጥቅምት አጋማሽ ጀምሮ እስከ ታህሳስ መጨረሻ
ድረስ ባለው ነው፡: ይህ ሲባል ሁሉም አካባቢ በተመሳሳይ ወቅት ይጀምራል ለማለት አያስችልም ለምሳሌ የደጋማ አካባቢ ከወይና ደጋ አካባቢዎች አስቀድመው እንደ ሚጀምሩ የማህበረሰቡ እናቶች ያስረዳሉ :: #ውሳቻ ከሌሎች ለየት የሚያደረገው አቅም የሌላቸው እናቶች መስራት አትችሉም
ተብለው ማግለል ሳይሆን የቻሉትን ያሕል ተሳታፊ ሆነው የእንሰት ምርታቸውን መሰብሰብ መቻላቸውና አቅመ ደካሞችን የነፃ ጉልበት ዕርዳታ ማድረጋቸው ውሳቻን ልዩ ያደርገዋል እንዲሁም በአካባቢ ለቅሶ ከተከሰተ የለቀስተኛው ቤት አንድ ዙር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመስጠት የእንሰት ምርት እንዲሰበሰብ ይደረጋል እንዲሁም ሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች ሲገጥሙ የመረዳዳት ባህላዊ እሴቶች ጎልቶ ይታያል። ይህ ውብ ባህላዊ እሴት በእናቶች ሲከወን የተለያዩ ባህላዊ ጨዋታዎች ይዜማሉ ከነዚህም ውስጥ ዋይ ወቶ እና   ሌሎችም ባህለዊ ዜማዎች ያዜማሉ፡፡

ባህላችን ለዓለም እናሰተዋውቅ!
ቅርሶቻችን በአንድነት እንጠብቅ!
241 views18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 10:58:41
አርቲስት ፈለቀ ማሩ አዲስ በሆነና ከፍ ባለ የሰርግ ስራ እየመጣ ነው
****
ስራው የክስታኔን የሰርግ ስርዓት እጅግ በጣም ጥንቃቄ በተሞላበትና ጥራት ባለው ሁኔታ ከቸግ እስከ እንሾሽላና ሰርግ ድርስ በግሩም ግጥም፣ኩልል ባለ ዜማ፣ ከፍተኛ ጥራት ባለው ቀረፃና ዳይሬክቲንግ ፍንትው አድርጎ ያሳየናል።
ለእያንዳንዱ ትህይንት የተደረገው ጥንቃቄና ትኩረት እጅግ ግሩም ነው።ክሊፑ ብዙ እንደተለፋበት ያሳያል።የክስታኔን በአጠቃላይ የጉራጌን የሙዚቃ ኢንዱስትሪ አንድ እርምጃ ከፍ ያደርገዋል ብዬ እጠብቃለው።

ፈሌን ከዚህ በፊት ይሄን ስራ ልሰራ ነው ብሎ ሲያማክረኝ አንድ ነገር ወቅሼው ነበር።የጉራጌ ሙዚቀኞች (በተለይ የክስታኔ አካባቢ) ትልቅ ሀሳብ፣ጥሩ ዜማ፣ጥሩ ግጥም ታነሱና የሚዚቃው ክሊፕ ላይ ግን ብዙ ክፍተት አያለው።
ይሄንን ክፍተት የሚደፍንና ለሌሎችም ጀማሪ አርቲስቶች ትምህርት የሚሆን ስራ ሰርተ እንደምታሳየን አምናለው ብዬው ነበር።
ፈሌ ዛሬ እጅግ በጣም ከምጠብቀው እስታንዳርድ በላይ በከፍተኛ ጥራትና ጥንቃቄ የሰራው ሙዚቃ ክሊፕ አግኝቶ አሳይቶኛል።በስራው እጅግ በጣም ኮርቻለው።በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍ ብሎ እንሚታይና እንደሚደመጥ ጥርጥር የለኝም።

እንግዲ እኛም ብዙ ወጪ አውጥተው እንዲ ለፍተው የሚሰሩና ባህላችን እያስተዋወቁልን ያሉ አርቲስቶቻችን በማበረታታት፣ስራዎቻቸው በማስተዋወቅ፣ዝግጅቶቻቸው ላይ በመሳተፍ እናግዛቸው።

ዘፀአት ዘጌ ገቾ
365 views07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-04 10:50:05
በቡድን በቪዲዮ ዪምር ዪምር የማሳየት ዘርፍ ተወዳዳሪዎች አጭር ማብራሪያ
*
ለውድድሩ መዝገባ የምናከናውነው እስከ ህዳር 30 ብቻ ነው።
ቪዲዮ የምንረከበው እስከ ታህሳስ 15 ብቻ ነው
ገለልተኛ ግልፅ በሆኑ መስፈርቶች ፕሮፌሽናልና ታዋቂ በሆኑ ሰዎች ይዳኛል። 30% በማህበራዊ ማዲያ በህዝብ ይዳኛል።
በማንኛውም ቦታ(ከሀገር ውጪም ሀገር ውስጥም) ሆናቹ ቪዲዮ በመላክ ብቻ መወዳደር ትችላላቹ።አሜሪካ፣አውሮፓ ሀረብ ሀገራት ያላቹ በዚህ ውድድር እንድታተፉ ትበረታታላቹ።
ውድድሩ ከ30%እድሜ በታች የሆኑና ከ8ዓመት ጀምሮ ያሉ ታዳጊዎችን ጭምር ያካትታል።ከ13 ዓመት በታች ያሉ ወንድ ታዲዎችም ማካተት ይቻላል።
የዪምር ትክክለኛና ሙሉ ስነስርዓት ማሳየት ይጠበቅባችዋል
ለዪምር የሚያስፈልጉ ግብሃቶች ማሟላት(ወንፊት፣አንጮት፣ገንቦ፣ጣሳቆሎ፣ጠላ፣) ማሟላት ተመራጭ ያደርጋል።
በተቻለ መጠን የአካባቢው አልባሳትና ጌጣጌጥ መጠቀም ተመራጭ ያደርጋል
ባህሉን ጥበባዊና ድራማዊ በሆነ መልኩ እንዲሁም ከባህሉ ጋር የተያያዘ ተጨማሪ እሴት መጨመር ተመራጭ ያደርጋል።
በጥሩ ቪዲዮ ካሜራ ወይም ጥራት ባለው የስልክ ካሜራ ስለቀረፃ እውቀት ባለው ሰው ሊቀረፅ ይችላል።አቀራረፁና ጥራቱ ከውድድሩ መስፈርቶች አንዱ ስለሆነ ጥንቃቄ ያስፈልጋል።
አዲስ አበባና ሀገርቤት ላላቹ የቡድን ተወዳዳሪዎች ቀረፃው በእኛ በኩል ልናከናውንላቹ እንችላለን።

ቡድን መመስረት የሚያስችል የሰው ብዛት ወይም ብቸኛ የሆናቸው ሌሎች ቡድኖች እንድትቀላቀሉ እድሉን እናመቻቻለን።
ስለዪምር ስለዪምር እውቀቱና መረጃ የሌላቹ በቪዲዮና በፅሁፍ መረጃው ከእኛ ማግኘት ትችላላቹ።እንዲሁም እንዴት መስራት እንዳለባቹ እናማክራለን።

የአዳብና በክስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማህበርና ተባባሪ አዘጋጆች
ለበለጠ መረጃ
ስልክ ቁጥር
0910186703
0910337765
459 views07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ