Get Mystery Box with random crypto!

#Update ' ተፈታኞች የቅሬታቸውን ምላሽ ከዛሬ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ማየት ይችላሉ ' - የት | Ac

#Update

" ተፈታኞች የቅሬታቸውን ምላሽ ከዛሬ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ማየት ይችላሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ነገ አርብ ጥር 26/2015 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት እንደሚያበቃ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

አገልግሎቱ ፤ ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረቢያው ቀን ነገ 11:30 እንደሚያበቃ አውቀው በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ አለን የሚሉትን ቅሬታ እንዲያቀርቡ መልዕክት አስተላልፏል።

በሌላ በኩል ፤ ቀድመው ቅሬታ ያቀረቡ ተፈታኞች የቅሬታቸውን መልስ www.neaea.gov.et:8081 ድረ ገጽ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን (Registration Number/ID) ብቻ በማስገባት ከዛሬ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ ቅሬታዎች ሁሉም ተጣርተው ሲጠናቀቁ በቀጣይ ቀናት የሚያሳውቅ መሆኑን ገልጾ የቅሬታ ምላሽ ያልደረሳቸው ተፈታኞች በትዕግስት እንዲትጠባበቁ አሳስቧል።

በተጨማሪ ባልተሟላ ወይም በተሳሳተ ወይም በሌላ ሰው መለያ ቁጥር ያመለከቱ የስም ዝርዝራቸው ዛሬ ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ከላይ በተጠቀሰው ድረ ገጽ አድራሻ ላይ እንደሚያሳውቅ የገለፀው አገልግሎቱ ተፈታኞች ቅሬታቸውን በድጋሚ በተስተካከለ መለያ ቁጥራቸው ማመልከት እንደሚችሉ ገልጿል።

tikvahethiopia

━━━━━━━━━━━━
Join & Share
    
@Aconcise
Contact & Ads
 
@Concise_bot
━━━━━━━━━━━━