Get Mystery Box with random crypto!

ኢንትራንስ አልፋችሁ ፤ፍሬሽማን የምትማሩ ልጆች የምትፈልጉትን ዲፓርትመንት ለመግባት ጠንከር ያለ ፉ | Ac

ኢንትራንስ አልፋችሁ ፤ፍሬሽማን የምትማሩ ልጆች የምትፈልጉትን ዲፓርትመንት ለመግባት ጠንከር ያለ ፉክክር ይገጥማችሗል።

ይህንን ታሳቢ በማድረግ ከአሁኑ የፍሬሽማን ትምህርትን ልዘጋጅ ላንብብ ብላችሁ የምታስቡ አላችሁ። መልካም ሀሳብ ነው ያሰባችሁት።

ነገር ግን ሁሉም ዩኒቨርሲቲ ተመሳሳይ ወይም አንድ አይነት የፍሬሽማን የመጀመሪያ ሴሚስተር ኮርስ አይሰጡም። ከግቢ ግቢ ይለያያል።

ለምሳሌ አዲስ አበባ ቢደርሳችህ ፥ ደብረ ማርቆስ ቢደርሳችሁ ፥ መደወላቡ ቢደርሳችሁ ፥ ባህርዳር ቢደርሳችሁ ወዘተ እነዚህ ግቢዎች የተለያየ የመጀመሪያ ሴሚስተር ፍሬሽማን ኮርስ ነው የሚሰጡት።

ስለዚህ ካሁኑ ንባብ ጀምራችሁ ፤ ቡሗላ ግቢ ስትመደቡ የተመደባችሁበት ግቢ ያነበባችሁትን ኮርስ first semester ላይ የማይሰጥ ከሆነ በባዶ መድከም ነው የሚሆነው።

በተጨማሪም አሁን አሁን ግቢዎች በ MoSHS የተዘጋጀውን የፍሬሽማን ሞጁሉ ላይ ማሻሻያ እያደረጉ የራሳቸውን ሞጁል እያዘጋጁ ነው።

ስለዚህ ግቢ ምደባ እስከሚደረግ ድረስ ኮመን የሆኑትን ኮርሶች ብታነቡ መልካም ነው። የ Natural Science ተማሪ ከሆናችሁ ፤ Maths, Physics እና Communicative English በየትኛወም ግቢ first semester ላይ ስለሚሰጡ እነሱን ከወዲሁ መዘጋጀት ትችላላችሁ። የ Social Science ተማሪዎች ግን ከ ግቢ ግቢ ይለያያል ዝብርቅርቅ ያለ ነው። ስለዚህ Communicative English ን ብቻ ብታነቡ የተሻለ ነው።

በተረፈ ወደፊት ለሚጠብቃችሁ ፉክክር ራሳችሁን ከወዲሁ በስነ-ልቦና አዘጋጁ።

Join and Share

https://t.me/FRESH_2015
https://t.me/FRESH_2015