Get Mystery Box with random crypto!

            FAQ በተደጋጋሚ ስለ Entrance Hub የሚጠየቁ ጥያቄዎች እና በቂ ምላ | Ac

            FAQ

በተደጋጋሚ ስለ Entrance Hub የሚጠየቁ ጥያቄዎች እና በቂ ምላሽ

1 ENTRANCE HUB ምንድነው?

2) ትምህርቱን እንዴት ያስተምራል?

3) ትምህርቱን እንዴት መከታተል እችላለሁ?

4) አንዴ ያለፈውን ትምህር እንዴት ማግኘት እችላለሁን ?

5) ምን ያህል ተዓማኒነት አለው?

6) ክፍያው በየወሩ ነው ወይስ አንዴ ብቻ ነው?

7) ሁል ጊዜ Online መገኘት አልችልም፣ ታዲያ እንዴት Entrance Hubን መጠቀም እችላለሁ?

8) ለ2015 ተፈታኞች ምን አቅዷል?

◇◇◇◇◇◇◇◇◇◇◇◇◇◇◇◇◇◇◇◇
       1➾ ENTRANCE HUB ምንድነው?

◉መልስ➔ ENTRANCE HUB በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነ ሙሉ ትኩረቱን በ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ለይ ያደረገ የማጠናከሪያ ትምህርት ማዕከል ነው።
Entrance Hub በሀሳብ ደረጃ ከ2013 ዓ/ም የነበረ ብሆንም ወደ ትግበራው በመግባት ለመጀመሪያ  ዙር  በ2014 ዓ/ም ከ500 በላይ ተፈታኞችን መዝግቦ የማጠናከሪያ ትምህርት ስሰጥ ቆይቷል።

2) ትምህርቱን እንዴት ያስተምራል?

መልስእንደምናውቀው በሀገራችን አብዛኞቹ የHighschool ተማሪዎች Smartphone ተጠቃሚዎች ብሆንም የInternet ተደራሽነት ውስን በመሆኑ በአንድ ግዜ  የራሳችንን platform ተግባራዊ  ማድረግ ለበርካታ ተማሪዎች ተደራሽ ለማድረግ እና ሁሉንም ያካተተ እንዲሆን በቂ የinternet  connection አስፈላጊ ሆኗል።
በግል Application ወይም በWebsite published በማድረግ ሙሉ ትምህቶቻችንን በተቀላጠፈ መልኩ ለማድረግ መጀመሪያ ከተማሪዎቹ ጋር ትውውቅ እንድኖር ለማድረግ እና እውቅና ለማግኘት ሁሉም ተማሪዎች የሚጠቀሙበትን ቀላል አማራጭ ተጠቅመን ትውውቅ ለማድረግ አስፈልጎናል፤ በዚህም በሀገራችን ከ90% ተማሪዎች የሚጠቀሙትን ቴሌግራምን ለመጠቀም ተገደድን። በዚህም  private የtelegram Channel በመክፈት ትምህርቶችን ቀላል እና  ምቹ ለማድረግ እንዲሁም አሳታፊ እንዲሆን እንደየትምህርት አይነት ባህርይ
➔በቂ ኖት እና አጋዥ መፅሐፍ ማቅረብ፣
➔በአማርኛ ፅሁፍ ማብራሪያ፣
➔በvideo  መብራሪያ ማቅረብ፣
➔በAudio መብራሪያ ማቅረብ፣
➔በtelegraph መብራሪያ በማቅረብ፣ በተቻለ መጠን ቀላል እና ግልፅ ለማድረግ ሞክረናል።
በዚህም መልኩ በ2014 ከ500 በላይ ተፈታኞችን ተቀብለን ሙሉበሙሉ ባይሆንም በቻልነው ሁሉ Tutorial ስንሰጥ ነበር።

በመጀመሪያ አመት ምን ያህል ስኬታማ ነበርን?

በ2014  እኛ ጋ ተመዝግበው ስከታተሉ ከነበሩ ተፈታኞች ውስጥ  70% ከ50% እና ከዚያ በላይ በማስመዝገብ በቀጥታ ወደዩኒቨርስቲ መግባት እንደቻሉ አሳውቀውናል
ተማሪ ተመስገን 636 ከmarv ትምህርት ቤት የአመቱን ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል።
ተማሪ ኤለሃም 457 በማስመዝገብ የአመቱን ማህበራዊ ሳይንስ ከፍተኛ አስመዝግባለች።


3) ትምህርቱን እንዴት መከታተል እችላለሁ?

መልስትምህርቱን ለመከታተል የEntrance Hub ቤተሰብ ከመሆን ውጭ ሌላ ምንም የተለያ ነገር የለውም።
ማንኛውም telegram Application ያለው ሰው እና የtelegram ተጠቃሚ የሆነ ሰው መከታተል ይችላል።
ለመከታተል በመጀመሪያ መመዝገብ ያስፈልጋል፣
በትክክል ስትመዘጋቡ ትምህርቱ የሚሰጥበት ቻናል link ይደርሳል፣ ያንን link Join በማድረግ ብቻ መከታተል ትችላላችሁ።

ያልተመዘገበ ሰው በምንም መልኩ መከታተል አይችልም!

4) አንዴ ያለፈውን ትምህር እንዴት ማግኘት እችላለሁን ?

መልስከላይ  እንደተገለጸው  ትምህርቶቹ የሚቀርቡት በቀጥታ ስርጭት ስላልሆነ አንዴ የቀረበውን ትምህርት እስከፈተናው ቀን ድረስ እዛው ቻናል ውስጥ ስለምኖር በፈለጋችሁት ሰዓት እና ቦታ ማግኘት እና ማንበብ ትችላላችሁ።

5) ምን ያህል ተዓማኒነት አለው?

◉መልስ➔ ይህ አሁን ለEntrance Hub  የሚቀርብ ጥያቄ ከመሆን አልፏል።
ምክንያቱ Entrance Hub አዲስ የተጀመረ አይደለም፤ከዚህ በፊት በ2014 እና በ2015 ዓ/ም ከጥቅምት ጀምሮ በርካታ ተማሪዎች እየተጠቀመበት ያለ ተቋም ነው።
በምንም እና በማንኛውም መልኩ የተማሪዎችን ብር ያለአግባብ አንቀበልም።
ከተቀመጠው የክፍያ ገደብ ጨምሮም ይሁን ቀንሶ ያስገባ ተማሪ ከላ ብሩን ወዲያውኑ ተመላሽ የምናደርግ ይሆናል።
እንዲሁም ተማሪዎች ገብተው አይተው በገቡበት 3 ቀን ውስጥ ተመልሰው መውጣት ከፈለጉ ብራቸውን በሙሉ ተመላሽ እናደርጋለን፣ ከ3 ቀን በላይ ከሆነ ግን ተመላሽ አይሆንም።


6) ክፍያው በየወሩ ነው ወይስ አንዴ ብቻ ነው?

መልስክፊያው በየወሩ ሳይሆን አንዴ ብቻ ለምዝገባ ስሆን የ2015 መመዝገቢያ ዋጋ 150 ብር ብቻ መሆኑን እንገልፃለን።
ከ150 ብር መቀነስም መጨመርም አይቻልም።
ማንኛውም ተማሪ አንዴ 150 ብር ከፍሎ ከገባ በድጋሚ ብር አንጠይቅም!!

7) ሁል ጊዜ Online መገኘት አልችልም፣ ታዲያ እንዴት Entrance Hubን መጠቀም እችላለሁ?

ሁሉጊዜ online መገኘት ግዴታ  አይደለም!
ነገር ግን ፈተና በምሆንበት ሰዓት የተወሰነ ስለሆነ በዚያ ሰዓት መገኘት አለባችሁ።
በተከታታይ 2 ሳምንት ውስጥ አንድም ቀን በፈተና ተሳትፎ ያላደረገ ተማሪ  ያልተገኘበትን ምክንያትን ለAdmin  ማቅረብ ይኖርበታል።
በ2015 በሁለት ዙር ትምህርት ለመስጠት አቅደን የመጀመሪያው ዙር ከጥቅምት 28 ጀምሮ እየተሰጠ ስሆን የሁለተኛ አሁን ተጀምሯል።
በዚህ አመት በአጠቃላይ በሁለት መልኩ ትምህርትን እየሰጠን እንገኛለን
1➔ መፅሐፍን መሠረት ያደረገ ትምህርት
2➔ ጥያቄን መሠረት ያደረገ ትምህርት
ግልጽ ለማድረግ ያህል መፅሐፍን መሠረት ያደረገ ትምህርት ማለት ከ9_12 ክፍል ያሉትን ዋሳኝ የሆኑ ምዕራፎችን በጥልቀት ማስተማር፣ እና ጥያቄዎችን መስራት ስሆን ሁለተኛው ወይም ጥያቄን መሠረት ያደረገ ትምህርት ነው።
ጥያቄ መሠረት ያደረገ ትምህርት ማለት የበርካታ አመታት ጥያቄዎችን በየምዕራፉ ተከፋፍለው ቀርበው እና እነዚያን ጥያቄዎች በምን አይነት መልኩ መስራት እንዳለብን፣ በየትኛው አመት ከባድ ጥያቄ እንደተጠየቅን እና ከየትኛው unit ብዙ ጥያቄ እንደምወጣ በጥንቀት መመርመር እና መስራት የዚህ አመት ሁለተኛው ተግባራችን ይሆናል።
የበርካታ አመታት ጥያቄዎችም በእጃችን ለይ አሉ
Chemistry ከ1981 ጀምሮ
maths ከ1990 ጀምሬ እና ሌሎች ከ1995 ጀምሮ ሁሉንም ከነመልሳቸው እና ከነማብራሪያ እያዘጋጀን እንገኛለን።
ሌላው በዚህ አመት ዋናው እቅዳችን
1K challenge  አንዱ ነው!!
1K Challenge ማለት በ2015 ብሄራዊ ፈተና  ተፈታኞች ውስጥ ብያንስ 1000 ተማሪዎችን ወደ ዩንቨርስቲ እንዲያልፉ ማድረግ የዚህ አመት ዋና እቅዳችን ነው።
እርስዎም ተፈታኝ ከሆኑ ወይም ተፈታኝ የሆነ ወዳጅ ከለ የ1K challenge አባል እንዲሆን ይጋብዙ


Entrance Hubን እንቀላቀል ይገብዙ
ወደ Entrance Hub ለመቀላቀል
@ENTRANCEHUBBOT
የበለጠ መረጃ ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ
@ENTRANCEHUBETHIOPIA
እኛን ለማግኘት
@Entrancehub_Admin
የክፍያ አማራጭ ለማግኘት
https://t.me/EntrancehubEthiopia/1046