Get Mystery Box with random crypto!

ከመወለድ አንስቶ የሚፈጠሩ የልብ ጤና እክሎች ከውልደት በፊት ሊታወቁ ይችላሉ ከእያንዳንዱ 100 | Acibadem Healthcare Services

ከመወለድ አንስቶ የሚፈጠሩ የልብ ጤና እክሎች ከውልደት በፊት ሊታወቁ ይችላሉ

ከእያንዳንዱ 100 በህይወት ከሚወለዱ ህጻናት ውስጥ በአማካይ 1 ልጅ ከማንኛውም የልብ ጤና እክል ጋር አብሮ ይወለዳል። በአጠቃላይ ከ200 የሚበልጡ ከውልደት አንስቶ የሚመጡ የልብ ጤና እክሎች ዓይነቶች አሉ፡፡ አንዳንዶቹ ቀላል ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ለሕይወት አስጊ ናቸው። ከሦስቱ አንዱ በህይወት የመጀመሪያዎቹ ቀናት ውስጥ ህክምና ወይም ቀዶ ጥገና ያስፈልገዋል፡፡ ቀደም ባሉት ጊዜያት ከባድ የልብ ችግር ያለበት ሕፃን በሕይወት ለመትረፍ አነስተኛ ዕድል ነበረው። በአሁኑ ጊዜ የተራቀቁ የሕክምና አማራጮች ከተጎዱት ህጻናት ከ 95% በላይ መደበኛ የልብ ተግባራትን ወደነበሩበት መመለስ ይችላሉ፡፡ በልጆች ልብ አሰራር ላይ ከበድ ያሉ ያልተለመዱ ችግሮች አፋጣኝ የህክምና እርዳታ ሊፈልጉ ይችላሉ፡፡ የልብ በሽታዎችን ቀደም ብሎ ለይቶ ማወቅ ለህልውና ወሳኝ የሆነው ከዚህ የተነሳ ነው ። ትክክለኛውን የምርመራ አይነት ለመወሰን የላቀ የቴክኖሎጂ መመርመሪያ መሳሪያዎች በአቺባደም ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ ነፃ የሕክምና ሁለተኛ አስተያየት ለማግኘት የግል መልዕክት ይላኩልን።