Get Mystery Box with random crypto!

Acibadem Healthcare Services

የቴሌግራም ቻናል አርማ acibadem_ethiopia — Acibadem Healthcare Services A
የቴሌግራም ቻናል አርማ acibadem_ethiopia — Acibadem Healthcare Services
የሰርጥ አድራሻ: @acibadem_ethiopia
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.27K
የሰርጥ መግለጫ

http://t.me/AcibademChatBot

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 10:26:17
ለልጆች የልብ ፈውስ - መላ አለን

ከለውዝ ፍሬ ብዙም ያልበለጠ መጠን ባለው ልብ ላይ የቀዶ ህክምና ማድረግ ቀላል ፈተና አይደለም። የሕፃናት የልብ ቀዶ ጥገና ሐኪሞች በትናንሽ አካላት ውስጥ ያሉ አነስተኛ ልቦችን ለፍጹምነት በቀረበ ትክክለኛነት እና የላቀ ትኩረት ለማከም ሲባል በልዩ ሁኔታ የሚሰለጥኑትም ለዚህ ነው፡፡ አቺባደም የህፃናት የልብ ማዕከል በቱርክ እና በክፍለ አህጉሩ በልጆች የልብ እና የልብ ቀዶ ህክምና ውስጥ በጣም ታዋቂ የሆኑ ልዩ ባለሙያተኞች መገኛ ነው፡፡ ሀኪሞቹ ከዓለም ዙሪያ ከ15,000 በላይ የሕፃናት የልብ ህመምተኞች ያከሙ እንደመሆናቸው በጣም በተወሳሰቡ ሁኔታዎች ላይ እንኳን ለጠቅላላው የልብ ጤና እክል የተለያዩ የምርመራ እና የሕክምና አማራጮችን መስጠት የሚያስችል የካበተ ልምድ አላቸው። ለዝርዝር መረጃ አግኙን!
 
163 views07:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 09:01:35
የተሟላ ህፃናት የልብ ቀዶ ህክምና - በአቺባደም

በየአመቱ ከ600 በላይ ቤተሰቦች ከአለም ዙሪያ ለልጆቻቸው አቺባደም የህፃናት የልብ ማዕከልን ይመርጣሉ። በአቺባደም አጠቃላይ የልብ ክብካቤ ህክምና ውስጥ የሚጠቃለሉ በሙያ ደረጃቸው የላቁ ሐኪሞች በዘመናዊ መሳሪያዎች ታግዘው ይሰራሉ፡፡ በልጆች ላይ አንዳንድ የልብ ጤና እክሎች ያለ ቀዶ ጥገና ሊታከሙ ይችላሉ፡፡ የህክምናውን ሂደት በጠበቀ መልኩ ወደ ደም ሥር በሚገባ ካቴተር በሚባል ቀጭን ቱቦ ወደ ልብ ውስጥ እንዲገባ ይደርጋል፡፡ ይህም ክፍት ቀዶ ጥገናን ያስቀራል፡፡ ለውስብስብ በሆኑ የውልደት እና አዲስ የልብ ቀዶ ጥገናዎች ልዩ ትኩረት ቢደረግም ቀዶ ጥገና በሚያስፈልግበት ጊዜ ሁሉም ዓይነት የሕፃናት የልብ ቀዶ ህክምናዎች በአቺባደም ውስጥ በመደበኛነት ይከናወናሉ፡፡ በቀዶ ህክምና እና ያለ ቀዶ ህክምና እንዲሁም በሌሎች ዘዴዎች የሚካሄዱ ህክምናዎች እንደ ታካሚው አይነት የሚወሰን ሲሆን የስኬት ምጣኔውም ከ95% በላይ ነው፡፡
556 views06:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 14:07:27
ቦድሩም - የገነት ማዕዘን እና የተከበረ የዕረፍት ጊዜ ማሳለፊያ

ቦድሩም በቱርክ ውስጥ እጅግ በጣም ተወዳጇ የቱሪስት መዳረሻ ነች። በሞቃታማ የአየር ጠባይ፣ በምሽት ገደብ የለሽ የህይወት እንቅስቃሴዎች እና አስደናቂ ባህር ያላት ቦድሩም ለበጋ ዕረፍት ወደር የማይገኝላት ቦታ ናት። ልዩ ትርኢቶች እና ኮንሰርቶች፣ በርካታ የውሃ ስፖርቶች እና ለወዳጅነት የቀረቡ ሰዎች እንዲሁም ማለቂያ የሌላቸው የመዝናኛ እንቅስቃሴዎች በቦድሩም ቆይታ ክረምቱን የማይረሳ ያደርጉታል። አቺባደም ቦድሩም ሆስፒታል እ.ኤ.አ በጁን 2012 ህሙማንን መቀበል ጀምሯል ። ሆስፒታሉ በሁሉም የህክምና ክፍሎቹ ውስጥ በግል የጤና መድህን ታግዞ ለሀገር ውስጥ እና ለአለም አቀፍ ቱሪስቶች የጤና እንክብካቤ አገልግሎት ይሰጣል ።
የቦድሩም ተፈጥሮን ማዕከል አድርጎ የተነደፈው ሆስፒታሉ ወደ 26,000 ሜትር ስኩዌር የሆነ ስፋት በሚሸፍን ቦታ 104 አልጋዎች እና 23 የከፍተኛ እንክብካቤ አልጋዎች ያሉት ሲሆን ይህም በአራስ ሕፃናት ከፍተኛ እንክብካቤ ክፍል ውስጥ 9 አልጋዎች፣ 4 የቀዶ ጥገና ልዩ አልጋዎች እና 10 የአደጋ ጊዜ ምልከታ አልጋዎች አሉት ። ማዕከሉ በተጨማሪም ለአደጋ ጊዜ ታካሚዎች የሄሊኮፕተር ማረፊያ ቦታ የተዘጋጀለት ነው፡፡ አቺባደም ቦድሩም ሆስፒታል ኦንኮሎጂ ማዕከል፣ የጡት ጤና ማዕከል፣ የመካንነት ህክምና ማዕከል፣ የምርመራ ክፍል፣ የራዲዮሎጂ ክፍል እና ኢንቫሲቭ ካርዲዮሎጂ ህክምና ክፍል አለው። የእረፍት ጊዜዎን ከአቺባደም ቦድሩም ሆስፒታል ጋር በተረጋጋ ሁኔታ ያሳልፉ!
693 views11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 08:31:01
የህጻናትን ልብ የማዳን ጥምረት

በዚህ ህክምና ውጤታማ ለመሆን ደረጃው የላቀ የቀዶ ጥገና ሐኪም በቂ አይደለም፡፡ ሁነኛ የሕፃናት የልብ ቀዶ ጥገና ሐኪም በዙሪያው በሁሉም ተዛማጅ የሕክምና ዘርፎች ውስጥ የሰለጠኑ ስፔሻሊስቶች ባለሙያዎች ቡድን ያስፈልገዋል፡፡በአቺባደም የህፃናት የልብ እንክብካቤ ቡድን ውስጥ በልጆች የልብ ህክምና፣ በልጆች የልብና የደም ህክምና ቀዶ ጥገና፣ ማደንዘዣ እና ከፍተኛ እንክብካቤ፣ የልብ ኢሜጂንግ እና ራዲዮሎጂ፣ ኒዮናቶሎጂ እና ማገገሚያ ሂደቶች ውስጥ ልምድ ያላቸው ዶክተሮችን ያካትታል፡፡ እነዚህ ሀኪሞቻችን የሁሉም ህጻናት የልብ ታካሚዎቻችንን ልዩ አካላዊ እና ስሜታዊ ፍላጎቶች በተሻለ ለመረዳት ለዓመታት ጥረቶች አድርገዋል። በአቺባደም ሁሉም አማራጮች ታሳቢ እንደሚደረጉ እና ልጅዎ ደህንነታቸው በሚያስተማምኑ እጆች ውስጥ እንዳለ ማወቁ የአእምሮ ሰላም ይሰጣል።
892 views05:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 08:02:04
ከመወለድ አንስቶ የሚፈጠሩ የልብ ጤና እክሎች ከውልደት በፊት ሊታወቁ ይችላሉ

ከእያንዳንዱ 100 በህይወት ከሚወለዱ ህጻናት ውስጥ በአማካይ 1 ልጅ ከማንኛውም የልብ ጤና እክል ጋር አብሮ ይወለዳል። በአጠቃላይ ከ200 የሚበልጡ ከውልደት አንስቶ የሚመጡ የልብ ጤና እክሎች ዓይነቶች አሉ፡፡ አንዳንዶቹ ቀላል ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ለሕይወት አስጊ ናቸው። ከሦስቱ አንዱ በህይወት የመጀመሪያዎቹ ቀናት ውስጥ ህክምና ወይም ቀዶ ጥገና ያስፈልገዋል፡፡ ቀደም ባሉት ጊዜያት ከባድ የልብ ችግር ያለበት ሕፃን በሕይወት ለመትረፍ አነስተኛ ዕድል ነበረው። በአሁኑ ጊዜ የተራቀቁ የሕክምና አማራጮች ከተጎዱት ህጻናት ከ 95% በላይ መደበኛ የልብ ተግባራትን ወደነበሩበት መመለስ ይችላሉ፡፡ በልጆች ልብ አሰራር ላይ ከበድ ያሉ ያልተለመዱ ችግሮች አፋጣኝ የህክምና እርዳታ ሊፈልጉ ይችላሉ፡፡ የልብ በሽታዎችን ቀደም ብሎ ለይቶ ማወቅ ለህልውና ወሳኝ የሆነው ከዚህ የተነሳ ነው ። ትክክለኛውን የምርመራ አይነት ለመወሰን የላቀ የቴክኖሎጂ መመርመሪያ መሳሪያዎች በአቺባደም ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ ነፃ የሕክምና ሁለተኛ አስተያየት ለማግኘት የግል መልዕክት ይላኩልን።
950 views05:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 08:00:31
አቺባደም ታክሲም - የመሃል ከተማው ሆስፒታል
አቺባደም ታክሲም ሆስፒታል በጥቅምት 2015 የተከፈተ የአቺባደም ኸልዝኬር ግሩፕ 18ኛው ሆስፒታል ነው። በ24000 ካሬ ሜትር ገደማ በሆነ ቦታ ላይ እንደ አጠቃላይ ሆስፒታል ተዋቅሯል። ሆስፒታሉ 93 አልጋዎች እና 6 የቀዶ ጥገና ክፍሎች አሉት። አጠቃላይ የፅኑ እንክብካቤው ክፍል 10 አልጋዎች ያሉት ሲሆን በኒዮናታል ከፍተኛ እንክብካቤ ክፍል ለይቶ ማቆያውን ክፍል ጨምሮ 7 አልጋዎች ይዟል። የአቺባደም ታክሲም ሆስፒታል በውስጡ አጠቃላይ የቀዶ ጥገና፣ የውበት፣ የፕላስቲክ እና የመልሶ ግንባታ ቀዶ ጥገና፣ የማህፀን ህክምና እና የጽንስና ህክምና፣ የነርቭ ቀዶ ጥገና፣ የአጥንት ህክምና እና ትራውማቶሎጂ፣ የዓይን ህክምና፣ ኦቶርሂኖላሪንጆሎጂ እና ዩሮሎጂን የመሳሰሉ ህክምናዎችን ያጠቃልላል። የወሊድ፣ የቅድመ ወሊድ እንክብካቤ እና የድህረ ወሊድ የምክር አገልግሎቶች በአቺባደም ታክሲም ሆስፒታል ይገኛሉ። የታክሲም ሆስፒታል የጤና ሚኒስቴር ህግን በጥብቅ በመከተልና ህሙማንን በማገልገል እጩ የ"እናቶች-ምቹ ሆስፒታል" ነው።
1.3K views05:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 16:55:25
የኮርኒያ ንቅለ-ተከላዎች ምን ያህል ስኬታማዎች ናቸው?

የኮርኒያ ንቅለ ተከላ ስኬታማነት መጠን ወደ ህክምናው በሚያመራው መነሾ ህመም ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ የዓይን ኤክስፐርት ፕሮፌሰር ዶክተር ባኑ ኮሳር እንዲህ ሲሉ ያብራራሉ፡፡ “በ keratoconus የኮርኒያ ንቅለ ተከላ ህክምና የስኬት መጠኑ ከ90 በመቶ በላይ ነው። ግን ለሌሎች ምልክቶች የስኬት መጠኑ ዝቅተኛ ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ፣ ለኮርኒያ እብጠት ከንቅለ ተከላ በኋላ ያለው ስኬት ከ80-90 በመቶ ገደማ ይደርሳል። ኮርኒያ በሄፕስ ቫይረስ ሲጠቃ በሚከሰተው የሄርፒቲክ የዓይን ሕመም የህክምናው የስኬት መጠን ከ50 በመቶ እስከ 80 በመቶ ይደርሳል።“ በነጻ የሕክምና አስተያየት አገልግሎትን ከባለሞያዎች ለማግኘት የግል መልእክት ይላኩልን!
1.3K views13:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 12:48:16
ለኮርኒያ ንቀለ-ተከላ እጅግ የዘመኑ ዘዴዎች

ቀደም ባለው ጊዜ የኮርኒያ ንቅለ ተከላ ማለት የታመመውን ኮርኒያ ሙሉ ለሙሉ በጤናማ መተካት ማለት ነበር። ዛሬ የታመሙትን ክፍሎችን ብቻ ለይቶ መተካት ይቻላል፡፡ በዚህም ምክንያት ተያያዥ ስጋቶችን መቀነስ እና የማገገሙን ሂደት ፈጣን ማድረግ ተችሏል፡፡ ይህ ለይቶ የመተካት ዘዴ lamellar keratoplasty ይባላል፡፡ Deep Anterior Lamellar Keratoplasty (DALK) በሚባለው የህክምና ዘዴ የኮርኒያ የላይኛው ሽፋኖችን ለይቶ መለወጥ ሲቻል Descemet Membrane Endothelial Keratoplasty (DMEK) በሚሰኘው የህክምና ዘዴ ደግሞ የውስጠኛውን ክፍል ይለወጣል፡፡ የአቺባደም የዐይን መዕከል እነዚህን የተመረጡ የህክምና ዘዴዎች ለመተግበር በህክምናው የላቁና ዘመናዊ ጥበቦችን የሚተገብሩ ሀኪሞችን ይዟል፡፡
1.3K viewsedited  09:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 08:03:15
ለዒድ አል-አድሐ በዓል እንኳን አደረሳችሁ!

ዒድ ሙባረክ ለእናንተ እና ለወዳጆችዎ ሁሉ። አላህ ይምራዎ፤ ሁልጊዜም መንገድዎን ያብራ።
1.1K views05:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 06:13:45
የኮርኒያ ንቅለ-ተከላ እይታን ይታደጋል

የአለም ጤና ድርጅት እንደሚያሳየው የኮርኒያ በሽታዎች በአለም አቀፍ ደረጃ ለዓይነ ስውርነት ዋነኛ መንስኤዎች ናቸው፡፡ በአብዛኛዎቹ በዚህ መልኩ የሚከሰት ዓይነ ስውርነትን መከላከል ይቻላል፡፡ ኮርኒያ ንቅለ ተከላ ወይም keratoplasty የታመመ ኮርኒያን ከለጋሽ ጤናማ ቲሹ ለመተካት የሚደረግ የቀዶ ጥገና ሂደት ነው። ኮርኒያ በፅኑ በሚታመምበት ጊዜ፣ የኮርኒያ መተካት ዓይንን ለማዳን፣ እይታን ለማሻሻል ወይም ህመሙን ለማስታገስ ይረዳል፡፡ በነጻ የሕክምና አስተያየት አገልግሎትን ከባለሞያዎች ለማግኘት የግል መልእክት ይላኩልን!
#cornea #cornealtransplant #keratoplasty #eyesurgery #RestoreSight
1.4K views03:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ