Get Mystery Box with random crypto!

የኮርኒያ ንቅለ-ተከላዎች ምን ያህል ስኬታማዎች ናቸው? የኮርኒያ ንቅለ ተከላ ስኬታማነት መጠን ወ | Acibadem Healthcare Services

የኮርኒያ ንቅለ-ተከላዎች ምን ያህል ስኬታማዎች ናቸው?

የኮርኒያ ንቅለ ተከላ ስኬታማነት መጠን ወደ ህክምናው በሚያመራው መነሾ ህመም ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ የዓይን ኤክስፐርት ፕሮፌሰር ዶክተር ባኑ ኮሳር እንዲህ ሲሉ ያብራራሉ፡፡ “በ keratoconus የኮርኒያ ንቅለ ተከላ ህክምና የስኬት መጠኑ ከ90 በመቶ በላይ ነው። ግን ለሌሎች ምልክቶች የስኬት መጠኑ ዝቅተኛ ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ፣ ለኮርኒያ እብጠት ከንቅለ ተከላ በኋላ ያለው ስኬት ከ80-90 በመቶ ገደማ ይደርሳል። ኮርኒያ በሄፕስ ቫይረስ ሲጠቃ በሚከሰተው የሄርፒቲክ የዓይን ሕመም የህክምናው የስኬት መጠን ከ50 በመቶ እስከ 80 በመቶ ይደርሳል።“ በነጻ የሕክምና አስተያየት አገልግሎትን ከባለሞያዎች ለማግኘት የግል መልእክት ይላኩልን!