Get Mystery Box with random crypto!

ለኮርኒያ ንቀለ-ተከላ እጅግ የዘመኑ ዘዴዎች ቀደም ባለው ጊዜ የኮርኒያ ንቅለ ተከላ ማለት የታመመ | Acibadem Healthcare Services

ለኮርኒያ ንቀለ-ተከላ እጅግ የዘመኑ ዘዴዎች

ቀደም ባለው ጊዜ የኮርኒያ ንቅለ ተከላ ማለት የታመመውን ኮርኒያ ሙሉ ለሙሉ በጤናማ መተካት ማለት ነበር። ዛሬ የታመሙትን ክፍሎችን ብቻ ለይቶ መተካት ይቻላል፡፡ በዚህም ምክንያት ተያያዥ ስጋቶችን መቀነስ እና የማገገሙን ሂደት ፈጣን ማድረግ ተችሏል፡፡ ይህ ለይቶ የመተካት ዘዴ lamellar keratoplasty ይባላል፡፡ Deep Anterior Lamellar Keratoplasty (DALK) በሚባለው የህክምና ዘዴ የኮርኒያ የላይኛው ሽፋኖችን ለይቶ መለወጥ ሲቻል Descemet Membrane Endothelial Keratoplasty (DMEK) በሚሰኘው የህክምና ዘዴ ደግሞ የውስጠኛውን ክፍል ይለወጣል፡፡ የአቺባደም የዐይን መዕከል እነዚህን የተመረጡ የህክምና ዘዴዎች ለመተግበር በህክምናው የላቁና ዘመናዊ ጥበቦችን የሚተገብሩ ሀኪሞችን ይዟል፡፡