Get Mystery Box with random crypto!

አርቲስት ብሩክታዊት ጌታሁን (ቤቲ ጂ) የፌስቡክ ገጿ መጠለፉን አስታወቀች አርቲስቷ ከ219 ሺህ | ዳሰሳ አዲስ-Access Addis

አርቲስት ብሩክታዊት ጌታሁን (ቤቲ ጂ) የፌስቡክ ገጿ መጠለፉን አስታወቀች

አርቲስቷ ከ219 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉትና ቬሪፋይድ የሆነዉ የፌስቡክ ገጿ መጠለፉን በኢንስታግራም አካዉንቷ ባሰፈረችዉ ጽሁፍ አስታዉቃለች።

“የፌስቡክ ገጼ መጠለፉን ሳሳዉቃቹ እያዘንኩ ነዉ። ይህን ጉዳይ ለመፍታት እየሰራን እንገኛለን። ከተጠለፈዉ ፌስቡክ ገጼም ሆነ ትክክለኛ ካልሆኑ (unofficial) አካዉንቶች የሚተላለፉ መልዕክቶች የኔ አይደሉም” ብላለች።

የአርቲስቷ ፌስቡክ ገጽ ፕሮፋይል ምስል ከአስር ቀናት በፊት መቀየሩንና ከዛ ወዲህም የተለያዩ መልዕክቶች በገጹ ላይ መለጠፋቸዉን ተመልክተናል።
@AccessAddis