Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት መረጃ( acadamic info)

የቴሌግራም ቻናል አርማ academic_info — ትምህርት መረጃ( acadamic info)
የቴሌግራም ቻናል አርማ academic_info — ትምህርት መረጃ( acadamic info)
የሰርጥ አድራሻ: @academic_info
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.30K
የሰርጥ መግለጫ

ትምህርትነክ እና ትክክለኛ መረጃዎች ይስተናገዱበታል።

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 15:42:40
የ2015 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምርት ቢሮ የሥርዓተ-የትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳሮክቶሬት በአዲሱ ሥርዐተ -ትምህርት ለሙሉ ትግበራ ሳምንታዊ ጊዜያዊ የክፍለ ጊዜ ድልድል የተላከ የክፍለ ጊዜ ሥርጪት።
351 views12:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 12:25:38
የዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ ቴክኒካል ረዳቶች እና የትምህርት ባለሙያዎች በሙሉ የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የ2014/15 ትምህርት ዘመን የሁለተኛ ደረጃ ማጠቃለያ ብሔራዊ ፈተናን በዩኒቨርሲቲዎች እንዲሰጥ መወሰኑ ይታወቃል።
በመሆኑም በፈታኝነት፣ ለአይነ-ስውራን ተፈታኞች አንባቢነት እና በመልስ መስጫ ወረቀት ቆጣሪነት ስራዎች የሚሳተፉ የፈተና አስፈፃሚዎችን መመልመያ መስፈርት
449 views09:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:32:48
Jinja University Job vacancy
222 views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 20:04:45 https://www.facebook.com/146634408702997/posts/pfbid02CdbZm94rsU1DNt3XhPqT9M4zqSftZkUQPzYpQhfZpJ8gt6585VUhUx9agcJfe7xrl/
የኢትዮጵያ መምህራን ማሕበር ጦርነቱ ቆሞ ድርድር እንዲጀመር ጠየቀ
በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት በአስቸኳይ ቆሞ የአፍሪካ ሕብረት ለሰላም የጀመረውን የማደራደር ኃላፊነት እንዲቀጥል የኢትዮጵያ መምህራን ማሕበር ጠየቀ።
ማሕበሩ ዛሬ በሰጠው መግለጫ በኢትዮጵያ የሚከሰቱና የተከሰቱ ግጭቶች ሁሉ በውይይት መፈታት ያለባቸውና የሚችሉ ናቸው ብሏል።
ጦርነቱ ለመምህራን ጥያቄዎች ወቅታዊ ምላሽ ለማግኘት እንቅፋት ሆኖብኛል ያለው ማሕበሩ በተለይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን የደሞዝ ማሻሻያ እና ሌሎች ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ግፊት ማድረጌን እቀጥላለሁ ብሏል።
የዩኒቨርሲቲ መምህራን በተለይ ለደሞዝ ጭማሪ ጥያቄዎቻቸው ምላሽ እንዲሰጣቸው ደጋግመው እየጠየቁ ሲሆን ማሻሻያ ካልተደረገ ሥራ በማቆም ጭምር ለጥያቄያቸው ምላሽ መገኘት ግፊት እንደሚያደርጉ እየገለፁ ይገኛሉ።
ዘገባው የአዲስ አበባው ዘጋቢችን የሰለሞን ሙጨ ነው።
303 viewsedited  17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 13:44:49 በ2015 ዓም የትምህርት ዘመን በመንግስት ትምህርትቤቶች የተማሪ የመመዝገቢያ ማስከፈል  አይፈቀድም
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ዘሬ ጥዋት ላይ በደረሰን ጥቆማ የተወሰኑ የመንግስት  ትምህርትቤቶች የመመዝገቢያ ክፍያ እያስከፈሉ መሆናቸውን
አረጋግጠናል። ይህ ተግባር ህገወጥ ነው።

ስለዚህ በ2015 ዓም የትምህርት ዘመን ማንኛውም የመንግስት ትምህርት ቤት ምንም አይነት የመመዝገቢያ ክፍያ ማስከፈል ያልተፈቀደለት መሆኑን  በጥብቅ እናሳስባለን።

N.B:
የግል ትምህርት ቤቶችን በተመለከተም በቢሮው በኩል ተዘጋጅቶ ከተላከው መመሪያ ውጭ ወርሀዊም ሆነ የመመዝገቢያ ክፍያ ያስከፈለ ትምህርት ቤት ካለ በአስቸኳይ እንዲያስተካክል እያስጠነቀቅን በምናደርገው ክትትል መመሪያውን ተላልፎ የሚገኝ ካለ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እናሳስስባለን።

ማተብ ታፈረ (ዶ/ር)

የአብክመ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ
558 views10:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 11:09:51 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሠራተኞች የጋራ ህንፃ መኖሪያ ቤት የህብረት ሥራ ማህበር አደረጃጀትና አፈፃፀም ደንብ ቁጥር 129/2014
562 views08:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 17:08:41 የትምህርት ማስረጃዎችን በዲጅታል መያዝ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ይፋ ሆነ።
****
(ኢ ፕ ድ)

የትምህርት ተቋማትን መረጀ ማስቀመጥና ማሥተዳደር የሚያስችል "ኢ-ስኩል" የተሰኘ ቴክኖሎጂ ይፋ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ቴክኖሎጂው ዋልያ ቴክኖሎጂ በተባለ የግል ድርጅት የበለፀገ ሲሆን የመምህራንና የተማሪዎችን መረጃዎች መያዝ ከማስቻልም ባለፈ የመማር ማስተማሩን ሂደት የሚያዘምን መሆኑ ተገልጿል።

በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ፋንታ ማንደፍሮ (ዶ/ር) የትምህርት ተቋማት የመረጃ አያያዝ ሥርዓታቸውን በማዘመን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በመታገዝ ማስቀመጥና ማስተደደር እንደሚገባቸው ገልጸዋል፡፡

ቴክኖሎጂው በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ አደጋ ምክኒያት በትምህርት ማስረጃዎች ላይ የሚደርሰውን ጥፉት ይቀርፋልም ብለዋል።

ዶ/ር ፋንታ በቅርቡ በሀገራችን በሰሜኑ ክፍል ሲካሄድ በነበረው ጦርነት ከትምህርት ተቋማቱ ባሻገር የትምህርት ማስረጃዎች መውደማቸውን ገልፀው ከዚህም ትምህርት በመውሰድ በቀጣይ ትምህርት ቤቶች የመረጃና ማስረጃ አያያዝ ሥርዓታቸውን በማዘመን የመረጃ ማዕከላቸውን በድጂታል ቴክኖሎጂ በመታገዝ እንዲያስተዳድሩ ማድረግ አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የዋልያ ቴክኖሎጂ መስራች የሆኑት አቶ አንተነህ አሥራት ዲጂታል ቴክኖሎጂው ትምህርት ቤቶች መረጃና ማስረጃዎችን ዲጂታላይዝ አድርገው እንዲያስቀምጡትና እንዲያስተዳድሩ የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል።

ቴክኖሎጂው ተማሪዎች የትምህርት መርጃ መጽሃፍትን የሚያገኙበትንም ቤተመጽሃፍትንም ማካተቱ ተገልጿል።

ቴክኖሎጂውን በመጠቀምም የትምህርት ቤት ክፍያዎችን በኦንላይን እንዲከፍሉ የሚያስችል እና ዘረፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ዘርፉን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።
324 views14:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 07:55:59 ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች
የመኖርያ ቤት ኪራይ መጨመርም ይሁን ተከራይን ማስወጣት የሚከለክለው ደንብ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት እንዲራዘም ተወስኗል፡፡

ነሐሴ 20/2014፣ የካ ኮሙኒኬሽን

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዜጎች ላይ የሚደርሰውን የኑሮ ጫናን ለመቀነስ በመኖርያ ቤት ተከራዮች ላይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ እና ተከራይን ማስለቀቅን የሚከለክል ደንብ አውጥቶ ተግባራዊ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ ይህም ደንብ በተለያየ ጊዜ እየተራዘመ ላለፈው አንድ አመት ተግባራዊ ተደርጎ ቆይቷል፡፡

ስለሆነም የከተማ አስተዳደሩ አሁን ያለውን አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ እና የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና ከግምት ባስገባ ወቅቱን በአብሮነትና በመተሳሰብ ለማለፍ ይረዳ ዘንድ ይህ ደንብ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት እንዲራዘም ወስኗል፡፡

በመሆኑም ይህንን ክለከላ በመተላለፍ ተከራዮችን የሚያስወጡ እና የኪራይ ዋጋን የሚጨምሩ አካላት ላይ ማህበረሰቡ በሚከተሉት የስልክ ቁጥሮች ጥቆማውን ለከተማ አስተዳደሩ ማድረስ እንደሚችል ያስታውቃል፡፡

አጭር ቁጥር ፡- 9977

የሞባይል ስልኮች

09-00640830
09-00640789
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
966 views04:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 07:48:33 የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

የደቡብ ክልል እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑ ዛሬ ተገልጿል።

በሁለቱ ክልሎች ውሳኔ መሰረት የማለፊያ ነጥብ ፦

ለወንዶች 41፣
ለሴቶች 40 እና
ለአይነ ስውራን 39 ሆኖ ተወስኗል።

በዚህ መሰረት ፦ በ2014 የትምህርት ዘመን በሁለቱም ክልሎች ለፈተና ከተቀመጡ ከ257 ሺህ በላይ ተማሪዎች 187 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች ወደቀጣይ ክፍል የሚያሳልፋቸውን ውጤት አምጥተዋል።

ለፈተና ከተቀመጠው አጠቃላይ ተማሪ ቁጥር ሲታይ ከ73 በመቶ በላይ ተማሪዎች አልፈዋል።

በተለየ መልኩ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ በአሉታዊ ጫና ውስጥ ሆነው የተማሩና ለፈተና የተቀመጡ የደራሼ ልዩ ወረዳ ተማሪዎችን ውጤት በተለየ መልኩ ታይቷታ።

በዚህም መሰረት ፦

ለወንዶች 39፣
ለሴቶች 38 እና
ለአይነ ስውራን 37 ሆኖ ተወስኗል።

የሁለቱ ክልሎች ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ጀምሮ መውሰድ ይችላሉ ተብሏል።

የደራሼ ልዩ ወረዳ ተማሪዎች ግን ውጤታቸው በእጅ የሚሰራ በመሆኑ የ1 ሳምንት ጊዜ ዘግይቶ ይደርሳል እስከዛው በትዕግስት እንዲጠባበቁ መልዕክት ተላልፏል
829 views04:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ