Get Mystery Box with random crypto!

* የመንፈስ ቅዱስ አካልነት! * > የተለያዩ የስህተት አስተማሪዎች ስለ መንፈስ ቅዱስ ሲናገሩ፣ | የጸጋ ወንጌል

* የመንፈስ ቅዱስ አካልነት! *

> የተለያዩ የስህተት አስተማሪዎች ስለ መንፈስ ቅዱስ ሲናገሩ፣ “መንፈስ ቅዱስ የሆነ ኃይል ወይም ተጽህኖ እንጂ አካል ያለው አይደለም” ይላሉ፡፡

> መጽሐፉ ግን መንፈስ ቅዱስ አካል ያለው መለኮት እንጂ የሆነ ኃይል ወይም ተጽህኖ እንዳልሆነ በሚከተሉት ጥቅሶች ያስረዳናል፡፡ አካል ስንል በዋናነት ስሜት፣ ፈቃድና እውቀት ያለውን ማንነት እያመለከትን ነው።

#ጥቂት ስለ መንፈስ ቅዱስ አካልነት የሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

1ኛ. 2ሳሙ.23፡2-3፣ ማቴ.10፡20 መንፈስ ቅዱስ ሲናገር ያሳያል፡፡

2ኛ. ማቴ.28፡19 መንፈስ ቅዱስ አካል ካላቸው አብና ወልድ ጋር በአንድነት ቀርቦዋል፡፡

3ኛ. ኢሳ.63፡14፣ ሉቃ.4፡1 መንፈስ ቅዱስ ይመራል፡፡

4ኛ. ሉቃ.12፡12 መንፈስ ቅዱስ ያስተምራችኃል ተብሎዋል፡፡

5ኛ. ዮሐ.16፡8 መንፈስ ቅዱስ ይወቅሳል ተብሎዋል፤ አካል እንጂ አይል አይወቅስም፡፡

6ኛ. ዮሐ.16፡13 ላይ መንፈስ ቅዱስ ይመራል፣ ይናገራል፣ ይሰማል ተብለናል፡፡

7ኛ. ዮሐ.14፡16 ላይ “ሌላ” የሚለው የተለየ ግን እንደ እኔው የሆነ አካል ማለት ነው፡፡

8ኛ. ዮሐ.14፡16፣ 16፡7 መንፈስ ቅዱስ የኢየሱስን ቦታ ተክቶ እንደሚያጽናናቸው ተነግሮናል፤ አይል የኢየሱስ ቦታ ሊተካም ሆነ ሊያጽናና አይችልም፡፡

9ኛ. ዮሐ.16፡16-17 መንፈስ ቅዱስ እርሱ ተብሎዋል፡፡

10ኛ. ዮሐ.14፡16 ከእናንተ ጋር ይኖራል የሚለው መንፈስ ቅዱስ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዳለው ማሳያ ነው፡፡

11ኛ. ዮሐ.15፡26 መንፈስ ቅዱስ ምስክር ተብሎዋል፤ አካል እንጂ አይል ምስክር ሊሆን አይችልም፡፡ ቁ.27 ላይ አካል የሆኑት ደቀመዛሙርቱ ምስክር በተባሉበት መጠን መንፈስ ቅዱስም እንደዚያ መባሉን ማስተዋ ይገባል፡፡

12ኛ. የሐዋ.5፡1-5 ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስን ለመዋሸት ወይም ለማታለል ሞከራችሁ ብሎዋል፡፡

13ኛ. የሐዋ.10፡19-20 መንፈስ ቅዱስ ሲናገር እና ሲልካቸው እናያለን፡፡

14ኛ. የሐዋ.13፡2 ሰዎችን ለስራ ለዩልኝ ሲል እናያለን፡፡

15ኛ. የሐዋ.15፡28 መንፈስ ቅዱስ ሲፈቅድ ይታያል፡፡

16ኛ. የሐዋ.16፡6-7 መንፈስ ቅዱስ ይከለክላል፡፡

17ኛ. ሕዝ.37፡14፣ ሮሜ.8፡11 መንፈስ ቅዱስ ሕይወትን ይሰጣል፡፡

18ኛ. ሮሜ.8፡14 መንፈስ ቅዱስ ይመራል፡፡

19ኛ. ሮሜ.8፡26 መንፈስ ቅዱስ ይጸልያል ወይም ይማልዳል እንዲሁም የአብን የእኛንም አሳብ ያውቃል ተብሎዋል፡፡

20ኛ. ሮሜ.8፡27 መንፈስ ቅዱስ አሳብ እንዳለው ይነገራል፡፡ አካል እንጂ አይል አሳብ የለውም፡፡

21ኛ. ሮሜ.15፡30 መንፈስ ቅዱስ እንደሚወድ ይናገራል፡፡ መውደድ የአካል ጠባይ ነው፡፡

22ኛ. 1ቆሮ.2፡10-11መንፈስ ቅዱስ እውቀት አለው፡፡

23ኛ. 1ቆሮ.12፡11 መንፈስ ቅዱስ ፈቃድ አለው፡፡