Get Mystery Box with random crypto!

#የመዳን ቀን ፣ #የቁጣው ቀን! “በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤ እነሆ፥ | የጸጋ ወንጌል

#የመዳን ቀን ፣ #የቁጣው ቀን!

“በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።”
  — 2ኛ ቆሮ 6፥2
#።።
ራእይ 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ፥
¹⁶ ተራራዎችንና ዓለቶችንም፦ በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን፤
¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን መጥቶአልና፥ ማንስ ሊቆም ይችላል? አሉአቸው።

☞ እያንዳንዱ ሰው ኃጢአተኛና በደለኛ በመሆኑ ለሰው ኃጢአትና በደል ምላሽ የሆነውን የቅዱሱ እግዚአብሔር የጽድቅ ቁጣ ማለትም #የዘላለም #የሞት_ፍርድ ይገቧል ነገር ግን የእግዚአብሔር ፍቅር  ሰለ ሰው ኃጢአትና በደል የጽድቁ ቁጣ #በቅዱሱ ልጁ #በኢየሱስ ክርስቶስ #በመስቀል ላይ  በማፍሰስ ይህን ፍቅር #አምነው ለሚቀበሉ ሁሉ #የዘላለም_መዳን አደረገ! የሚደንቅ ጸጋ።

— ኢየሱስ ክርስቶስ ሰለ ኃጢአታችን ሞቷል(1ዼጥ3፥18)
— ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሁሉ ይድን ዘንድ በመስቀል ስለ ሁሉ ነፍሱን #ቤዛ አድርጎ ሰጥቷል(2ጢሚ2፥5–6 ፣ ሮሜ 3፥23–24)
— ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ኃጢአተኛው(ሰው ሁሉ) የሚገባውን ፍርድ በመቀበል #በመስቀል ላይ #ተፈጸመ በማለት #የኃጢአተኛውን #መዳንና #ከሞት #በመነሣት ደግሞ #የኃጢአተኛውን በእግዚአብሔር ዘንድ #መጽደቅ ወይም መሉ በሙሉ #ተቀባይነት ማግኘቱን አረጋግጧል(ዮሓ19፥28–30 ፣ ሮሜ4፥25)።

# ሰው ሰለ ኃጢአቱና ሰለ በደሉ ከሚገባው #የዘላለም የእግዚአብሔር የጽድቅ #ቁጣ #ይድን ያልተጠናቀቀ የቀረ ሥራ የለም #ሁሉም #በቅዱሱ #በእግዚአብሔር ልጅ #በኢየሱስ_ክርስቶስ #ሞትና #ትንሣኤ ተፈጽመዋል! የሰው ድርሻ ሰለ ኃጢአቱ #በሞተውና እርሱን ሰለማጽደቅ ከሞት #በተነሣው #በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ #በእውነት #ማመን ብቻ ነው።

“#በእርሱ #የሚያምን #ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”
  — ዮሐንስ 3፥16


☞ ታድያ ሰው #በእውነተኛው #አዳኝና #ጌታ #በእውነት አምኖ የሚድንበት ቀን መቼ ይሆን? የእግዚአብሔር ቃል #የመዳን ቀን #አሁን ነው ይላል! ወገኖች #በጌታ #በኢየሱስ_ክርስቶስ #በእውነት #ካለመናችሁ #አሁኑኑ በእርሱ አምናችሁ #ከዘላለም ቁጣ ትድኑ ዘንድ #በእግዚአብሔር ፍቅር ጥሪአችንን እናቀርባለን።

☞ በብዙ የዋህነትና ትዕግስት በምድር ላይ በተመላለሰው ፣ የዓለምን ኃጢአት ያስወግድ ዘንድ በመስቀል #በሞተው #በእግዚአብሔር_በግ #ኢየሱስ  ዛሬ አሁን #የጸጋው_በር ሳይዘጋ #በእውነት #ያላመኑና #የማያምኑ ሰዎች #የቁጣ_ቀን ይጠብቃቸዋል! ያኔ በጉ በቁጣ ይገለጣል(ራእ6፥ 15–17)።

“በልጁ( በኢየሱስ) የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን #የእግዚአብሔር #ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።”
  — ዮሐንስ 3፥36