Get Mystery Box with random crypto!

*እግዚአብሔርን የሚቀድመው ማነው?* ፍጥረት በሙሉ በጊዜ ውስጥ ነው፤ ጊዜ ራሱ ደግሞ በእግዚአብሔር | የጸጋ ወንጌል

*እግዚአብሔርን የሚቀድመው ማነው?*
ፍጥረት በሙሉ በጊዜ ውስጥ ነው፤ ጊዜ ራሱ ደግሞ በእግዚአብሔር ውስጥ ነው!

> እግዚአብሔር አሳቡ፣ ሰው በምድር ባሉት ፍጥረታት ሁሉ ላይ ባለስልጣን ሆኖ ምድርን እየጠበቃት እና እያበጃት፣ በጋብቻም ሕይወት እየተባዛ በተባረከች ምድር ከእርሱ ጋር ኅብረት እያደረገ እንዲኖር ነበር።

#ይህን ያየው ሰይጣን ምን አደረገ?

> እግዚአብሔር ያሰበው ከመፈፀሙ በፊት ሊቀድመው ሞከረ፤ አዳምና ሚስቱ የገነት ኑሮን መኖር በጀመሩ በጥቂት ጊዜ ውስጥ (ምክንያቱም ልጅ እንኳ ገና አልወለዱም) የሰማይን ምክር ሊያፈራርሰው ፈለገ፤ ሰይጣን የእግዚአብሔርን አሳብ ቀድሞ በመገኘት ከፊት ያለውን እቅድ ጨለማ ሊያደርገው ሞከረ።

#ውጤት ምን ሆነ?

> ከላይ ሲታይ ሰይጣን ተሳካለት፤ እግዚአብሔርም ለሰው ያሰበው በአብዛኛው ሳይሆን ቀረ። ሰይጣን አዳምና ሔዋን ከእግዚአብሔር አለያይቶ፣ የሰማዩን እቅድ የቀደመ መሰለ።

#እና እግዚአብሔር ተቀደመን?

> በፍፁም! ሰይጣን ያልገባው አንድ ነገር ነበር፤ አዳምና ሔዋን ገና ኃጢአት ከመስራታቸው በፊት በእግዚአብሔር ፊት ሲኖሩ ሳለ፣ ኃጢአት ሰርተው ከእርሱ እንደሚርቁ የሚያውቀው እግዚአብሔር፣ አዳምና ሔዋን ኃጢአት የሚሰሩበትን ቀን ቀድሞ ሄዶ አልፎ ገና ባልመጣ ቀን ላይ ቀድሞ ሄዶ እየጠበቃቸው ነበር።

> ሰዓት ቀዶሞ የሄደው ያው እግዚአብሔር፣ ወደፊት ብቻ ሳይሆን ወደ ኋላ ማለት አዳምና ሚስቱ ከመፈጠራቸው በፊትም አለና ሰይጣን የማያውቀውን ሌላ እቅድ አስቦ ጨርሷል(ኤፌ፡1÷4)።

> ምን እያልኩ ነው፦ እግዚአብሔር አልፋና ዖሜጋ ነው፤ ዛሬ ቅዳሜ ነው፤ እግዚአብሔር አልፋ ነውና ከቅዳሜ በፊት አለ፤ እግዚአብሔር ዖሜጋ ነውና ከቅዳሜ በኋላ አለ።

ፍጥረት በሙሉ በጊዜ ውስጥ ነው፤ ጊዜ ራሱ ደግሞ በእግዚአብሔር ውስጥ ነው!

#እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ዓለም ሳይፈጠር ያቀደውን ተመልከቱ

1: ሊበላሽ የሚችለው የተፈጥሮ ሕይወት ቀርቶ የዘላለም ሕይወት ባለቤት ማድረግ

2ኛ፡ በምድር ገነት ቀርቶ፣ በሰማዩ ገነት ማኖር

3ኛ፡ የምድር ላይ ብቻ ብቻቸውን ባለስልጣን ከሚሆኑ ከክርስቶስ ጋር በሰማይና በምድር ማንገስ

4ኛ፡ ሰይጣን፣ ኃጢአት፣ ሞት ለመግባት እድሉ ካላቸው ምድር ይልቅ ሶስቱም ድርሽ የማይሉበት የአብ ቤት ማኖር

> ሰይጣን ነገር አበላሻለሁ ብሎ፣ ክብር አስጨመረልን! ዘፍ፡3÷15 ላይ እግዚአብሔር የሴቲቱት ዘር ክርስቶስን እንገሚልክ ሰይጣን ሲሰማ፣ "ምነው መጀመሪያም ባልነካካው!" እንዳለ አስባለሁ።

#እናም መልእክቱ ይህ ነው! እግዚአብሔርን ማንም አይቀድመውም!!!

“አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።”
— ራእይ 22፥13