Get Mystery Box with random crypto!

«ስምህን ለወንድሞቼ እነግራቸዋለሁ በጉባኤም መካከል አመሰግንሃለሁ፡፡ እግዚአብሔርን የምትፈሩ አመስ | የጸጋ ወንጌል

«ስምህን ለወንድሞቼ እነግራቸዋለሁ በጉባኤም መካከል አመሰግንሃለሁ፡፡ እግዚአብሔርን የምትፈሩ አመስግኑት የያዕቆብ ዘር ሁላችሁ ፍሩት፡፡ ... በታላቅ ጉባኤ ምስጋናዬ ከአንተ ዘንድ ነው፤ እርሱን በሚፈሩት ፊት ስለቴን እሰጣለሁ፡፡ ችግረኞች ይበላሉ ይጠግቡማል፤ እግዚአብሔርንም የሚሹት ያመሰግኑታል፤ ልባቸውም ለዘላለም ሕያው ይሆናል፡፡ የምድር ዳርቻዎች ሁሉ ያስቡ ወደ እግዚአብሔርም ይመለሱ፤ የአሕዛብ ነገዶች ሁሉ በፊቱ ይሰግዳሉ፡፡ መንግሥት ለእግዚአብሔር ነውና እርሱም አሕዛብን ይገዛል፡፡... ዘሬ ይገዛለታል፤ የምትመጣው ትውልድ ለእግዚአብሔር ትነግረዋለች ጽድቁንም ለሚወለደው ሕዝብ እግዚአብሔር ያደረገውን ጽድቁን ይነግራሉ» (ቁ.22-31)፡፡
ታላቅ በሆነ ግልጽነት እነዚህ ሁለት ጥቅሶች የክርስቶስን ሞት ሁለቱን ገጽታዎች ያሳያሉ፡፡ እርሱ እንደ አንድ ሰማዕት ስለጽድቅ በሰው እጅ ሞተ፡፡ ለዚህም የሰው ልጅ ስለፈጸመው ግድያ ለእግዚአብሐር መልስ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡ ነገር ግን በሌላ ገጹ እርሱ እንደ አንድ ሰለባ በእግዚአብሔር እጅ ለኃጢአተ ሞተ፡፡ ይህም በስሙ ለሚያምኑት ሁሉ ለበረከቶች ሁሉ መሠረት ነው፡፡ የክርስቶስ የሰማዕትነት መከራ ቁጣንና ፍርድን በአምላክ የለሸ ዓለም ላይ ያወርዳል፤ ሥርየትን ለማስገኘት የተቀበለው መከራው ግን ለቤተክርስቲያን ለእስራኤልና ለመላው ፍጥረት ሁሉ ሕይወትና የመዳን የዘላለም ምንጭ እንዲከፈት አደረገ፡፡ የኢየሱስ ሞት የዓለምን የጥፋት ቁንጮ ሲያመለከት ለቤተክርስቲያን ግን ተቀባይነትዋን ያረጋግጣል፡፡ ዓለም በመስቀል ደም ስትጐድፍ ቤተክርስቲያን ግን በዚሁ ደም ነጻች፡፡