Get Mystery Box with random crypto!

ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ

የቴሌግራም ቻናል አርማ abuteqiypomechannel — ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ
የቴሌግራም ቻናል አርማ abuteqiypomechannel — ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ
የሰርጥ አድራሻ: @abuteqiypomechannel
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.14K
የሰርጥ መግለጫ

📚ይህ ቻናል
ግጥሞችን፣
ቁርዓንና ሀዲስ፣
ደርሶችን፣
ሙሀደራ
ሊንክ፣የመሳሰሉትንበኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ ስር በተከፈቱት ቻናሎች ውስጥ የሚተላለፉ መልዕክቶች ከየሁሉም የተሰባሰቡ ትምህርቶች የሚላክበት ቻናል ነው።
አስተያየት 📞 @CommentAnd1_bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-04-10 12:52:06 https://t.me/SadatKemalAbuMeryem?livestream
1.2K viewsابو تقي قاعد, 09:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 18:44:21 ‏عاجل:

‏رؤية هلال شهر رمضان في سدير..
‏وغداً السبت أول أيام رمضان بالسعودية .

በአላህ ፍቃድ ነገ ቅዳሜ ረመዷን አንድ ነው።
1.3K viewsابو تقي قاعد, 15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 22:25:45 ታላቁ ወር .... ወደ አላህ ለመቅረብ በዚክር በኢባዳ በኢኽላሱ መጠን ሊበዛልን ምንዳ ታላቁ ወር መጣ ኸይርን መሸመቻ የአጅር ሀሰናት ካዝናን ማካበቻ። እንግዲህ የአላህ ቤት በኸልቁ ተዋቢ መጣልሽ ረመዳን በድምፆች አብቢ። ምላስም ለዘበች ከወሬ ከሀሜት ከተራ ዛዛታ የማይረቡ ቃላት ከከንቱ ንግግር ከቀልድ ና ውሸት ተጠመደች…
1.6K viewsابو تقي قاعد, 19:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 21:17:41 ታላቁ ወር ....


ወደ አላህ ለመቅረብ በዚክር በኢባዳ
በኢኽላሱ መጠን ሊበዛልን ምንዳ
ታላቁ ወር መጣ ኸይርን መሸመቻ
የአጅር ሀሰናት ካዝናን ማካበቻ።

እንግዲህ የአላህ ቤት በኸልቁ ተዋቢ
መጣልሽ ረመዳን በድምፆች አብቢ።

ምላስም ለዘበች ከወሬ ከሀሜት
ከተራ ዛዛታ የማይረቡ ቃላት
ከከንቱ ንግግር ከቀልድ ና ውሸት
ተጠመደች እና በዚክር በቂርዓት።

ባማረ ቅላፄ ድምጿ ሊስተጋባ
ወደ አላህ በመቅረብ ሊረጥብ ነው ቀልቧ።

በአመፅ በገፍላ የተረሱ ለይሎች
ደረሰ ረመዳን ብድግ አሉ ጎኖች
ሀጃ ገጠማቸው እዝነቱ ጠራቸው
ከእንቅልፍ አባንኖ ለይል አቆማቸው።

ቀልብም ይመርባት ተጊጣ ተውባ
በመልካም ስራዎች ወደ አላህ ቀርባ
ሰኪናን አግኝታ ተቅዋን ደርባ።

በወርሃ ረመዳን ሁሉም ነገር ያምራል
ከወንጀል ከባጢል ከተማው ይፀዳል
ሼጧን አሳሳቹ ከኛ ይታሰራል
ከሰዎች ልብ ላይ ውስወሳው ይርቃል
በሙዐዚን ጥሪ ሀገሩ ይደምቃል
ጀሀነም ተዘግቶ ጀነት ይከፈታል
የራህመት እጆቹን አላህ ይዘረጋል
በስቲግፋር ሰደቃ ቁጣው ይወገዳል
ከወር ሁሉ መርጦ አላህ አልቆታል።

ፈድሉና ራህመቱ ኒዕማው እና ፀጋው
በወርሃ ረመዳን ሰፊና ጥልቅ ነው።

በዚህ በረመዳን ፆመኞች በሙሉ
በተሟላ ኒያ አላህን ካሰቡ
ሽርክና ቢድዓ ክልክላት ከራቁ
በተውሂድ ተጉዘው ሱናን ከጠበቁ
በሆድ ብቻ ሳይሆን በአካል ከፆሙ
ረያን አላቸው ምነኛ ታደሉ።

ማንም አይገባትም ይችን የጀነት በር
ሳይታክት ቢታገል ወይም ደግሞ ቢጥር
ማንም ይሁን ማንም ከፆመኞች በቀር
አላህ ይወፍቀን ይጠብቀን ከሸር
ግዴታ መሆኑ በዚሁ ታላቅ ወር
መፆሙ ለአላህ ተቅዋ እንዲኖር።

ከዚሁ እንንቃ ሴቶች እባካቹ
ሳንቡሳ ስጠብሱ ሾርባውን ጥዳቹ
ከምግቡ ብዛት ብፌ ደርድራቹ
ምግብን በማብሰል አይለቅ ጊዜያቹ
ሳትጠቀሙበት ወሩ እንዳያልፋቹ
ወሩ እኮ አይደለም የምግብ የመጠጥ
ቤቶችን የማስዋብ በውዶች ጌጣጌጥ
ከዚህም ከዚያም በስራ መራወጥ።

አጥብቀን እንያዝ የነብዩን ሱና
ጥርት ባለው መንገድ በሰለፎች ፋና
ተውሂድ እንዲሰምር ህይወት እንዲቃና።

ምስጋና ይገባህ ወሮችን ለፈጠርክ
በተለይ ረመዳን ለኛ ስላደረክ
ውለታህ ብዙ ነው ተነግሮ አያልቅም
ለፀጋህ መግለጫ አጥቻለው አቅም
አንተን ማወደሻ ቃላትን አላውቅም
ቃላት ቢሰካኩ ለክብርህ አይበቃም።

አድርሰን ያረቢ አግራልን ኢባዳ
ነጃ እንድንባል ከቁጭቱ ዕዳ።

ሙና ሙሀጅር
https://t.me/AbuTekiyPomeChannel
1.9K views@munatiiiiiiii, edited  18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ