Get Mystery Box with random crypto!

የፋሲካሰላምታአሰጣጥትርጉም ምሕዛል ወቃለ ባሕ ዘትንሣኤ Paschal troparion & Greeti | አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)

የፋሲካሰላምታአሰጣጥትርጉም

ምሕዛል ወቃለ ባሕ ዘትንሣኤ Paschal troparion & Greeting

(ለትንሣኤ የተቆነጠረ ሐሳብ)

ሀገርኛው የዘውትር ሰላምታችን ሰላም ላንተ ይኹን ጠላትኽን ያውድቅ ቢሰኛኽን ያርቅ! በሚል መነሻ ስብሐተ እግዚአብሔር የሚታከልበት ምኞት መግለጫና ምስጋና ማቅረቢያ ነው!

የሰላምታው መንገድ ደግሞ በሦስት ሂደት (በቃል በእጅና በአንገት) የሚከወን ነው።


መጨባበጥ (ተራክቦተ እድ ፣ ፅብጠት፣ ተጻብሖ) ☞ በእጅ የሚፈጸም ፦ በመጨባበጥ handshake በመተቃቀፍ hugging አልያም በጉንጭ በመሳሳም cheek kissing ይፈጸም የነበረውን በቀደሙቱ ዘንድ “አምኃ ቅድሳት” holy kiss & kiss of peace ⇨ ἐν ἁγίω φιλήματι, και φιλί της ειρήνης እየተባለ የሚጠራው መንገድ ነው!

በዚኽ አጋጣሚ በወቅቱ ጉዳይ መጨባበጥ መተቃቀፍና መሳሳም ለወረርሽቹ በፍጥነት መዛመት ምክንያት መሆናቸውን አውቀን #አካላዊፈቀቅታ|ን በመጠበቅ በበሽታው የምናልፍ ሳንሆን በሽታውን የምናሳልፍ ነገንም የምናይ እንድንሆን በተከታዮቹ መንገዶች ሰላምታ የምንለዋወጥ ይሁን!


"እጅ መነሳሳት" (እማኄ) ☞ ባንገት፣ በወገብና በጕልበት የሚፈጸም ነው


የሰላምታ ቃል መለዋወጥ (በቃለ ተአምኆ) ሰላምታ በንግግር በመለዋወጥ የሚፈጸም ዋናዎቹ ናቸው!

ወደ ተቆነጠረው ሐሳብ እንለፍ ተዝካረ ትንሣኤው በሚታሰብበት ዐባይ ፋሲካ ፶ ዕለት በቤተክርስቲያናችን የሚፈጸም የተለየ ሰላምታና የዜማ ድጋም አመላለስ አለ

የጌታችን ተዝካረ ትንሣኤ በቤተክርስቲያናችን ሰፊ ቦታና ትርጉም ያለው በመሆኑ የዓመት ሢሦው (⅓) ነገረ ፋሲካን የሚያስታውስ ነው (የፋሲካ ጾም ⁵⁵ እና ዘመነ ትንሣኤ⁵⁰)

በቅዳሴው መግቢያ መስዋእቱ ከቤተልሔም ወደ ቤተ መቅደስ ሲመጣ ከትንሳኤው እስከ በዓለ ፶ ጊዜው የተለየ መሆኑን ለማሳወቅ "እመቦ ብእሲ… " በሚለው መግቢያ ፈንታ "ሃሌ ሉያ ዮሴፍ ወኒቆዲሞስ ገነዝዎ ለኢየሱስ በሰንዱናት ለዘተንሥአ እሙታን በመንክር ኪነ ⇨ ሃሌ ሉያ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ድንቅ በሚሆን ጥበብ ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ኢየሱስን በበፍታ ገነዙት፡፡" የሚል መልእክት በዜማ ይደርሳል!

ከዚኽ ውጪ ምሕዛል ዘትንሣኤ ወይም «የፋሲካ አመላለስ» ያልነው Paschal troparion እና ቃለ ባሕ ዘትንሣኤ «የፋሲካ ሰላምታ» ያልነው Paschal Greeting ከወትሮው በተለየ መንገድ ይፈጸማል። ሁለቱም በልሳነ ጽርእ (ግሪክ) #ክሪስቶስ_አኔስቲ / Χριστὸς ἀνέστη እየተባለ ይጠራል

① #ምሕዛል_ዘትንሣኤ Paschal troparion የፋሲካ አመላለስ

በእርግጥ ምሕዛል አልያም ምስትሕዛል የሚባለው በድጓው ሊቃውንቱ የሚያስተዛዝሉት ዜማ ድጋም ሲሆን መነሻውን ድጓ ያደረገው በቅዳሴው ክፍል የምናገኘው ይኽ የተዝካረ ትንሣኤ ምስትሕዛል፦
«ህየንተ ዝውእቱ ጊዜ ባርኮት እምትንሣኤ እስከ በዓለ ፶ » በሚል የገባ ሦስት ጊዜ ደጋግመን በመቀባበል የምናደርሰው " ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ሞተ ወኬዶ ለሞት ለእለ ውስተ መቃብር ወሀበ ሕይወተ ዘለዓለም ዕረፍተ ⇝ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ሞቶ ሞትን አጠፋው በመቃብር ላሉ የዘላለም ዕረፍት የሚሆን ሕይወትን ሰጠ "

በሌሎች ምሥራቃውያን (Eastern ) እና ጽባሓውያን (Orientals) ዘንድም በእጅጉ የተለመደ ነው!

በግሪክ ፓስካል ትሮፓርዮን አልያም χριστος ανεστη የሚባል በዜማ የሚደርስና የዘመነ ሐዋርያት ጭምር ጥንታዊ መገለጫ አለው ተብሎ የሚታመን ነው።

Χριστὸς ἀνέστη ἐκ νεκρῶν,

θανάτῳ θάνατον πατήσας,

καὶ τοῖς ἐν τοῖς μνήμασι,

ζωὴν χαρισάμενος!

የንባባዊ ፍቺው አማርኛ ትየባ (transliteration) ደግሞ ይኽን ይመስላል!

ክርስቶስ አኔስቲ ኤክ ኔክሮኒ ፣ ታናቶ ታናቶን ፓቲሳስ፣ ኬቲስ ኤን ቲስ ሚ’መሲ፣ ዞይን ካሪዛሜኖስ

በትርጉሙም የእኛው " ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ሞተ ወኬዶ ለሞት ለእለ ውስተ መቃብር ወሀበ ሕይወተ ዘለዓለም ዕረፍተ ⇝ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ሞቶ ሞትን አጠፋው በመቃብር ላሉ የዘላለም ዕረፍት የሚሆን ሕይወትን ሰጠ " ካለው ጋር አቻ ፍቺ አለው

Christ is risen from the dead, Trampling down death by death, And upon those in the tombs, Bestowing life!

② #ቃለባሕዘትንሣኤ Paschal Greeting «የፋሲካ ሰላምታ»

በሓ ወይም ባሕ የሚባለው የሰላምታ የቡራኬ ቃል ፍሥሓ ሰላም የሚለውን የሚገልጥ ነው!

በቤተክርስቲያናችን አበው መምህራንም ቅድመ ቃለ እግዚአብሔር ፣ ድኅረ ቃለ ቡራኬ ለ፶ው ዕለት ከምእመናን ጋር የሚለዋወጡት ሰላምታ ነው! ከዚያም አልፎ ምእመናንም ከምእመናን ጋር የትንሳኤውን የምሥራች ለማብሰርና መልካም ምኞት ለመግለጥ ያውሉታል።

አቀራረቡ በአመላለስ አገባብ የሚከወን ሲሆን ሰላምታ ሰጪና ሰላምታ ተቀባይ ይኽን ይለዋወጣሉ፤

በኢትዮጵያዊቷ የተዋህዶ ቅድስት ቤተክርስቲያናችም ከ6ኛው ምዕተ ዓመት አንስቶ አገልግሎት ላይ መዋሉን መረጃዎች ይገልጣሉ። በቅዱስ ያሬድ ምዕራፍ (ዘመወድስ) ውስጥ በፍታሕ ሊተ ሥር በመሪና ተመሪ የሚቀርብ ዛሬ ለፋሲካ ሰላምታ የምንገለገልበት የትንሣኤው ምስክርነት ቃል አለ። እንዲህ ይላል ፦

☞ ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ፣ በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን ፣ አሠሮ ለሰይጣን ፣ አግዓዞ ለአዳም ፣ ሰላም ፣ እምይእዜሰ ፣ ይኩን ፣ ሰላም!
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፣ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ፣ ሰይጣንን አሠረው፣ አዳምን ነጻ አወጣው ፣ ሰላም፣ ከዛሬ ጀምሮ ፣ ይሁን ፣ ሰላም

በመቀባበል እንዲህ ተጽፏል

☞ Christ is risen from the dead!
☜ By the highest power and authority!
☞ He chained Satan!
☜ Freed Adam!
☞ Peace!
☜ Henceforth!
☞ Is!
☜ Joy and Peace!

☞ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን!
☜ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን!
☞ አሰሮ ለሰይጣን!
☜ አግዐዞ ለአዳም!
☞ ሰላም!
☜እምይእዜሰ!
☞ ኮነ!
☜ ፍስሐ ወሰላም!

ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ዲያብሎስን አሰረው አዳምን ነጻ አወጣው፤ሠላም ከዛሬ ጀምሮ ሰላም ሆነ.....
See more
@ABUNE_ABIB