Get Mystery Box with random crypto!

ቅበላ «ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ አሥሩ ቆነጃጅት» 'በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማያት መብራታቸው | አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)

ቅበላ «ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ አሥሩ ቆነጃጅት»


"በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ አሥር ቆነጃጅትን ትመስላለች።
ከእነርሱም አምስቱ ሰነፎች አምስቱም ልባሞች ነበሩ።
ሰነፎቹ መብራታቸውን ይዘው ከእነርሱ ጋር ዘይት አልያዙምና፤ ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር በማሰሮአቸው ዘይት ያዙ። ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ።እኩል ሌሊትም ሲሆን።

እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ሁካታ ሆነ።
በዚያን ጊዜ እነዚያ ቆነጃጅት ሁሉ ተነሡና መብራታቸውን አዘጋጁ። ሰነፎቹም ልባሞቹን መብራታችን ሊጠፋብን ነው፤ ከዘይታችሁ ስጡን አሉአቸው። ልባሞቹ ግን መልሰው። ምናልባት ለእኛና ለእናንተ ባይበቃስ፤ ይልቅስ ወደሚሸጡት ሄዳችሁ ለራሳችሁ ግዙ አሉአቸው።ሊገዙም በሄዱ ጊዜ ሙሽራው መጣ፥ ተዘጋጅተው የነበሩትም ከእርሱ ጋር ወደ ሰርግ ገቡ፥ ደጁም ተዘጋ።

በኋላም ደግሞ የቀሩቱ ቈነጃጅት መጡና። ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ፥ ክፈትልን አሉ። እርሱ ግን መልሶ። እውነት እላችኋለሁ፥ አላውቃችሁም አለ። ቀኒቱንና ሰዓቲቱን አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።"

{የማቴዎስ ወንጌል ፳፭÷ ፩-፲፫}
«እንኳን ለዓቢይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ! »