Get Mystery Box with random crypto!

ፍቄ ክራር ቲዩብ-Fike Kirar Tube

የቴሌግራም ቻናል አርማ aboutkirar — ፍቄ ክራር ቲዩብ-Fike Kirar Tube
የቴሌግራም ቻናል አርማ aboutkirar — ፍቄ ክራር ቲዩብ-Fike Kirar Tube
የሰርጥ አድራሻ: @aboutkirar
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.13K
የሰርጥ መግለጫ

መንፈሳዊ የክራር ትምህርት
.....ስለ ክራር ለማወቅ እና ክራር ለመማር/ለመለማመድ አሪፍ ቻናል ነው....እንዲሁም መዝሙሮችን በቁጥር እየለቀቅን እናስተምራለን.....
.
.
ከእርሶ የሚጠበቀው አሪፍ ክራር እጅዎ ላይ እንዲኖር ብቻ ነው....
.
.
እንዲሁም፡ ለክራር የሚያስፈልጉ ነገሮችን እንለቃለን.....
ሠላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን!!!
@aboutkirar...
ሊንኩን ሼር እናርግ

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-05 09:07:20 ​​ሱባዔ ለምን?
#ክፍል_ሁለት

የሰው ልጅ፤ ኃጢአት በሚስማማው የሥጋ ሰውነቱ ዘወትር ፈጣሪውን ይበድላል፡፡ በፈጸመው በደል ኅሊናው ይወቅሰዋል፤ ይጸጸታል፡፡ በመጀመሪያ ደፍሮ በሠራው ኃጢአት በኋላ ይደነግጣል፡፡ ይህ በማንኛውም ሰብአዊ ፍጥረት ኅሊና ውስጥ የሚፈራረቅ ክስተት ነው፡፡ በዚህ ጊዜ የፈጣሪውን ይቅርታ ለማግኘት ያስባል፤ ይተክዛል፡፡

በውስጡ ሰውነቴ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለኛል. ነገር ግን በብልቶቼ ባለ በኃጢአት ሕግ የሚማርከኝ ሌላ ሕግ አያለሁ፡፡ እኔ ምንኛ ጐስቋላ ሰው ነኝ ለዚህ ሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ያድነኛል? እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ፡፡ ሮሜ.7.22-25፡፡

ሰው በደፋርነቱ የኃያሉን አምላክ ትእዛዝ ተላልፎ ትካዜ ሽክም ሲያስጨንቀው ሸክሙን የሚያቃልልበትና የሚያስወግድበት መንፈሳዊ ጥበብ ከቸሩ ፈጣሪ ተሰጥቶታል፡፡ ይኸውም በጥቂት ድካመ ሥጋ ጸጋ እግዚአብሔር የሚያገኝበት ሥርዓት ሱባዔ ነው፡፡ ከጥንት እስከ ዛሬ አንድ ሰው በትካዜ ሽክም መንፈሱ ሲታወክ የነፍስና የሥጋ ጸጥታውን ለመመለስና ለማስከበር መጾምና መጸለይ ግድ ይሆንበታል፡፡ በዚህ ጊዜ አመክሮ /ሱባዔ/ ይገባል፡፡

እግዚአብሔርን ለመማፀን ሰው ሱባዔ ከሚገባባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች አንዱ እግዚአብሔርን ለመማፀን ነው፡፡ ማንኛውም ሰው ሱባዔ ሲገባ በቁርጥ ወደ ፈጣሪው የሚያቀርበው ተማኅፅኖ ሊኖረው ይገባል፡፡ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታና ዝግጅት ሱባዔ የሚገቡ ሰዎች ከሱባዔ በኋላ ምን እንደ ተመለሰላቸው የሚያውቁት ነገር ስለማይኖር ሱባዔ በመግባታቸው የሚያገኙት ነገር የለም፡፡

ስለዚህ ሱባዔ ከመግባታችን በፊት፡- ሱባዔ የምገባው ለምንድን ነው? በማለት ራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ ለምሳሌ አንድ ክርስቲያን በግል ሕይወቱ ዙሪያ ስለ ሀገር ሰላም፣ ስለ ጓደኛው ጤና ወዘተ ጉዳዮች ላይ ፈጣሪውን ይማፀናል፡፡ በዚህ ጊዜ በግል ሕይወቱም ሆነ በሀገር ጉዳይ ለገባው ሱባዔ ወዲያውኑ መልስ ሊያገኝ ይችላል፤ እንዲሁም መልሱ ሊዘገይ ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ከተሐራሚው ትዕግሥት /መታገሥ/ ይጠበቅበታል፤ «ለምን ላቀረብኩት ጥያቄ ቶሎ መልስ አልተሰጠኝ?» በማለት ማማረርና እግዚአብሔርን መፈታተን ተገቢ አይደለም፡፡

ለምሳሌ በጓደኛው ውድቀት ምክንያት ሱባዔ ገብቶ በአንድ ሳምንት ውስጥ መልስ ያገኘ የአንድ ገዳም አገልጋይ ታሪክ መመልከት ተገቢ ነው፡፡

አኃው ለተልእኮ በወጡበት አንዱን ድቀት አግኝቶት ያድሯል፡፡ በነጋው ወንድሜ እኔ ድቀት አግኝቶኛልና እንግዲህ ወዲህ ተመልሼ ከዚያ ገዳም አልሔድም፤ ሽለሙን መስዬ እኖራለሁ አለው፡፡እኔም እንዲሁ አግኝቶኛል፤ ይልቁንስ ሔደን ኃጢአታችንን ለመምህረ ንስሐችን ነግረን፤ ቀኖናችንን ተቀብለን እንደ ቀደመው ኾነን እንኖራለን ብሎ አጽናንቶ ይዞት ሔደ፡፡

ሔደው ለመምህረ ንስሐቸው ነግረው ቀኖናቸውን ተቀብለው 1 /አንድ/ ሱባዔ፣ ቀኖና እንዳደረሱ ሰረይኩ ለከ በእንተ ዘኢገብረ እኁከል፤ ኃጢአት ስላላደረገው ወንድምህ ይቅር ብዬሃለሁ የሚል ድምፅ አሰምቶታል፡፡ /ዜና አበው/፡፡

ከላይ ታሪካቸው የሰፈረው የገዳም አገልጋዮች ለአገልግሎት በተላኩበት አገር አንዱ ድቀት አግኝቶት በዝሙት ሲወድቅ ጓደኛው እንደ እርሱ ድቀት እንዳገኘው አድርጐ ጓደኛውን በማጽናናት ወደ ገዳም በመመለስ አንድነት ኾነው ሱባዔ ይገባሉ፡፡ አንድ ሱባዔ /ሰባት ቀን/ እንደ ጨረሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ኃጢአት ሳይሠራ ለአንተ ብሎ ሱባዔ ስለገባው ወንድምህ ስል ይቅር ብዬሃለሁ የሚል ፈጣን መልስ አግኝቷል፡፡

ስለዚህ ሱባዔ በግል ሕይወትም ሆነ በጓደኛችን ሕይወት ዙሪያ ስንገባ ፈጣን ወይም የዘገየ መልስ ሊሰጠን ስለሚችል በትዕግሥት መጠባበቅ ይኖርብናል፡፡

#ይቀጥላል
በቀጣይ ክፍል ሱባዔ ለመግባት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታና ዝግጅት?

ለእህት ወንድሞች ይማሩበት ዘንድ አጋሩ
@aboutkirar
@aboutkirar
@aboutkirar
2.0K viewsFike, 06:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 07:35:13 ​​ሱባዔና ሥርዓቱ
ቃለ እግዚአብሔር ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ Share ያድርጉ

ያለንበት ወቅት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ጾመ ፍልሰታን የሚጾሙበት ሱባዔ የሚገቡበት ወቅት ነው፡፡ ለዚህ ወቅት ምእመናን ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡ መልካም የሱባዔ ጊዜ ይሁንልን፡፡

ሱባዔ ምንድን ነው?

ሱባዔ በሰዋሰው ትርጉሙ ሰባት ማለት ነው፡፡ ሱባዔ በመንፈሳዊ አተረጓጎም አንድ ሰው ከዚህ ቀን እስከዚህ ቀን በጸሎት ከፈጣሪዬ እገናኛለሁ ብሎ የሚያቅደው መንፈሳዊ ዕቅድ ነው፡፡ ሰባት ቁጥር በእስራኤላውያን ዘንድ በሥራም በቃልም የሚገለጥ ፍጹም ቁጥር ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን ሥነ ፍጥረትን ከመፍጠር ማረፉ፣ ለጸሎት የሚተጉ ምእመናን በቀን ለሰባት ጊዜ ማመስገናቸው የሰባት ቁጥርን ፍጹምነት ያመለክታል፡፡ ዘፍ.2፥2፤ መዝ.118፥64፡፡

ከዚህ አንጻር አንድ ሰው ለሰባት ቀናት ቢጾም አንድ ሱባዔ ጾመ ይባላል፡፡ ለዐሥራ አራት ቀን ቢጾም ሁለት ሱባዔ ጾመ እያለ እየጨመረ ይሄዳል፡፡

ሱባዔ መቼ ተጀመረ?

ሱባዔ የተጀመረው ከውድቀት በኋላ በመጀመሪያው ሰው በአዳም ነው፡፡ ቅዱሳን መላእክት አዳምን ጸሎት መጸለይን እንዳስተማሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ መላእክት ለአዳም ጊዜያትን አስተምረውት ነበር፡፡ ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ፡፡ አዳም ጥፋቱን አምኖ ከባሕር ውስጥ ሱባዔ በመግባቱና በመጸለዩ እግዚአብሔር በማይታበል ቃሉ ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንኀለሁ ሲል ቃልን ገብቶለታል /መጽሐፈ ቀሌምንጦስ አንቀጽ አራት/፡፡

#ይቀጥላል ....
በቀጣይ ሱባዔ ምንድን ነው ጥቅሙ?

ለእህት ወንድሞች ይማሩበት ዘንድ አጋሩ
@aboutkirar
@aboutkirar
@aboutkirar
1.5K viewsFike, 04:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 02:51:19

2.0K viewsFike, 23:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 19:38:51 ክራር በኦንላይን (online)

ክራር በኦንላይን (online) መማር ለምትፈልጉ በሙሉ አሁኑኑ በዚህ ስልክ 09 33 34 59 72 ደውለው ይመዝገቡ...በሌላ አማራጭ በቴሌግራም @Fkirar ይመዝገቡ...

ከእናንተ የሚጠበቀው
1. ተስፋ አለመቁረጥ
2. ብቁ እንደምትሆኑ ማመን
3. የራሳችሁ ክራር ይኑራችሁ
4. በሰዓቱ መገኘት
5. በቀኑ ካልተመቻችሁ አስቀድሞ ማሳወቅ

ሌላውን ለፍቄ...ይመቻችሁ
3.0K viewsFike, 16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 07:35:43

2.9K viewsFike, 04:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 07:25:36
ሁላችሁም ሼር (share) አድርጉ
2.7K viewsFike, 04:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 18:23:35
ፖስት በማድረግ ተባበሩን
2.5K viewsFike, 15:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 18:34:44

2.4K viewsFike, 15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 16:52:09 ቅድስት ድንግል ማርያም ብቻ

ይህንን መልእክት SHARE የማያደርግ የማርያም ወዳጅ አይደለም !

1• አምላክን የወለደች-ማርያም ብቻ !

2• ከመውለዳ በፊትም ሆነ ኋላ ድንግል የሆነች - ማርያም ብቻ!

3• ከሰው ወገን ተለይታ መርገም ያልነካት - ማርያም ብቻ!

4•የእግዚአብሔር ሀገር ከተማ የተባለች - ማርያም ብቻ!

5• በድምጽዋ መንፈስ ቅዱስን የምትሞላ ንግስት- ማርያም ብቻ!

6• ጽንስ በማሕፀን የዘለለላት ብጽዕት - ማርያም ብቻ!

7• ያላፈውም የሚመጣውም ትውልድ የሚያመሰግናት - ማርያም ብቻ!

8• ጸሐይን ተጎናፅፋ ጨረቃን የተጫማች ልዩ እናት - ማርያም ብቻ!

9• በጌታ ሞት ያዘነውን ዓለም እንድታፅናና ጌታ የሰጠን ሥጦታችን - ማርያም ብቻ!

10• በስጋዋ፣ በነፍስዋና በሕሊናዋ በሶስት ወገን ድንግል የሆናች - ማርያም ብቻ!

11• ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ የሆነች - ማርያም ብቻ!

12• ከፍጥረት ሁሉ ተላይታ አምላኳን "ልጄ" የምትል - ማርያም ብቻ!

13• ፍቅርዋ በልቤ የሚቀጣጠል አማላጅነትዋን ነፍሴ የሚመሰክርላት እናቴ - ማርያም ብቻ!

14• ከሰው ወገን 'ቤዛዊተ ዓለም' የሚል የጸጋ ስም ያላት - ማርያም ብቻ!

15• በንጉሱ ቀኝ ቆማ የምትማልድ ንግስት - ቅድስት ድንግል ማርያም

16• ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን የሚላት - ማርያም ብቻ!

17• አባ ኤፍሬም ያወደሳት፣ አባ ሕርያቆስ ያመሰገናት፣ ቅ.ያሬድ የተቀኘላት እመቤት - ማርያም ብቻ!

18• ከሰው ወገን በስጋ ከሞት ተነስታ ያረገች ንጽሕት እናት - ማርያም ብቻ!

19• የመላእክት እህታቸው፣ የሰማዕታት አክሊላቸው፣ የመነኮሳት መመኪያቸው - ማርያም ብቻ!

20• ዘንዶው በሰው ልብ እንዳትቀረፅ ሊውጣት የሚፈልግ፣ ዘርዋንም ሊዋጋ የሚሻቸው ባለ ሁለት ክንፍ እመቤት - ማርያም ብቻ!

21• ጌታ ከፍጥረት ሁሉ ለይቶ "እናቴ" የሚላት - ማርያም ብቻ

ይሄን ሼር የማያደርግ የማርያም ወዳጅ አደለም
@aboutkirar
@aboutkirar
@aboutkirar
2.9K viewsFike, 13:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 11:43:45

2.2K viewsFike, 08:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ