Get Mystery Box with random crypto!

ስንት አይነት ክራር አለ? በመሰረቱ 3 የክራር አይነቶች አሉ...እነርሱም 1ኛ. ድርድር (ሊድ) | ፍቄ ክራር ቲዩብ-Fike Kirar Tube

ስንት አይነት ክራር አለ?

በመሰረቱ 3 የክራር አይነቶች አሉ...እነርሱም
1ኛ. ድርድር (ሊድ) ክራር
2ኛ. ግርፍ ክራር
3ኛ. ቤዝ ክራር

1ኛ. ድርድር (ሊድ) ክራር:- ይህን ክራር ለድርድርም ለግርፍም መጠቀም ይቻላል ይህ ክራር በተለምዶው ሁሉም ሰው እጅ ላይ የምናየው ነው...ምክንያቱም ለግርፍም ለድርደራም ስለሚጠቀሙበት ማለት ነው...ይህ ክራር በተለያዩ የድምፅ ሳጥኖች ሊሰራ ይችላል።
ለምሳሌ:-
ከእንጨት የሚሰራ ገበቴ (የድምፅ ሳጥን) ለምሳሌ-ከዋንዛ እንጨት
በጣም ትልቅ ከሆነ ቅል የሚሰራ ገበቴ (የድምፅ ሳጥን)
ከትልቅ ጎድጓዳ ሰሀን የሚሰራ ገበቴ (የድምፅ ሳጥን)
ከኮምፖርሳቶ (ስስ ጣውላ) የሚሰራ ገበቴ (የድምፅ ሳጥን)

ለዚህ የድርድር ክራር የምንጠቀማቸው የክር አይነቶች...የውሀ ክር(የአሳ ማጥመጃ ስትሪንግ string) ፣ የጫማ መስፊያ ጅማት እና የመሳሰሉት...እኔ የምመክረው ግን የውሀ ክር(የአሳ ማጥመጃ ስትሪንግ string) ነው። ዋጋው ቢበዛ 500 ነው...አነሰ ከተባለ ደግሞ ከ250-300ETB ነው። የሚገኝበት ቦታ ደግሞ አዲስ አበባ መርካቶ አይጠፋም። አልያም ደግም በናዝሬት (አዳማ) ከተማ ላይ ካሉት ABC tradings ውስጥ አለ።

2ኛ. ግርፍ ክራር :-ይህ ክራር አብዛኛው ሰው ሙሉ ለሙሉ ማለት በሚቻል ሁኔታ ለዘፈን ነው የሚጠቀመው። አብዛኛው የግርፍ ክራር ከቤዝ ክራር ጋር አሰራሩ ተመሳሳይ ነው። የሚያለያያቸው ነገር string (ክር) ነው።
አብዛኛው የመድረክ ግርፍ ክራር ተጫዋቾች የሚጠቀሙት የክር አይነት የሽቦ ስትሪንግ ነው። በሌሎች ክሮች መጠቀም ይቻላል። ነገር ግን በጣም የሚያምር ድምፅ የሚያወጣው የክሩ አይነት ሽቦ ሲሆን ነው።

3ኛ. ቤዝ ክራር:- ይህ ክራር ደግሞ በአይነቱም በድምፁም ከሁሉም ክራር ለየት ተደርጎ ነው የሚሰራው።
ድምፁ ከሌሎቹ ለየት ያለ ወፍራም እና የሚያምር ድምፅ ነው ያለው።
ይህ ክራር ጥቅሙ የሊዱን ክራር ወይም የድርድሩን ክራር ድምፅ ተከትሎ በወፍራም ድምፁ የእነዚህን ክራር ድምፅ ማሳመር ነው።
ይህ የክራር አይነት ሁለት አይነት አመታት አለው። እንደ ግርፍ ክራር በጭራሽ አይመታም።

1ኛው አመታት:- በግራ እጃችን ወደ መቃኛው አካባቢ ከፍ ብለን አምስቱ ጣቶቻችንን በስድስቱ ክሮች መካከል አስገብተን ፤ በቀኝ እጃችን ደግሞ ሶስቱ ጣቶቻችንን በመጠቀም እየደረደርን ከግራ እጃችን ጋር እያግባባን አንዳንድ ክር እየመታን እንጠቀመዋለን ማለት ነው። ይህ አመታት በዓለማዊም በመንፈሳዊም መጠቀም ይቻላል።

2ኛው አመታት:- ሁለተኛው አመታት ደግሞ ይህን ቤዝ ክራር ከሊድ (ከድርድር) ክራር ጋር አንድ ላይ ይዞ በመጫወት መምታት ነው።

@aboutkirar
@aboutkirar
@aboutkirar