Get Mystery Box with random crypto!

ወንጪ ሁሌም ንፁህ የተፈጥሮ ስጦታ ሆና ቆይታለች። የተፈጥሮን ድንቅ በረከት ተቀብሎ ተንከባክቦ እና | Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

ወንጪ ሁሌም ንፁህ የተፈጥሮ ስጦታ ሆና ቆይታለች። የተፈጥሮን ድንቅ በረከት ተቀብሎ ተንከባክቦ እና አበልፅጎ መጠቀም ደግሞ የኛ የሰውልጆች ተጠባቂ ተግባር ነው። የወንጪ ዳንዲ ኢኮ ቱሪዝም መንደርን በማልማት ሂደት በግንባታው ምዕራፍ ከ8,000 እስከ 12,000 ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል። ግዙፍ የመሰረተ ልማት ስራ ተሰርቷል። 43 ኪ.ሜትር መንገዶች፤ 35ኪ. ሜትር የመንገድ መብራት እና የኃይል አቅርቦት፤ 72 ሜትር ድልድይ እና ትምህርት ቤት ተጠቃሽ ናቸው። የአካባቢው ወጣቶች ታላላቅ የልማት ስራዎች ይዘው የሚመጡትን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማጣጣም ጀምረዋል። ሰፊው የአካባቢው ማኅበረሰብም አሁን የላቀ የተጠቃሚነት ዕድል አግኝቷል።

Wanchi has always existed as a pristine gift of nature. It is our duty though to receive nature’s blessing and add value. In the process of developing the Wanchi-Dandi Eco Tourism Village, between 8,000 to 12,000 jobs have been created during the construction phase. Massive infrastructure has been introduced including 43kms access roads, 35km of road lights and power supply, a 72mts long crossing bridge. Youth in the community are seizing the economic benefits of what such large scale development introduces and the community at large have now greater opportunities.