Get Mystery Box with random crypto!

በተለመደው መንገድ እየተጓዝን የሀገራችንን የኢኮኖሚና የቴክኖሎጂ አቅም ማሳደግ አዳጋች ነው። አዲስ | Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

በተለመደው መንገድ እየተጓዝን የሀገራችንን የኢኮኖሚና የቴክኖሎጂ አቅም ማሳደግ አዳጋች ነው። አዲስና ፈጠራ የታከለባቸው መንገዶችን መከተል ይኖርብናል። ዓለም በእጅጉ እየተቀየረ ነው። በቀድሞ አስተሳሰብ አዲሱን ዓለም ለመቀበል መሞከር ልጆቻችንን በሕጻንነታቸው ባዘልንበት ጫንቃችን በወጣትነታቸው ለማዘል እንደመሞከር ይቆጠራል።

እየገነባናቸው ያለት ነፃ የንግድ ቃጣናዎች በፍጥነት እየተለወጠ ወደሚገኘው ዓለም የምንቀላቀልባቸው መንገዶቻችን ናቸው። ዞኖቹ ንግድና ኢንቨስትመንትን ከማቀላጠፍ ባለፈ የቴክኖሎጂ አቅማችንን እንደሚያሳድጉ አልጠራጠርም።

Increasing the economic and technological capacity of our country while traveling in the same old way is a cumbersome journey. We need to follow new and innovative pathways. The world is changing exponentially. Trying to accept the new world with old thinking is considered as good as carrying our youth on our shoulders in the same way we carried them as children.

The Free Trade Zones we are building is one of our ways to integrate into a rapidly changing world. I have no doubt that the zones will not only facilitate trade and investment but also enhance our technological capabilities.