Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና በአዲስ አበባ ብቻ ከ20 ሺህ በላይ አማሮች አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ታፍሰው | አቢሲኒያ - Times

ሰበር ዜና

በአዲስ አበባ ብቻ ከ20 ሺህ በላይ አማሮች አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ታፍሰው መታሰራቸው ተገለፀ

ከተለያዮ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ከፈረንሳይ፣ሽሮሜዳ፣ልደታ፣አራት ኪሎ፣ፒያሳ እና በዋናነት ከቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ታፍሰው በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ የታሰሩት አማሮች እና የአዲስ አበባ ልጆች ቁጠር ከ20 ሺህ ማለፉን የውስጥ መረጃችን ገልጿል።

ጎተራ ማሳለጫ አካባቢ Obn ህንፃ ፊት ለፊት የኮሮና ማገገሚያ ተብሎ በተሰራው ባለ ቀይ ቀለም ህንፃ ውስጥ ብቻ በቁጥር ከ6 ሺህ በላይ አማሮች እና አዲስ አበቤዎች በኦህዴድ ሠራዊት ታፍሰው መታጎራቸው ታውቋል።በተጨማሪም በአባ ሳሙኤል፣በማዕከላዊ፣በቂሊንጦ፣በተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች እና መጋዘኖች ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ታስሯል ሲል የውስጥ ምንጫችን አሳውቋል።

የግፍ እስረኞች በአንድ ክፍል ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ በመታጨቃቸው ምክንያት ለወረርሽ ህመም መጋለጣቸው ታውቋል።የመፀዳጃ፣የሚጠጣም ሆነ የንፅህና መጠበቂያ ዉሃ ባለመኖሩ ለከፍተኛ ጉዳት ተጋልጠዋል ሲል የመረጃ ምንጫን አስረድቷል።

በአዲስ አበባ የእስረኞች ቁጥር ከአቅም በላይ መሆኑን ተከትሎ ወደ ሸዋሮቢት፣ሚዛን ቴቢ፣አዋሽ አርባና ወደ ሌሎች የግፍ እስር ቤቶች ሊያግዟቸው እንደሆነ ተገልጿል።ይህ ደግሞ የእስረኞችን ስቃይ ያበዛዋል ተብሏል።

ጋዜጠኞች፣ሙሁራን፣መምህራን፣የፖለቲካ ፓርቲ አባላት፣የሚዲያ ባለሙያዎች፣ቄሶች፣የታክሲና የሞተር አሽከርካሪዎች፣የበቁ እና የነቁ ንፁሃን የአዲስ አበባ ልጆች እና አማሮች ይገኙበታል።
#ሼር
@ሳተናው ሚድያ

@abisiniya_times