Get Mystery Box with random crypto!

ግርማ የሽጥላ በተፈፀመበት ጥቃት ህይዎቱ ማለፉ ተረጋገጠ ሰበር ዜና አቶ ግርማ የሺጥላ መሃል ሜ | አቢሲኒያ - Times

ግርማ የሽጥላ በተፈፀመበት ጥቃት ህይዎቱ ማለፉ ተረጋገጠ

ሰበር ዜና
አቶ ግርማ የሺጥላ መሃል ሜዳ ላይ በተፈጸመበት ጥቃት መገደሉ ተረጋገጠ።
(ኢትዮ 360 - ሚያዚያ 19/2015)የብአዴኑ ብልጽግና ጽህፈት ቤት ሃላፊ ግርማ የሺጥላ በጥይት ተደብድቦ መሃል ሜዳ ሆስፒታል ቢገባም በህይወት ሳይተርፍ መቅረቱን የኢትዮ 360 ምንጮች አረጋገጡ።
ጉዳቱ የደረሰው በሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ጌራ ምድር ወረዳ መሃል ሜዳ ከተማ ስብሰባ አድርገው በመመለስ ላይ ባሉበት ወቅት መሆኑንም ታውቋል።
ግርማ የሺጥላ በህይወት ስለመትረፉ በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም ብለው የነበሩት ምንጮቹ የዞኑ አስተዳዳሪን ጨምሮ አብረውት የነበሩት በሙሉ በህይወት ስለመትረፋቸውም በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም ብለዋል።
ጓሳ በምትባለው አካባቢ ዛሬ ከደቂቃዎች በፊት በተፈጸመው በዚህ ጥቃት በህይወት ላይተርፍ ይችላል የተባለውን ግርማ የሺጥላን ወደ ሌላ ሆስፒታል ለማዛወር ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም በህይወት ግን ሊተርፍ አለመቻሉን ገልጸዋል።
እስካሁን ግርማ የሺጥላ የተገደለው ከየትኛው ወገን በተፈጸመ ጥቃት መሆኑን ማወቅ እንዳልተቻለም ተናግረዋል።

@abisiniya_times