Get Mystery Box with random crypto!

የቀድሞው የሱዳን ፕሬዚዳንት ማምለጣቸው እየተዘገበ ነው። የሱዳኑ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኦማር ሐሰን | አቢሲኒያ - Times

የቀድሞው የሱዳን ፕሬዚዳንት ማምለጣቸው እየተዘገበ ነው።

የሱዳኑ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኦማር ሐሰን አልበሽር በእርስ ላይ ከሚገኙበት ኮብር ወህኒ ቤት ማምለጣቸውን ሱዳን ፖስት ዘግቧል። አልበሽር ከኮብር እስር ቤት እንዳመለጡ የፈጥኖ ደራሹ ጦሩም ዛሬ ይፋ አድርጓል። በሱዳኑ ቀውስ ማረሚያ ቤት የነበሩ አብዛኛዎቹ ታራሚዎች ማምለጣቸው እየተነገረ ነው።

አልበሽር ከእስር ቤት ቢያመልጡም፤ በጉልበታቸው ላይ ባደረጉት ቀዶ ጥገና ምክንያት በፍጥነት መሮጥ እንዳልቻሉም ተነግሯል። አንዳንድ ዘገባዎች ደግሞ የጄኔራል አልቡርሃን ጦር አስቀድሞ ወደሌላ ቦታ ወስዷቸዋል ይላሉ።

አልበሽር ስልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ በተጠረጠሩበት በሙስና ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ ሲሆን፤ ከዚህ በተጨማሪም እ.ኤ.አ. በ1989 ወደ ስልጣን ካመጣቸው መፈንቅለ መንግስት ጋር በተያያዘ፣ በዘር ማጥፋት እና በርካታ ተቃዋሚዎችን በመግደል ወንጀል ክስ ቀርቦባቸው ነበር።

ሁለት ዓመት ተፈርዶባቸው ከፍተኛ ጥበቃ ከሚደርግበት ኮብር እስር ቤት የነበሩ ቢሆንም፤ በሱዳን በተቀጣጠለው የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት የእስር ጊዜያቸውን ሳይጨርሱ ማምለጣቸው እየተነገረ ነው።

@abisiniya_times