Get Mystery Box with random crypto!

መልዕክታችን ውድ ወላጆች መምህራን እና የመማር ማስተማር ባለድርሻ አካላት በቅድሚያ የአክብሮት ሰ | ABG Weyra branch Grade1-8

መልዕክታችን
ውድ
ወላጆች መምህራን እና የመማር ማስተማር ባለድርሻ አካላት በቅድሚያ የአክብሮት ሰላምታችንን እያቀረብን የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ በአሁኑ ወቅት በሥሩ የሚገኙ 25 ቅርንጫፍ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ከ17 ሺህ በላይ ተማሪዎች የሚማሩ፣ ከ10 ሺህ በላይ ወላጆች ልጆቻችሁን በማስተማር ላይ መሆናችሁ ይታወቃል፡፡
የመማር ማስተማሩን ሂደት ለማሳለጥም በየቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ በተከፈቱ ቴሌግራም ቻናሎች መረጃ እንደምትለዋወጡ ይታወቃል፡፡ የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የህዝብ ግንኙነት አገልግሎትም እነዚህን ቴሌግራም ቻናሎች በመጠቀም በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሥራዎችን ለእናንተ ለማድረስ ቻናሎቹን በማስተሳሰር ላይ የሚገኝ በመሆኑ ሥራዎቻችንን እንድትከታተሉን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
ከአክብሮት ሰላምታ ጋር
የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ

ትውልድን የሚተካ ትውልድ በተሻለ ጥራት እናፈራለን!