Get Mystery Box with random crypto!

ABG Weyra branch Grade1-8

የቴሌግራም ቻናል አርማ abgwerabranchgrade1to8 — ABG Weyra branch Grade1-8 A
የቴሌግራም ቻናል አርማ abgwerabranchgrade1to8 — ABG Weyra branch Grade1-8
የሰርጥ አድራሻ: @abgwerabranchgrade1to8
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.02K

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-30 15:55:28
441 views12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 15:55:23
445 views12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 15:55:20
445 views12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 15:55:15
432 views12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 15:55:10
405 views12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 15:55:05
409 views12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 15:55:01 ዝክረ ቅዱስ ያሬድ በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለቡ ቅርንጫፍ በታላቅ ድምቀት ተከበረ፡፡
*************
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለቡ ቅርንጫፍ መምህራን እና ተማሪዎች ኢትዮጵያዊው ሊቁ ቅዱስ ያሬድ የተሰወረበትን ቀን በትምህርት ቤቱ በተዘጋጀ መርሐግብር ዘክረው ውለዋል፡፡
በ505 ዓ/ም የተወለደው ሊቁ ማኅሌታይ ቅዱስ ያሬድ አክሱም አካባቢ ከእናቱ ክርስቲና (ታኡክልያ) አባቱ ደግሞ ይስሐቅ (አብድዩ) እንደተወለደ የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ:: አንድ ቀን ግን መምህሩ የነገሩት ቀለም አልያዝህ አለው፣ ሲፈትኑትም ባለመመለሱ ተገረፈ:: ዱላው በጣም ስለ ተሰማው ቅዱሱ ከመምህሩ ኮብልሎ ማይ ኪራሕ አካባቢ ሲደርስ ደክሞት አርፎ እግዚአብሔር ትጋትንና ተስፋ አለመቁረጥን ከትል አስተማረው:: ትሏ ስድስት ጊዜ ወድቃ በሰባተኛው ፍሬዋን ስትበላት ተመልክቷልና:: ከዚህ በኋላ ቅዱስ ያሬድ ወደ መምህሩ ተመልሶ እና ይቅርታ ጠይቆ ትምህርት ጀመረ:: ሊቁም ትጋትንና ጸሎትን ከሰጊድ ጋር አበዛ:: እግዚአብሔርም በድንግል እናቱ አማካኝነት የምሥጢር ጽዋን አጠጣው:: እርሱም በጸሎት ላይ ሳለ ተደሞ መጣበት:: ሦስት መላእክት በሦስት ወፎች አምሳል መጥተው አነጋገሩት:: ድንገትም ነጥቀው ወደ ሰማያት ወደ ልዑላኑ መላእክት ዘንድ አደረሱት:: ሊቁ በሰማያት ልዩ ምሥጢር : ልዩ ምስጋናና ልዩ ዜማን አዳመጠ:: ይህንን ምስጋና ብዙ ቅዱሳን ቢሰሙትም ቅዱስ ያሬድ ግን ይዞት እንዲወርድ ተፈቀደለት::
ቅዱስ ያሬድ በሊቅነቱ ካበረከታቸው አምስት ያህል መጻሕፍትን በተጨማሪ በጣና ቂርቆስ፣: በዙር አምባና በሌሎችም ቦታዎች ወንበር ዘርግቶ ብዙ ደቀ መዛሙርትን ያፈራ ሊቅ ሲሆን በሰሜን ተራሮች አካባቢ በትጋሀ መላእክትና በተባሕትዎ እንደኖረም ይነገራል::
በተወለደ በ71 ዓመቱ ግንቦት 11 ቀን በ576 ዓ/ም እንደተሰወረ የሚነገረው ቅዱስ ያሬድን በዜማው በጥበቡ የሚዘክር መርሐ ግብር በተማሪዎች እና መምህራን በማቅረብ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለቡ ቅርንጫፍ ዘክረውታል::
430 views12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-26 14:31:57
መልዕክታችን
ውድ
ወላጆች መምህራን እና የመማር ማስተማር ባለድርሻ አካላት በቅድሚያ የአክብሮት ሰላምታችንን እያቀረብን የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ በአሁኑ ወቅት በሥሩ የሚገኙ 25 ቅርንጫፍ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ከ17 ሺህ በላይ ተማሪዎች የሚማሩ፣ ከ10 ሺህ በላይ ወላጆች ልጆቻችሁን በማስተማር ላይ መሆናችሁ ይታወቃል፡፡
የመማር ማስተማሩን ሂደት ለማሳለጥም በየቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ በተከፈቱ ቴሌግራም ቻናሎች መረጃ እንደምትለዋወጡ ይታወቃል፡፡ የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የህዝብ ግንኙነት አገልግሎትም እነዚህን ቴሌግራም ቻናሎች በመጠቀም በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሥራዎችን ለእናንተ ለማድረስ ቻናሎቹን በማስተሳሰር ላይ የሚገኝ በመሆኑ ሥራዎቻችንን እንድትከታተሉን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
ከአክብሮት ሰላምታ ጋር
የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ

ትውልድን የሚተካ ትውልድ በተሻለ ጥራት እናፈራለን!
717 views11:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 04:32:27
255 views01:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 16:30:50 ውድ ወላጆች እንደምን ሰነበታችሁ እያልን የፊታችን እሁድ በ24/07/2015 ዓ.ም የተማሪ ወላጆችና አሳዳጊዎች ስልጠና ስለሚሰጥ ከወዲሁ የተለየ መርሐ ግብር እንዳይዙ እናሳስባለን ።።።።።።።።።።።።። ት/ቤቱ
194 views13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ