Get Mystery Box with random crypto!

👉👉👉❤️❤️❤️❤️👈👈👈

የቴሌግራም ቻናል አርማ lover_times — 👉👉👉❤️❤️❤️❤️👈👈👈 L
የቴሌግራም ቻናል አርማ lover_times — 👉👉👉❤️❤️❤️❤️👈👈👈
የሰርጥ አድራሻ: @lover_times
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 309
የሰርጥ መግለጫ

ፍቅር ከቃል በላይ ነው
አዲሱን ግሩፕ ለመቀላቀል
👇👇👇👇👇👇👇
@LOVER_TIMES1
👆👆👆👆👆👆👆

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-14 01:38:02 #አስተማሪ_ታሪክ

ጥንዶቹ ከተጋቡ 11 ዓመታቸው ነው፡፡ ነገር ግን ልጅ ማግኘት አልቻሉም፡፡ በሰተመጨረሻ ግን ከ11 ዓመታት ጥበቃ በኋላ የልመናቸውን ፍሬ ወንድ ልጅ ተበረከተላቸው፡፡ ልጁ ከእነሱ አልፎ የቤተ ዘመዱ ሁሉ ዓይን ማረፊያ ሆነ፡፡ ደስታ እና ፌሽታ ከእዚ ህፃን ጋር አብረው ወደ ጥንዶቹ ጎጆ ብቅ አሉ፡፡ ይህ ፃና 2 ዓመት ሆነው፡፡

ከዕለታት አንድ ቀን ጠዋት ባል ስራ እረፍዶበት እየተጣደፈ ሳለ እናት ከምትወስደው መዳኒት አንዱ ክዳኑ ተከፍቶ ሳሎን ጠረጴዛ ላይ ከእነ ብልቃጡ ተቀምጦ ተመለከተ፡፡ እና እንድታነሳውና ከድና ህፃኑ የማያገኘው ቦታ እንድታስቀምጠው ነግሯት ወደ ስራ ሄደ፡፡

እናት ብዙ ስራዎች ነበሯትና ስትሯሯጥ ጠረጴዛ ላይ ያለውን መድኃኒት ዘነጋችው፡፡ ትዝ እንዳላት ለማንሳት ወደ ሳሎን እሮጠች፤ ነገር ግን መድኃኒቱ የለም፡፡ ልቧ ለሁለት ተሰነጠቀ፡፡ ወዲያውኑ ልጇን ስትመለከት ከሶፋው ስር ወድቆ አራፈ ይደፍቃል፡፡ ቤቱን በእሪታ አቀለጠችው፡፡ ተጣድፈው ወደ ሃኪም ቤት ወሰዱት፡፡ ነገር ግን ከሚባለዉ በላይ እረፍዷል፡፡ ህፃኑ ድቡልቡሎቹን እንክብሎች እንደከረሚላ እያሰበ በሙሉ ውጧቸዋል፡፡ እናም እንኳን የ2 ዓመት ልጅ አዋቂም በማይችለው መልኩ ከመጠን በላይ መድኃኒት ጨጓራው ላይ በማረፉ ከ11 ዓመት ጥበቃ በኀላ በቤተ ዘመድ ፀሎት የመጣው ጨቅላ ገና ዳዴን እንኳን በቅጡ ሳይጨርስ ላይመለስ አሸለበ፡፡

እናት ዕብድ ሆናለች፤ ገና ደሞ ጠዋት ላይ እንድታነሳው አስጠንቅቋት የወጣው ባል ሲሰማ ምን እንደሚላት ስታስብ አእምሮዋ ተዛባ፡፡ ጠዋት ሰላም ዋሉ ብሎ በደስታ ቤተሰቦቹን ተሰናብቶ የወጣው ባል ሆስፒታል እንዴት እንደደረሰ አያውቀውም፡፡ ሚስቱን ጨምሮ ዘመድ አዝማዱ ሲያለቅስ ውድ ልጁን እንዳጣ መንፈሱ ነገረው፤ ትንፋሽ ሳያወጣ እንባ ልክ እንደተከፈተ ቧንቧ በአይኖቹ ግራና ቀኝ ያለማቋረጥ መውረድ ጀመሩ፡፡

ወደ ሚስት ተጠጋ፤ ሚስት "ይቅርታ" በሚል አስተያየት በቀጣይ ከባል አንደበት የሚወጡትን ቃላት ለመስማት መጠበቅ ጀመረች፡፡ "አንቺ ነሽ ልጄን የገደልሽው" ይለኛል ብላ ጠበቀች፡፡ ባል ግን አንዲት ቃል ሳይተነፍስ አቅፏት ማልቀስ ጀመረ፡፡ ቀጠለና ውዴ "አይዞሽ እናቴ፤ እንግዲህ የፈጣሪ ፈቃድ ነው የሆነው" በማለት ሊያፅናናት ሞከር፡፡

እናት ፈፅሞ ያልጠበቀችውን ነገር በመስማቷ ጉልበት ሆናት፡፡ አዎ ይቺ እናት በዚህ ሰዓት የሚያስፈልጋት ወቀሳ፣ ለምን እንዲህ አላደረግሽም? የሚል ቁጣ ሳይሆን ብርታት የሚሆኗት የማፅናኛ ቃላት፣ እንባዋን የሚጠርጉ እጆች ናቸው፡፡ ምክንያቱም ለክ እንደ ባል እሷም ያጣችው አንድ ልጇን ነው፡፡

በተጨማሪ ደሞ ለልጁ ሞት ከእሷ ባልተናነሰ ባልም ተጠያቂ ነው፡፡ መድኃኒቱን እንደተመለከተ ከማዘዝ ይልቅ እራሱ አንሰቶ ከድኖ ማስቀመጥ ይችል ነበር፡፡ አሁን ላይ አንቺ ነሽ፤ አንተ ነህ መባባሉ ህፃኑን አይመልሰውም፡፡ ነገር ግን በሕይወት ያሉትን ሰዎች ስሜት ይጎዳል እንጂ፡፡

በእኛ ህይወትም ሁሌ እንዲህ አይነት ሁነቶች ይፈጠራሉ፡፡ ነገር ግን ተጎጂ ሁለታችንም ሆነን ሳለ፤ ያጠፋነው ሁለታችንም ሆነን ሳለ ጣቶቻችንን ወደ ሌሎች ለመቀሰር እንወዳለን፡፡

"ምላስ አጥንት የለውም ግን ሰዎችን ይወጋል"

እኔነቴ ከሚለው የጳውሎስ መፀሐፍ የተቀነጨበ
#Pawlos
https://t.me/Loveerdey
#የጳውሎስ_መጣጥፎች
https://t.me/Arte_Pawlos
33 views K I N G , 22:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 13:07:41 ............ " ከዛፉ ተማሩ " ..............

ሰውየው በቤቱ አንድ ትልቅ ዛፍ ነበረው አሉ፤ ይህ ዛፍ ህልውናው እንደትንጠለጠለበት ሁላ በእጅጉ ይንከባከበው ነበር። በቀን በቀን፤ ሲመሽም ሲነጋም ወደ ዛፉ እየሄደ ምርጥ ጊዜ ያሳልፋል። ከእለታት አንድ ቀን ግን፤ ይህን ግዙፍ ዛፍ ትክ ብሎ ሲመለከተው አንዳንድ ቅጠሎቹ ቀለማቸውን እየቀየሩ እየጠወለጉ መምጣታቸውን ተመለከተ፤ ሰውየው ሃዘን ገባው። ምንም እንኳን ዛፉ ትልቅ እና ግዙፍ ቢሆንም፤ እንደምንም ከዛፉ እላይ እየወጣ፤ የጠወለጉትን ቅጠሎች በውሃ ማራሱን ተያያዘው። ተመልሰው ነፍስ እስኪዝሩ ድረስ፤ ሽቅብ ወደ ላይ እየወጣ ቅጠሎቹን እየወለወለ በውሃ ያርሳቸዋል። ለብዙ ቀን እንዲህ ሲለፋ ቆየ፤ ምንም እንኳን የተቻለውን ያህል ቢለፋም ቅጠሎቹ አንድ በአንድ ከመድረቅ እና ከመጠውለግ አልዳኑም። በመጨረሻ ሰውየው ከልፋቱ ብዛት ደከመው፤ የነበረውም ውሃ በሙሉ አለቀበት። ቀስ በቀስ ዛፉ መሞት ጀመረ……..
ይህ ሰው ሃይል እና ጉልበቱን እንዲሁም ሃብቱን በከንቱ አባከነው። የዛፉን ስር ውሃ እንደማጠጣት፤ የጠወለጉት ቅጠሎች ላይ ጊዜውን በማጥፋቱ፤ ዛፉን በሙሉ አበላሸው። ምን አልባት ብልህ ሆኖ ስሩን በውሃ ቢያርሰው ኖሮ፤ የጠወለጉት ቅጠሎች መልሰው ባበቡ፤ ሌሎችም ከመጠውለግ በዳኑ ነበር።
አብዛኛዎቻችን እንዲህ ነን፤ ሕይወታችን መታደግ የሚያቅተን፤ ትኩረታችን ሁሉ፤ ስራችን ላይ ሳይሆን ቅጠላችን ላይ ስለሆነ ነው። ቅጠሎቻችን ምንድን ናቸው? ባህሪያችን፣ ልምዳችን፣ ስርዓታችን፣ ተግባራችን ወይም ሌሎች የአስተሳሰባችን ውጤት የሆኑ ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ። ስራችን ግን ማንነታችን የሚበቅልበት አስተሳሰባችን ነው። ባህሪዎቻችን ወይም ተግባሮቻችን ሲጠወልጉ ስራችንን እንደማስተካከል ጊዜ እና ጉልበታችንን ለውጥ በማያመጡ ነገሮች ላይ እናጠፋለን። ወገን እናስተውል።

#አስተሳሰብና #አመለካከታችን ላይ መስራቱ ቢቀድም በጎ ነው፤አለዚያ ከፈረሱ ጋሪው ቀደመ ይሆናል ነገሩ !!!!!!!!

#Pawlos
https://t.me/Loveerdey
#የጳውሎስ_መጣጥፎች
https://t.me/Arte_Pawlos
47 viewsሜሔሎኒ, 10:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 10:49:20 #ጠንቋዮ

"አሻግረን የምናየውን ነገር ሁሉ አቅርበን እኔ ብሆን ኖሮስ ብለን ልናጤነው ይገባል"
ፈገግ ብለው ትምህርት የሚያገኙበት ድንቅ ወግ

https://t.me/Loveerdey
#የጳውሎስ_መጣጥፎች
https://t.me/Arte_Pawlos
42 views K I N G , 07:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 23:33:30 #ዛሬ_የቆሸሸው_ነገ_ታጥቦ_ይጠራልና_ቆሻሻውን_እንጂ_ልብሱን_አትጥላው

እስኪ አንድ ነገር ልጠይቃችሁ መልሱልኝ? አንድ ቡቲክ ገብታችሁ በጣም የሚያምረውን እና ውድ የሆነውን ልብስ ገዝታችሁ ወጣችሁ… ከዛም ለቀናት ለበሳችሁት በጣም ቆሸሸ… ያ የሚያምረውና የምትወዱት ልብስ አሁን ከማስጠላቱ የተነሳ እንኳን ለመልበስ በእጃቹሁ ለመንካት ቀፈፋችሁ እና ስንት ከፍላችሁ የገዛችሁትን ልብስ በመቆሸሹ ብቻ ትጥሉታላችሁ? ታቃጥሉታላችሁ? መቼም አዎ የሚለኝ አይኖርም፡፡

የሰው ልጅም እንደዚሁ ልብስ መጀመሪያ ላይ ፈጣሪ በውድ ዋጋ ፈቅዶና ወዶ ነው የሰጠው። ልብሱም ንፁህ የሆነው ስብዕናው ነው፡፡ ከዛ ወደዚች ክፉ ዓለም ሲመጣ አእምሮውም ሆነ ልቡ ቆሸሸ፡፡ ነገር ግን ሰውም ልክ እንደቆሸሸው ልብስ አስተሳሰቡና ተግባሩ ታጥቦ መፅዳት ይችላልና በሰዎች ላይ ተስፋ አንቁረጥ፡፡

በሱስ የተጠመደ ጓደኛ ካለክ ወንድሜ የተጠናወተውን ሱስ እንጂ ጓደኛክን አትጥላው፤ ምክንያቱም በአንድ ወቅት እሱም እንዳንተ እንከን የማይወጣለት ሰው ነበረና፡፡

ክፋት በልቡ ላይ ነገሶ በሰዎች ላይ መጥፎን የሚያደርግ ወዳጅ ካለክ ተግባሩን እንጂ እሱን አትጥላው፡፡ ጥላቻ እኮ የክፋት አንዱ አካል ነው። ክፉ የሚሰሩ ሰዎችን ከጠላን እኛ ከእነሱ በምን ተለየን? በልብ ያደረ ጥላቻ ነገ መጥፎ ተግባርን ይወልዳልና እንጠንቀቅ፡፡

ቀና ቀናውን እናስብ… መልካም መልካሙን እንናገር…

ይቀላቀሉን


#Pawlos
https://t.me/Loveerdey
#የጳውሎስ_መጣጥፎች
https://t.me/Arte_Pawlos
53 views K I N G , 20:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 19:42:53 የህይወት እውነታ

#ሁሉንም ሰው ልታስደስት አትችልም፡፡ ይህ ትልቅ እውነታ ነዉ፡፡

#የሆኑ ሰዎች ቢጠሉህ ምንም ማለት አይደለም፡፡ #የሚወዱህ እንዳሉ ሁሉ የሚጠሉህም እንደዚያው መብዛታቸው አይቀርም፡፡ #ሰዎች ስላንተ ያላቸው አመለካከት ያንተ ጉዳይ አይደለም፡፡

#የመሰላቸውን ያህል ሊገምቱ ፣ ዋጋ ሊያወጡ ሊያወርዱ ፣ ወይም ሊሰቅሉ ይችላሉ፡፡

#ሰዎች አንተ ላይ ባላቸው #አመለካከት ማንነትህን እያመቅክ እና ቀዝቀዝ እያደረክ አትኑር...

#ራስህን ሆነህ በሕይወትህ ትልቅ ዋጋ ለምትሰጣቸው ሰዎች ብቻ የሚጠበቅብህን መስዋእትነት ክፈል ፡፡

#Pawlos
https://t.me/Loveerdey
61 viewsጥቁር ሰው, 16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 11:31:53
ሳትሰስች ስጪ!!

ማታ ለመኝታ አልጋ ላይ ስትወጪ
ለሊቱ እንዲሰምር ሳትሰስች ስጪ
ጥዋት እንደነጋ ሳትወርጂ ከአልጋ
ደግመሽ መስጠትሽ እንዳይዘነጋ
ሻወር ቤትም ቢሆንም ኩሽና ስትገቢ
ካንጀትሽ ለግሽው ሳትንገበገቢ
ከዋልሽበት ቦታ በሰላም ስትመጪ
በርከክ በይና ጎንበስ ብለሽ ስጪ
ቀናትን ሳትመርጪ ሰኞ አርብ ሳትይ
ሰባቱንም ቀናት ለሱ አትከልክይ
ሕይወትሽ እንዲያምር ኑሮሽ እንዲቃና
ለአምላክ ምስጋና ይገባዋልና።

@KING_SGL
#ጳውሎስ
https://t.me/Arte_Pawlos
75 viewsሜሔሎኒ, 08:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 13:24:49 ልጄ ሆይ ወዳጅ ማለት ሰው አይምሰልህ። ነገር ግን ወዳጅ ማለት ጊዜ ነዉና በጊዜህ ሁሉ ይወድሃል አለ ጊዜህ ግን ወዳጅህ እንኳን ይጠላሃል። ጊዜ ማለትም ቀንና ሌሊት አይምሰልህ። ነገር ግን ጊዜ ማለት የእግዚአብሔር አሳብ የሚፈፀምበት ነው ስለዚህ በሆነውም በሚሆነውም ነገር ሁሉ የእግዚአብሔር ፍቃድ ይሁን እያልህ ተቀመጥ።

#ጳውሎስ
ሰው ምንድነው ከሚለው መፀሐፍ የተወሰደ
ከ #የጳውሎስ_መጣጥፎች የተወሰደ
https://t.me/Loveerdey
80 views K I N G , 10:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 23:25:55
አንድ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ቆመና "ጌታ ሆይ ተመልከት እጆቼ ንፁሃን ናቸው። ደም አላፈሰሱም የሰው ገንዘብ አልቀሙም" አለ እግዚአብሔርም መለሰለት "ልጄ ሆይ! አዎ እጆችህ ንፁሃን ናቸው ግን ባዶዎች ናቸው" አለው ይባላል።

ያልገደለ እጅ ግን ያላዳነ፣ ያልሰረቀ አጅ ግን ያልመፀወተ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ የለውም። እውነተኛው መልካምነት ክፋ አለማድረግ ብቻ ሳይሆን መልካም ማድረግም ነው። የሚጎዳንን መተው ብቻ ሳይሆን ስለ ሌሎች ጥቅም መድከምም ነው።
ዘወትር የላቁ ምክሮችን ለማግኘት ሰማያዊውን ነክታችሁ ተቀላቀሉ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ

https://t.me/Loveerdey
#የጳውሎስ_መጣጥፎች
https://t.me/Arte_Pawlos
108 views K I N G , 20:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 14:03:47 ​​​​# በህይወትህ ትግስተኛ መሆን
ከቻልክ የምትፈልጋቸው ነገሮች
በሙሉ ግዜያቸውን እየጠበቁ
ወዳንተ ይመጣሉ!

በፍቅር አለም ውስጥም ትልቁን
ዋጋ ሚያስከፍለው ትግስት ነው
መታገስ ይከብዳል፤

ያ' ግዜ ሲያልፍ ግን ምንፈልገውን
እናገኛለን መራራውን ግዜ አልፈህ
ጣፋጩን ፍሬ ትበላ ዘንድ ታጋሽ ሁን።

#Pawlos
ከ #የጳውሎስ_መጣጥፎች የተወሰደ
https://t.me/Loveerdey
94 views K I N G , 11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 16:04:11
ይቅርታ መጠየቅ ቀላል አይደለም፤ ተበድሎ ይቅር ማለት ግን ይበልጥ ይከብዳል። በድለን መርሳቱ ላይከብደን ይችላል፤ ተበድለን መርሳት መቻል ግን ጥንካሬን ይሻል። እየተጠሉ መወደድ፤ እየተዋረዱ ክብር መስጠት፤ እየተገፉ አለሁኝ ማለት፤ ጠንካራ ማንነትን ይጠይቃል

#Pawlos
ከ #የጳውሎስ_መጣጥፎች የተወሰደ
https://t.me/Loveerdey
100 views K I N G , 13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ