2022-04-05 23:05:19
ክፍል አንድ
ሙስሊሙ ዝሙት ላይ መውደቁን የሚጠቁሙ ነገሮች
በተለይ በረመዷን ምሽቶች የተስተዋሉ የሙስሊም ልጆች ልቅነት።
ምንም እንኳን በረመዷን ምሽቶች የፆመኞች ትኩረት ወደ መስጂድና ተራዊሕ ቢሆንም ግና የብዙ አዳጊ ልጆች (በተለይ ከ10 ዓመት ጀምሮ ያሉ ሴቶች እና ወንዶች ትኩረታቸው መስጂድ ላይ አልነበረም፤ ይልቁንም የረመዷን ሌሊቶች በተለይ ለአዳጊዎች ከተቃራኒ ፆታ ጓደኞቻቸው ጋር በነፃነት የሚገናኙበት ወር ሆኖላቸው አርፏል፡፡ የዚህ አብይ ምክንያትም ልጆቹ ለተራዊሕ በሚል ከቤተሰብ ፈቃድ ስለሚሰጣቸው፣ ብሎም ከወላጆቻቸው ጋር ይልቅ ከጓደኞቻቸው ጋር እንዲሄዱ ስለሚፈቀድ በዚህም አጋጣሚ ልጆቹ ልቅ በመሆን በርካታ ድብቅ ገመናዎቻቸውን ይፋ አውጥተዋል፡፡ ይህም አጋጣሚ የአዳጊዎችን እምቅ የመበላሸት ችሎታቸውን ገላልጦ ያሳየን የማንቂያ ደውል ነበር፡፡ ወሩ የተከበረ የመሆኑን ያህል የመጪው ትውልድ ገመናን ልንማርበት አልያም ችላ ካልነው መቀመቅ ልንወርድበት፣ ብሎም በቁም ልንቀበርበት ዘንድ ልቅነታችንን ቁልጭ አድርጎ አሳይቶናል፡፡ በዚህ አጋጣሚ አንድ የቁርኣን አንቀጽ ትዝ ይለኛል፡፡
አላህ (ሱብሃነ ወተዓላ) እንዲህ ይላል
Surah At-Taubah 115
وَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِيُضِلَّ قَوْمًۢا بَعْدَ إِذْ هَدَىٰهُمْ حَتَّىٰ يُبَيِّنَ لَهُم مَّا يَتَّقُونَ إِنَّ ٱللَّهَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌ
አላህም ሕዝቦችን ከአቀናቸው በኋላ የሚጠነቀቁትን (ሥራ)ለእነሱ እስከሚገልጸላቸው(እስከሚተውትም) ድረስ ጥፋተኛ የሚያደርግ አይደለም፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነውና፡፡
ይህ አንቀጽ ከባድ መልዕክት አለው፡፡
የአዳጊዎቻችን ድብቅ ገመና ጋር ትልቅ ትስስር አለው፡፡ በተለይ ወላጆች ያሉበትን ሁኔታ ያሳየ ነበር፡፡ ምናልባትም አላህ(ሱብሃነ ወተዓላ)በዚያ በተከበረው ወር ይህንን ዘግናኝ ድብቅ ገመናችንን ያሳየን ጥፋተኛ አድርጎ ከማያዙ በፊት ማስጠንቀቂያን ሊሰጠን ሽቶ ይሆናል፤ ምክንያቱም አላህ(ﷻ)ሕዝቦችን ቅናቻውን መንገድ ከመራቸው በኋላ ጥፋተኛ ሳያደርጋቸው በፊት ትምህርት የሚወስዱበትን ነገር(ማስጠንቀቂያን)አስቀድሞ በግልጽ ያሳያቸዋልና፡፡ በውነቱ የባለፈው ረመዷን የአዳጊዎቻችን ገመና ትምህርት ከወሰድንበት ትልቅ ማስጠንቀቂያና የማንቂያ ደውል ነበር፡፡ አዎን! አዳጊዎች ማታ ማታ በተራዊሕ ስም ከቤት ይወጡና ከዚያም በዚህ ዕድሜያቸው ወደ መስጊድ ከማቅናት ይልቅ በየጥጋጥጉ ተያይዘው ሲቀመጡ፣ ውስጥ ለውስጥ ተቃቅፈው ሲዞሩ፣ ሲገባበዙና አብረው ሲያመሹ ተስተውሏል፡፡ በርካታ ሙስሊሞችም ይህን አሳፋሪ ትዕይንት በዓይናቸው አይተዋል፡፡ የበርካታ መስጂድ ኮሚቴዎችም በተደጋጋሚ ሴት ልጆቻችሁን ብቻቸውን አትልቀቁ እያሉ ወላጆችን አስጠንቅቀዋል፡፡ የወላጆች እንዝላልነት ግን ሥር የሰደደ ስለሆነ ይህንን ማስጠንቀቂያ ከመጠየፍም የቆጠሩ አይመስሉም፡፡ በተለይም ለእናቶች ሴት ልጆቻችሁን እጃቸውን ይዛችሁ እንጂ ወደ መስጂድ አትምጡ ብሎ ኢማሙ በቁጣ ተናግሯል።
«እንደውም ብልግናው እንዲህ ከተንሰራፋ ሴቶች ከቤት ባይመጡ ይሻላል» ሲሉ አስተያየት ሰጥተው ነበር፡፡ የመስጂድ ኮሚቴዎች በበኩላቸው «ሴት ልጆች ከእናቶቻቸው ጋር ካልመጡ አናስገባቸውም» ሲሉ መመሪያ ሁሉ ለማውጣት ተገደው ነበር፡
እነዚህ ለናሙና የተጠቀሱ ናቸው እንጂ በርካታ መስጊዶችም ተመሳሳይ ማስጠንቀቂያዎችን ሰጥተዋል፡፡ ወላጆችም ቢሰሙም ተግባራዊ አላደረጉትም፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ አንድ በሙያው መምህር የሆነ ወንድማችን የዘመኑን ወላጆችና የልጆችን ግንኙነት አስመልክቶ የታዘበውን ነገር ሲናገር እንዲህ ይላል
«አሁን አሁን ወላጆች ከልጆቻቸው እየፈሩ ይገኛሉ፡፡ ልጆቻቸውን ከማዘዝ ይልቅ ለነርሱ መታዘዝ ይቀናቸዋል፡፡
በተለይም እነዚያ ውጭ ሄደው ገንዘብ የሚልኩ ልጆች የወላጆችን ሥልጣን ተቀናቅነዋል፡፡ እነርሱ ከዚያ እየደወሉ ስለሚያዙ ወላጆች በዚህ ዓይነት ሁኔታ ያዳበሩትን ባህሪ በሌሎች ልጆቻቸው ላይም ይደግሙታል፡፡
ሀገር ቤት ያለው ልጅም ቢሆን ትንሽ ገንዘብ አምጥቶ ዱዓ ካስደረገ በቃ ወላጆች በርሱ ትዕዛዝ ሥር ይሆኑና ሐቁም ይረሳል፡፡ በተለይ ሴቷ ለወላጆቿ ብር ካመጣች ቤተሰብ በሙሉ በርሷ ተጽዕኖ ሥር ይወድቃል፡፡ ለምን እንደዚህ እንዳልኩ ታውቃላችሁ? ሴቷ ከጓዳ ጀምሮ፣ ኩሺናውን እካሎ መላውን ግቢ ለመቆጣጠር ትፈልጋለች፡፡ ወንዱ ግን ምናልባትም ሳሎን ቤቱንና ግቢውን ለመቆጣጠር ቢፈልግ እንጂ ወደ ኩሺና አይዘልቅም፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ የወላጆች የማዘዝ ወኔያቸው ስለሚሟሽሽ ልጆቻቸውን ለማዘዝ ይሳናቸዋል፡፡ ሌላው ደግሞ ልጆች ተምረዋል ብለው ስለሚያስቡ የተማረ ሁሉ ጨዋና የማይባልግ ይመስላቸዋል፡፡ ከዚህም የተነሳ ወላጆች በልጆቻቸው ላይ የሚያሳድሩት አሻራ ተዳፍኖ ወደመቅረቱ እያቀና ነው፤ አላህ ይጠብቀን እንጂ፡፡»
የመጨረሻው ክፍል
ይ ቀ ጥ ላ ል
እራስ ወዳድ ካልሆኑ መልዕክቱን ሼር ያድርጉት በምታውቋቸው ግሩፖች ሼር ያድርጉ በውስጥ መስመርም ለሁሉም ጓደኞቻችን እንላክላቸው።
ሃላፊነት አለብን! ምን አልባትም የአንድ ሰው ወደ አላህ የመመለስ ሰበብ ልንሆን እንችላለን።
ለመልካም ነገር እንሽቀዳደም
ባረከላሁ ፊኩም
ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር
ሼር ሼር ሼር ሼር
ሼር ሼር ሼር
ይህ ባጭር ግዜ ውስጥ ተወዳጅነት ያተረፈውን የቴሌግራም ቻናላችን ነው። አልሃምዱሊላህ የአላህ ፍቃድ ሆኖ በምናቀርባቸው ፁሁፎች ብዙዎች ተጠቅመውባቸዋል እናንተም ትቀላቀሉን ትጠቀሙበታላችሁ በአላህ ፍቃድ።
1.3K viewsAbdu ( ነጃሺ ማርኬት), edited 20:05