#እንደ_ስሙ_አንዋር ብዕሬን ሸክፌ ሀሳብ አጠንፍፌ ቃላት አጣልፌ ሄድኩኝ ከወረቀት: ቅኔ ልደረድር ግጥሜን ልሰድር ከመድብሌ ልከት! አንዋርዬ ስላንተ በቀን አንድ ግጥም ሳልከትብ ከዋልኩኝ: ምኑን ባለቅኔ ጎበዝ የብዕር ሰው ገጣሚ ተባልኩኝ: ወንድም ብዬ ጀመርኩ ጀምሬ ላልጨርስ ወንድም ሲመርቀኝ ይሁን አሁን ሲለኝ ጨርቄን ዘረጋሁኝ ቃሉ እንዲያበሽረኝ: ይሁን ያለኝ ጊዜ የያዘኝ በሽታ በቱፍታው ቀለለኝ። ስሙ አንዋር ነው አንዋሩ የሚያበራ: ለወንድም አዛኝ ነው ልቡ የሚራራ: ከክፉ የሚጠብቅ ልክ እንደ ተራራ: ትስስርም የለን በደም በአጥንት: የሌለን ዝምድና በእናትም በአባት: ዲን ነው ያስተሳሰረን የአኺራ ወንድምነት: ከጥቅም የነፃ ከወረተኝነት: ጀሊሉ ያስተሳሰረን በሙሀባ አጥር: ጣእሙ ልዩ ነው ለወንድም የመኖር: መውደዴን ለመግለፅ ቃላቶች ባይችሉም: ፍቅሬን መግለፅ ግን በፍፁም አላቆምም። እንግዲህ ጀሊሉ ዱኣ ያደረግንበት ትልቅ ሃጃ ወጣ: የሚነጥቀን ሂዶ የሚሰጠን መጣ። አብዱ ኤምሬ @abduftsemier @abduftsemier 1.1K viewsAbdu Emre (አብዱ ኤምሬ), edited 20:07