Get Mystery Box with random crypto!

#ሱንና ሱንና ከቁርአን ቀጥሎ የኢስላም ሁለተኛው ምንጭ ነው። ነገሮችን በመፍቀድ እና በመከልከ | Abdu ft hasu 🎤🎤

#ሱንና

ሱንና ከቁርአን ቀጥሎ የኢስላም ሁለተኛው ምንጭ ነው። ነገሮችን በመፍቀድ እና በመከልከል የቁርአንን አይነት ሚና ይጫወታል። የፈርድ: የሱንና: ሙስተሐብ መርህና ሌሎች ሸሪዓዊ መስፈርቶችን ያስቀምጣል። የቁርአንን እምቅ መልእክት ጥልቅ ይዘቱን ይተነትናል።

#የሱንና_አይነቶች
1)ሱነቱል ቀውልየህ (ንግግራቸው)
የሱንና የመጀመሪያው አካል የነብዩ ሙሀመድ ሰዐወ ንግግሮች ናቸው።
2) ሱነቱል ፊእልየህ (ተግባራቸው)
ይህ የሱንና ክፍል የነቢዩን ተግባራት የሚያካትት ሲሆን በቁርአን የተገለፁ ትእዛዛትን ተግብረው ያሳዩበት መልክ ነው።
3)ሱንና ተቅሪርየህ
ይህ የሱንና ክፍል ሌሎች ሲሰሩት አይተው ያፀደቁት መልካም ስራ ነው።

@abduftsemier
@abduftsemier