Get Mystery Box with random crypto!

ጌታዬ ሆይ! ሀገራችንን ሰላም አድርግልን!።ጌታዬ ሆይ! አቅማችን ዝሏል፣ ጉልበታችንም ታክቷል፣ ሀይ | نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

ጌታዬ ሆይ! ሀገራችንን ሰላም አድርግልን!።ጌታዬ ሆይ! አቅማችን ዝሏል፣ ጉልበታችንም ታክቷል፣ ሀይሉም ብቃቱም ያንተው ነውና እባክህን ሀገራችንን ሰላም አስፍንባት!!።

رَبِّ اجْعَلْ هَـذَا الْبَلَدَ آمِناً

ኢላሂ! ምንም'ኳን ወንጀላችን ቢበዛ፣ ከኛ ወንጀል ራህመትህ ሰፊ ነውና በራህመትህ ከለላ ውሥጥ አኑረን።

رَبِّ اجْعَلْ هَـذَا الْبَلَدَ آمِناً

ያኢላሃና! እባክህን ለፖለቲካ ፉቾታ እኛን እራት አታድርገን፣ ጌታችን ሆይ! መጥፎ ሰዎች ሚስኪኑን ህዝብ ገለው የጥቅማቸው መዳረሻ እያደረጉን ነውና አንተው ተበቀልልን።

رَبِّ اجْعَلْ هَـذَا الْبَلَدَ آمِناً

ጌታዬ ሆይ! በልጅ አንደበቴ ለመንኩህ እባክህን ዱዓዬን ተቀበለኝ! (አሚን)

እዝነትህን ከጃዩ ሚስኪኑ ባርያህ
አብደረህማ አማን ነኝ
t.me/abdu_rheman_aman