Get Mystery Box with random crypto!

Abbay media ዓባይ ቲቪ

የቴሌግራም ቻናል አርማ abbay_media — Abbay media ዓባይ ቲቪ A
የቴሌግራም ቻናል አርማ abbay_media — Abbay media ዓባይ ቲቪ
የሰርጥ አድራሻ: @abbay_media
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 613
የሰርጥ መግለጫ

#መረጃ_አይናቅም ‼️ @Daves_Art
ትኩስ ና አዳዲስ የሀገር ውስጥ ና የአለም ዜናዎችን በፍጥነት ሰብስበን ወደናንተ እናደርሳለን
#ለእውነት ና #ለትክክለኛ #መረጃ ብቻ እንሰራለን።
አቦይ ሚዲያ የእርሶ፣ የአንተ፣ የአንቺ፣ የእናንተ፣ የኛ የሁላችንም ድምጽ ነው!
መረጃዎቹን ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ አብሮነታችሁ ያሳዩ
አባይ ሚዲያ ሁሉ ነገሮ ስለ ኢትዮጵያ 🇪🇹

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-14 10:57:20
በህወሃትና በሸኔ አማራንና ኦሮሞን የማባላት እንቅስቃሴ በዜጎች ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎች መበራከታቸውን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ፡፡

ህወሃትና ኦነግ ሸኔ በዋነኛነት አማራንና ኦሮሞን አባልተን ይህን ሀገር ለእኛ እንደሚመች አድርገን እንቀይራለን በሚል እምነት በሚያደርጉት የተናበበ እንቅስቃሴ፤ባልታጠቁ ዜጎች ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎች መበራከታቸውን የትምህርት ሚኒስትሩና የኢዜማ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል፡፡

ህጻን ልጅና አዛውንትን በመግደል የፖለቲካ አላማን ማስፈጸም አይቻልም ያሉት ሚኒስትሩ፤ ሰዎች ሙሉ ለሙሉ የሞራል ስብዕናቸውን አጥተው ወደ አውሬነት ተቀይረው ህጻን ልጅና አዛውንት የሚገድሉበት ደረጃ ላይ ሲደርሱ የፖለቲካ አላማ ማስፈጸሚያ መሆኑ ይቆምና እብደት ይሆናል ብለዋል፡፡

ፕሮፌሰሩ ከዘመን መጽሄት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፤ እንደ ታጣቂ ቡድን ውጊያ የሚባለው ከወታደሮች ጋር መግጠም መሆኑን ጠቅሰው፤ መሳሪያ ያልታጠቀ ሰላማዊ ህዝብን መግደል ሽብርተኝነት ነው ብለዋል።

መንግሥት ህብረተሰቡን ለመከላከል በፀጥታ ኃይሎች ከሚወስደው እርምጃ ባሻገር ህብረተሰቡም ራሱን እንዲጠብቅ ማድረግ አለበት ያሉት ፕሮፌሰሩ፤ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ሆነው ችግር የሚፈጥሩ አንዳንድ አካላትን በአግባቡ ፈትሾ ራሱን ማጽዳት ይጠበቅበታል ሲሉ አሳስበዋል።

@Abbay_Media
1.3K views07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 10:51:14

1.1K views07:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 22:50:01

1.3K views19:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 22:49:34

1.3K views19:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 16:38:58

1.4K views13:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 14:15:34
"#Man_Yikenes (ማን ይቀነስ) በአርቲስት ሸዋፈራው ደሳለኝ የሚቀርብ ልብ አንጠልጣይ የጨዋታ ትዕይንት (Game Show).

ዘወትር እሁድ ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት በዓባይ ቴሌቪዥን

Sunday @ 7:00 PM only on Abbay TV"
1.5K viewsedited  11:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 12:15:59
የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ምትኩ ካሳ በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት ምትኩ ካሳ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረውዛሬ በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ውለዋል።

በፌደራል ፖሊስ በወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የሙስና ወንጀሎች ምርመራ መምሪያ ሀላፊ ረዳት ኮሚሽነር ታደሰ አያሌው እንደገለጹት ኮሚሽነሩ በቁጥጥር ስር የዋሉት ኤልሻዳይ ከተሰኘ በጎ አድራጎት ማህበር ባለቤት ጋር በመመሳጠር የሙስና ወንጅል ፈፅመዋል በሚል በመጠርጠራቸው ነው።

ይህ ኤልሻዳይ የተሰኘ ድርጅት በአዋሽ፣ በአዳማ፣ በሀዋሳ፣ በእንጅባራ በመሳሰሉ አካባቢዎች ተፈናቃዮች በሌሉበት ተፈናቃዮች አሉ በማለት በተደጋጋሚ ጊዜ የእርዳታ እህልና አልባሳት በመረከብ ሽጦ ለተጠርጣሪው መኖሪያ ቤት መግዛቱ በምርምራ መረጋገጡን ነው ረዳት ኮሚሽነር ታደሰ የተናገሩት።

ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ ሰፊ ክትትል ሲያደርግ እንደነበረም ረዳት ኮሚሽነሩ አብራርተዋል::

@Abbay_Media
1.5K views09:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 12:10:28
በኦሮሚያ ክልል በፀጥታና በድርቅ ምክንያት ከ50 ሺህ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው መሰተጓጎላቸውን አስታወቀ፡፡

በኦሮሚያ ክልል በ2014 በጀት ዓመት በፀጥታና በድርቅ ምክንያት ከ50 ሺህ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው መሰተጓጎላቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሰታውቋል።

የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተሮ ቶላ በሪሶ የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ በበጀት ዓመቱ 10 ነጥብ 6 ሚሊየን ተማሪዎች ወደ ትምህርት የገቡ መሆኑን ገልፀው በዚህም ከእቅዱ 92 በመቶ ማሳካቱን ተናግረዋል።

የ2014 ዓ.ም በትምህርት ዘርፍ ከፍተኛ ስራና ለውጥ የታየበት ነው ያሉት ቢሮው ኃላፊ በተማሪዎች ውጤት ላይ ለውጥ የታየና በትምህርት ዘመኑ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 52 ነጥብ 8 በመቶው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባቸውን ውጤት ማስመዝገባቸውን አስታውቀዋል።

በፀጥታና በድርቅ ምክንያት ከ50 ሺህ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው መሰተጓጎላቸውን ጠቅሰው፣ በተሰራው ሰፋፊ ስራ አብዛኞቹ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ተመልሰው የሚጠበቅባቸውን ትምህርት መውሰዳቸውን አውስተዋል።

@Abbay_Media
1.3K views09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 12:09:40
መንግስትን ወክሎ ከህወሃት ጋር የሚደራደረው የሰላም አማራጭ ዐቢይ ኮሚቴ ወደ ስራ መግባቱን አስታወቀ፡፡

የሰላም አማራጭ አብይ ኮሚቴው የመጀመሪያ ስብሰባውን ማካሄዱን የኮሚቴው አባል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አሰታውቀዋል።

ኮሚቴው በአፍሪካ ሕብረት መሪነት ከህወሃት ቡድን ጋር ለሚካሄደው ንግግር የራሱን የአሰራርና ሥነምግባር አካሄድ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉንም አማባሳደሩ ገልጸዋል። በንዑሳን ኮሚቴዎች በመደራጀትም ኃላፊነት ተከፋፍሎ ስራውን ጀምሯል ሲሉ አስታውቀዋል።

መንግሥት ከህወሃት አመራሮች ጋር ለመደራደር በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ሰብሳቢነት የሚመራ ሰባት አባላት ያሉት የሰላም አማራጭ ዐቢይ ኮሚቴ መሰየሙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለፓርላማው መግለጻቸው ይታወሳል።

ተደራዳሪ ቡድኑ በውስጡ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የፍትህ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ ሌ/ጄ ብርሃኑ በቀለ፣ ዶ/ር ጌታቸው ጀምር እና አምባሳደር ሐሰን አብደልቃድርን አካትቶ መያዙም መገለጹም ይታወሳል።

መንግሥት ተደራዳሪዎችን ይፋ አድርጎ ሥራ መጀመራቸውን ቢያሳውቅም ከትግራይ ክልል አመራሮች በኩል ግን እስካሁን ድረስ ተደራዳሪዎችን በተመለከተ የተሰጠ መረጃ የለም፡፡

ሁለቱ አካላት ባለፈው ሰኔ ወር በአሩሻ ታንዛንያ ይደራደራሉ ተብሎ የነበረ ቢሆንም ሳይካሄድ መቅረቱ ይታወቃል።

@Abbay_Media
1.3K views09:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 10:54:38

1.5K views07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ