Get Mystery Box with random crypto!

Abbay media ዓባይ ቲቪ

የቴሌግራም ቻናል አርማ abbay_media — Abbay media ዓባይ ቲቪ A
የቴሌግራም ቻናል አርማ abbay_media — Abbay media ዓባይ ቲቪ
የሰርጥ አድራሻ: @abbay_media
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 613
የሰርጥ መግለጫ

#መረጃ_አይናቅም ‼️ @Daves_Art
ትኩስ ና አዳዲስ የሀገር ውስጥ ና የአለም ዜናዎችን በፍጥነት ሰብስበን ወደናንተ እናደርሳለን
#ለእውነት ና #ለትክክለኛ #መረጃ ብቻ እንሰራለን።
አቦይ ሚዲያ የእርሶ፣ የአንተ፣ የአንቺ፣ የእናንተ፣ የኛ የሁላችንም ድምጽ ነው!
መረጃዎቹን ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ አብሮነታችሁ ያሳዩ
አባይ ሚዲያ ሁሉ ነገሮ ስለ ኢትዮጵያ 🇪🇹

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-25 10:28:16
የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር አሸባሪው ህወሓት የፈፀመው ዝርፊያ አፀያፊና አሳፋሪ ነው አለ፡፡


አሸባሪው ህወሓት መቀሌ ከሚገኘው የዓለም ምግብ ድርጅት መጋዘን ላይ የፈፀመው ዝርፊያ አስፀያፊ እና አሳፋሪ መሆኑን የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ባስሌ ተናገሩ።


የሽብር ቡድኑ ትናንት ጠዋት ላይ መቀሌ ወደሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን በሀይል በመግባት 12 የነዳጅ ቦቴዎችን በአጠቃላይ 570 ሺህ ሊትር ነዳጅ መዝረፉን ተመድ መግለፁ ይታወቃል።


ይህን ድርጊቱን አስመልክተው ዋና ዳይሬክተሩ ባወጡት መግለጫ የህወሓት ድርጊት አስፀያፊና አሳፋሪ መሆኑን ገልፀዋል።


ነዳጅ ከሌለ በሚሊየን የሚቆጠሩ የሰብዓዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎችን መድረስ እንደማይቻል ነው የጠቆሙት።


በመሆኑም ቡድኑ የዘረፈውን ነዳጅ በአስቸኳይ እንዲመልስ አሳስበዋል።


@Abbay_Media
3.0K views07:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 20:55:21

2.7K views17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 19:07:10

2.6K views16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 15:44:51 ለህወሓት ቡድን የጦር መሳሪያ በመጫን በሱዳን አልፎ የኢትዮጵያን አየር ክልል ጥሶ የገባ አውሮፕላን ትናንት ሌሊት 4 ሰዓት ላይ በአየር ሃይል ተመትቶ መውደቁ ተገለጸ

ትናንት ሌሊት 4 ሰዓት ላይ የኢትዮጵያን መዳከም የሚፈልጉ፤ ለዚሁም ለዘመናት የሚንቀሳቀሱና ህወሃትን በመደገፍ ላይ የሚገኙ ታሪካዊ ጠላቶች ንብረት እንደሆነ የሚታመን አውሮፕላን ለሽብር ቡድኑ የጦር መሳሪያ ጭኖ በሱዳን አልፎ የኢትዮጵያን አየር ክልል ጥሶ ሲገባ በጀግናው አየር ሃይል ተመትቶ መውደቁ ተገልጿል።

ሠራዊቱ የአገሩን ሉዓላዊነት ለማስከበር ከመቼውም ጊዜ በላቀ ኹኔታ ዝግጁ መሆኑም ተገልጿል።

በአገር መከላከያ ሠራዊት የመከላከያ ህብረት ዘመቻ ዋና መምሪያ የመከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊ ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ላለፉት በርካታ ወራት ከፍኛ ወታደራዊ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየው አሸባሪው ህወሃት ካለፉት ኹለት ሳምንታት ጀምሮ ኃይሉን ለውጊያ ሲያስጠጋ ነበር።

በየጊዜውም ተኩስ እየከፈተ የአገር መከላከያን ሲተነኩስ መቆየቱንም ነው ያነሱት።

ቡድኑ መንግስት የዘረጋውን የሰላም አማራጭ ከቁብ ሳይቆጥርና የሰላም ሂደቱ ቴክኒካሊ ፈርሷል ብሎ መግለጫ ባወጣ ማግስት ነሐሴ 17 ቀን 2014 ሌሊት 11 ሰዓት ላይ በቆቦ ግራና ቀኝ ባሉ አካባቢዎች፣ በዞብል ተራራ፣ በቢሶበርና በወትወት ውጊያ መክፈቱን ገልጸዋል።

በዚህም የተኩስ አቁም ሥምምነቱን ማፍረሱን ጠቅሰው፤ የሽብር ቡድኑ እየላከ ያለው ጀሌ በአገር መከላከያ ሠራዊትና በጸጥታ ሃይልች እየተለበለበ ነው ብለዋል።

ሜጀር ጀኔራሉ አክለውም፤ በሱዳን አድርጎ የአየር ክልላችንን ጥሶ በሁመራ ሰሜናዊ ክፍል በኩል ወደ ትግራይ ሊያልፍ የነበረና ለሽብር ቡድኑ የጦር መሳሪያ ሊያቀበል የነበረ የማንንቱ ያልታወቀ አውፕላንም በጀግናው አየር ሃይል ሌሊት አራት ሰዓት ላይ ተመትቶ መውደቁን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስደፈር የሽብር ቡድኑን እየጋለቡ ያሉ ሃይሎች ቢኖሩም የአገር መከላከያ ሠራዊትና ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ለማስክበር በተጠንቀቅ ላይ መሆናቸውን ጠቅሰዋል

በቀጣይም የሽብር ቡድን አገር የማፍረስ ህልሙን ትቶ ወደ ሰላማዊ መፍትሔ ካልመጣ እስከመጨረሻው እርምጃ ለመውሰዱ ሙሉ ዝግጅተ መደረጉን ጠቅሰዋል።

አሁን የመከላከል እርምጃ እየተወሰደ ሲሆን፤ በቀጣይም የማጥቃት እርምጃዎች እንደሚኖሩ ነው ሜጀር ጀኔራሉ የጠቀሱት።

@Abbay_Media
2.6K viewsedited  12:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 15:26:28

2.4K views12:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 17:36:01
በሙስና የተጠረጠሩት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሀላፊዎች ከሃላፊነታቸው ተነሱ፡፡

የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ የነበሩትን ጨምሮ ሌሎች የስራ ሀላፊዎች ከሀላፊነታቸው የተነሱት በክፍለ ከተማው በተንሰራፋው ሙስና ምክንያት መሆኑ ተገልጿል፡፡

የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ትናንትና ስራ የጀመሩት አቶ ጥላሁን ሮባ እንደተናገሩት ከሀላፊነታቸው ከተነሱት የክፍለ ከተማ ሀላፊዎች መካከል የመሬት ልማት ማኔጅመንት ጽ/ቤት እና የግንባታ ፈቃድ ሀላፊዎች ከነምክትሎቻቸው ይገኙበታል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስታደር የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ነባር ሀላፊዎች አንስቶ በአዲስ እየተካ ያለው ህዝብ ያቀርብ የነበረውን የመልካም አስተዳደር ቅሬታ መነሻ አድርጎ ባደረገው ማጣራት ነው ሲሉ ስራ አስፈፃሚ ተናግረል፡፡

በክፍለ ከተማው የሚሰጡ የመሬትና የግንባታ ፈቃድ አገልግሎቶች ሙስና በመንሰራፋቱ ለጊዜው መቆማቸውን ዋና ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል፡፡ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በተለይ ከመሬትና ከግንባታ ፈቃድ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ የሆነ ሌብነት እንደሚፈፀም በተደጋጋሚ መገለጹ ይታወሳል፡፡

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ 11 ክፍለ ከተማ ሆኖ የተዋቀረው አምና በጥቅምት ወር ነው፡፡

@Abbay_Media
2.5K views14:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 17:34:41
በሐረሪ ክልል ከ25 ኪሎ በላይ የሚመዝን አደንዛዥ ዕፅ ተያዘ፡፡

በሐረሪ ክልል ከ25 ኪሎ በላይ የሚመዝን ካናቢስ አደንዛዥ ዕፅ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።

አደንዛዥ ዕፁ ከሻሸመኔ አትክልት ጭኖ ሲጓዝ በነበረ አይሱዙ መኪና ላይ በተደረገ ፍተሻ ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉን የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል አስተባባሪ ምክትል ሳጅን ጃሚ አብዱረህማን ገልጸዋል።

በተጨማሪም በሕግ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ግምቱ ከ80 ሺህ ብር በላይ የሆነ በጤና ባለሞያ የተከለከለ መድኃኒት በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዋል።

የክልሉ ጤና ቢሮ በመድኃኒቶቹ ላይ ባደረገው ምርመራም ለጤና ጉዳት የሚያመጡ መሆናቸው ተረጋግጧል ብለዋል።

ሕገ-ወጥ መድኃኒቱ እና አደንዛዥ ዕፁ ከፖሊስ አልፎ ወደ ኅብረተሰቡ ቢደርስ የሚያስከትለው ጉዳት የከፋ ሊሆን ይችል እንደበርም ተገልጿል።

ኅብረተሰቡም መሰል እንቅስቃሴዎችን በማጋለጥ እርምጃ እንዲወሰድ እያደረጉ ያሉትን ትብብር አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተገልጿል።

@Abbay_Media
2.1K views14:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 17:33:02
የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ተሰርቆ ወጥቷል በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑ ተገለጸ፡፡

መስከረም 30 ቀን 2015 መሰጠት የሚጀምረው የ2014 ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና " ተሰርቆ ወጥቷል " በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆነን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " የዘንድሮ " ነው ተብሎ የሚሰራጨው ፈተና በ2013/14 (2021) ዓ.ም የተሰጠ እንደሆነ ያስረዱት የአገልግሎተ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ከበደ ከፈተና ስርቆት ጋር በተያያዘ እተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን የገልፀዋል።

የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ድረስ በሁለት ዙር እንደሚሰጥ የተገለጸ ሲሆን በአጠቃላይ በሁለት ዙር በሚሰጠው ፈተና ከ984,000 በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ የተገለጸ ሲሆን ከዚህም ውስጥ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር 622,739 መሆኑን አመልክተዋል።

ፈተናው ተዘጋጅቶ እየታተመ ሲሆን ፈተናው እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ ተፈታኞች እራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸውም ተገልጿል፡፡

@Abbay_Media
2.0K views14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 14:03:17

2.0K views11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 12:08:01
የህዳሴው ግድብ ለልማት ያለንን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ ነውሲሉ አምባሳደር ስለሺ ተናገሩ፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአንድነታችን ድንቅ ማሳያና ለልማት ያለንን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ ነው ሲሉ አምባሳደር ስለሺ በቀለ ተናግረዋል፡፡

በዋሺንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያና የምስጋና ስነ ስርዓት የተካሄደ ሲሆን ለግድቡ ግንባታ የሚውል ከ70 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በላይ ተሰብስቧል፡፡

ለህዳሴ ግድብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ በተዘጋጀው ድረ-ገጽ የተሰበሰበው 310 ሺህ ዶላርም ለመንግሥት ገቢ ተደርጓል።

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለህዳሴ ግድብ በገንዘብ፣ በእውቀት፣ በውግንና፣ በማህበራዊ ትስሰር ገጾች ቅስቀሳ፣ በምርምርና በተለያዩ መስኮች እያደረጉት ያለውን ድጋፍ አድንቀዋል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በበኩላቸው፥ የህዳሴ ግድብን ዘርፈ ብዙ ጥቅም የኢትዮጵያን የለውጥና እድገት ህልሞች ለማሳካት ልናውለው ይገባል ብለዋል።

ተሳታፊዎችም ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚያደርጉት ድጋፍ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

@Abbay_Media
2.0K views09:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ