Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያውያን ታዳጊ ህፃናት በአሜሪካ በተካሄደው የአለም አቀፍ የሮቦ ፌስት ውድድር አሸናፊ ሆኑ * | Abrehot Library

ኢትዮጵያውያን ታዳጊ ህፃናት በአሜሪካ በተካሄደው የአለም አቀፍ የሮቦ ፌስት ውድድር አሸናፊ ሆኑ
*

ኢትዮጵያውያኑ ሶስት ሽልማቶችን የግላቸው ያደረጉ ሲሆን የመጀመሪያው ከ 10 አመት በታች በተወዳደሩበት ሮቦ ፓሬድ የውድድር ዘርፍ ተሸልመዋል።

ሁለተኛው ደግሞ በሲንየር ኤግዚቢሽን ከ14 -16 አመት ስፔሻል አዋርድ ሽልማትንም ማግኘት ችለዋል።

በጁንየር ኤግዚብሽን ዘርፍ ደግሞ በአለም አቀፍ ውድድሩ የሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።

እንዲሁም ከየውድድሩ ከ 1-3 ለወጡ ተወዳዳሪዎች የሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

አሜሪካ በሚገኘው የሚችጋን ላውረንስ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው ውድድር 23 ታዳጊ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውን ወክለው በተለያዩ ዘርፎች ለውድድር መቅረባቸው ይታወሳል።

ተወዳዳሪዎቹ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ድጋፍ ፣ አብርሆት ላይብራሪ ከአቦጊዳ የሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ ማዕከል ጋር በመተባበር ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን በአለም አቀፍ መድረኮች ለማወዳደር በገቡት ስምምነት መሰረት የተካሄደ ነው።

የሮቦ ፌስት ውድድር በሎረንስ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በአሜሪካን ሚችጋን ክፍለ ግዛት ውስጥ የሚሰጥ አለም አቀፍ ውድድር ሲሆን ዋነኛ አላማውም ሳይንስና ቴክኖሎጂን በማበልፀግ ዝንባሌው ያላቸውን ታዳጊ ህፃናትን በዘርፉ ከፍ ወዳለ ደረጃ ማሸጋገር ነው።