Get Mystery Box with random crypto!

#AAU የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ካላንደር ላይ ለውጥ አደረገ | AAU,School of Law Info Center⚖️

#AAU

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ካላንደር ላይ ለውጥ አደረገ።

የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ከትምህርት ሚኒስቴር በተላለፈ ትእዛዝ መሰረት የዩኒቨርሲቲው ግቢዎች በሙሉ ከመስከረም 28 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም ለአስራ ሁለተኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና አገልግሎት ስለሚዉሉ በአካዳሚክ ካላንደሩ ላይ ለዉጥ ማድረጉን ገልጿል።

በዚህም ፦

1ኛ፥ ሁለተኛ አመትና ከዚያ በላይ የቅድመ ምረቃ (Undergraduate) ተማሪዎች ምዝገባ ጥቅምት 22 ቀን እና ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም

2ኛ፥ አዲስና ነባር የድህረምረቃ(postgraduate) ተማሪዎች ምዝገባ ጥቅምት 21 ቀን 2015 ዓ.ም ሲሆን
3ኛ፥ ትምህርት የሚጀመረዉ ሐሙስ ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።

4ኛ፥ በ2014 ዓ.ም የገቡ የአንደኛ አመት ተማሪዎች በአስራ ሁለተኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ምክንያት የሁለተኛ ሴሚስተር ትምህርት ተቋርጦ መስከረም 21 ቀን 2015 ዓ.ም የዩኒቨርስቲውን ጊቢዎች ለቀው እንደሚወጡና ጥቅምት 19 ቀን 2015 ዓ.ም ተመልሰው ጥቅምት 21 ቀን 2015 ዓ.ም ትምህርት እንደሚጀምሩ ገልጿል።

#ማሳሰቢያ : ዩኒቨርሲቲው ከላይ ከተገለጹት ቀናት ዉጪ ወደ ግቢ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን አሳስቧል።

በተጨማሪም ከመስከረም 28 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም በየትኛውም የዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢዎች የተገኘ ማንኛውም ተማሪ ላይ የዲሲፕሊን ቅጣት እንደሚወሰድበት አስጠንቅቋል።

(አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር)

@AAU_Lawschool