Get Mystery Box with random crypto!

የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በክረምት የበጎ ፍቃድ መርሀ-ግብር ያስገነባቸውን የአቅመ-ደካማ ቤቶች | Addis Ababa Technical Vocational Training and Technology Development Bureau

የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በክረምት የበጎ ፍቃድ መርሀ-ግብር ያስገነባቸውን የአቅመ-ደካማ ቤቶች አጠናቅቆ ለባለቤቶቹ አስረከበ፡፡

ነሀሴ 19 ቀን 2014 ዓ.ም

ኮሌጁ በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ውስጥ ከሚገኙ የአቅመ ደካማ ቤቶች መሀከል የሁለት አረጋውያን ቤቶችን በመለየት ሙሉ በሙሉ አፍርሶ በመገንባት ነው በዛሬው እለት ያስረከበው፡፡

ቤቶቹ የተገነቡት በኮሌጁ አሰልጣኞች ሙሉ የጉልበት እና የሙያ ተሳትፎ መሆኑ የተለየ እንደሚያደርገው የኮሌጁ ዋና ዲን ወ/ሮ ጌጤነሽ ዘራብዛ ገልጸዋል፡፡

በቤቶቹ ርክክብ መርሀ-ግብር ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ቴክኒክ ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ምክትል ሃላፊ ወ/ሪት ፀዳለ ተክሉ በዚህ የቤት ግንባታ ሂደት ጉልበታቸውንና ሙያቸውን በነፃ ያበረከቱ የኮሌጁ አሰልጣኞችን አመስግነዋል፡፡ 

ወ/ሪት ፀዳለ የቤቶቹን ቁልፍ ለባለቤቶቹ ካስረከቡ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት ቢሮው በስሩ የሚገኙ ኮሌጆችን በማስተባበር የሚያከናውናቸውን ማህበረሰብ አቀፍ ተግባራት አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ቴክኒክ፣ ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በዘንድሮ የክረምት በጎ ፍቃድ መርሀ-ግብር በስሩ የሚገኙ ኮሌጆችን በማስተባበር በከተማ ደረጃ 40 የአቅመ ደካማ ቤቶችን በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡